በነገው ዕትም ከሀገር ውስጥ ዘገባችን የአሰልጣኝ ገብረ ክርስቶስ ቢራራና የኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ቡድን መቻል የሊጉን የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ በመሪነት ማጠናቀቁን ተከትሎ የቡድኑን አምበል ምንተስኖት አዳነ ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ በሊጉ ሁለተኛ ጨዋታ ላይ በባህርዳር ከተማ ከደረሰባቸው ሽንፈት ይልቅ ያበሳጫቸው ” ከባህርዳር ከተማ ይበልጥ በኢትዮጵያ ቡና የደረሰብን ሽንፈት አበሳጭቶኛል” ሲል ተናግሯል። አምበሉ አሁን ጊዜው ተለውጧል እያለ ነው….
“ተጋጣሚ ክለቦች ከእኛ አንድ ነጥብ ለማግኘት በመከላከል ላይ ያተኩራሉ” ሲልም መቻል ተፈሪ መሆኑን ተናግሯል…ቃለምልልሱን ይዘናል…..
*…… የሸገር ደርቢን ጨምሮ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሙሉ ጨዋታን አዲስ አበባ ላይ ማየት ካቃተን ከ40 ወራቶች በላይ አልፏል…ሊግ ኩባንያው ከ28-30ኛ ሳምንት ድረስ ያሉ 24 ጨዋታዎች በአዲስ አበባ ይካሄዳሉ ብሏል…በዚህ ዙሪያ የሚያተኩር ዘገባ ይዘናል
….በውጪ ዘገባ ደግሞ….
የኖርዊያዊው ማርቲን ኦዴጋርድ የተለወጠ ሚና ተጨዋቹን አግኖታል…የሻምፒየንስ ሊጉ ሽንፈት በመድፈኞቹ ጉዞ ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል ..? በዚህ ዙሪያ የሚያጠነጥን ዘገባ ይዘናል ….
** በአንድ ክለብ ውስጥ የተጀመረ የተጨዋችነት ዘመን እዚያው ክለብ ውስጥ ተጠናቆ ማየት ብርቅ እየሆነ ነው ..ለዛሬ የአንድ ክለብ ተጨዋቾችን መለስ ብለን እንቃኛለን…
የተቺዎቹን አፍ ስላዘጋው ኖርዌያዊው የግብ ቀበኛ ኤርሊንግ ብራውት ሃላንድ የምንላችሁ አለ….
አሰልጣኝ ጋርሺያ አሰልጣኝ ማዞሪ አሁን ደግሞ አሰልጣኝ ካልዞና ኔፕልስ ደርሰዋል …የናፖሊ ቤት ተከታታይ ለውጥን እናስቃኛችኋለን …
ብዙዎች ለሚካሂሎ ሞድሪክ ቸልሲ አልተመቸም እያሉ ነው …በዚህ ዙሪያ ዘገባ ይዘናል…
** የማን. ዩናይትድ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሃግ ምክትል አሰልጣኞችን ያውቋቸዋል…? ለዛሬ በነሱ ዙሪያ የሚያጠነጥን መረጃ ይዘናል…
….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን አካተናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…
….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ…