በነገው ዕትም በሀገር ውስጥ ዘገባችን ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወደ ከፍተኛ ሊግ በወረደበት አመት አምስት ጨዋታ እየቀረው ዳግም ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ማደጉን አረጋግጧል። ይህን ገድል የሰራው ደግሞ ለመሞዳሞድ አይመችም አይበላም አያስበላም የተባለለት አሰልጣኝ ሳምሶን አየለና የቡድን አባላቱ ከፍተኛ ሙገሳ እየቀረበላቸው ነው። በዚህ ስኬት የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው አሰልጣኝ ሳምሶን ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ስለውጤቱና ስለገጠመው ፈተና ተናግሯል። ” የስኬታችን መነሻ ውድድሩ ሲጀመር በተከታታይ ያደረግነውን አምስት ጨዋታ አሸንፈን 15 ነጥብ በመያዛችን ነው” የሚለው አሰልጣኙ ስለደረሰበት ፈተና ሲናገር “የላይሰንስና የውጤት ችግር የልምድ ክፍተት የስነምግባር ችግር ሳይኖርብኝ እንድገፈተር ተደርጌያለሁ” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል። ቃለምልልሱን ይዘናል….
*……በውጪ ዘገባ ደግሞ ………
*…… በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂው የማን.ዩናይትድና የአርሰናል ጨዋታ እሁድ ምሽት 12.30
ላይ በኦልድትራፎርድ ይካሄዳል። ለ241ኛ ጊዜ የሚደረገው ጨዋታ በቀይ ሰይጣኖቹ አሸናፊነት ይጠናቀቅ ይሆን..? ወይስ መድፈኞቹ ደርሶ መልስ ይረቱ ይሆን..? በዚህ ተጠባቂ ጨዋታ ዙሪያ የምንልዎ አለ…
*….. በአውሮፓ ክለቦች ሻምፒየንስ ሊግ የካርሎ አንቾሎቲ ሪያል ማድሪድ ለ18ኛ ጊዜ ለፍጻሜ አልፎ ለ15ኛ የውድድሩ ዋንጫ ሲፋለም በተመሳሳይም ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ሁለተኛ የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ለማንሳት በፍጻሜው ከማድሪድ ጋር ይፋጠጣል…… ስለ ሪያል ማድሪድ ድንቅ ጉዞና ስለ ዶርትሙንድ ተፈጥሯዊ መሪ ማት ሃመልስ የምንላችሁ አለ…..
*…. በአውሮፓ ክለቦች ሻምፒየንስ ሊግ የማይረሱ የፍጻሜ ጨዋታዎችን መለስ ብለን እናስቃኞታለን…
*…. ስለ ማን.ዩናይትድ የቀድሞ ኮከብ ዌይን ሩኒ ምን ይነገራል…? የማይረሱ ገድሎችን የከሰተው የምርጥ ታሪክ ባለቤቱ ግላዲያተሩ ሩኒ የራሱን ጉዞ መለስ ብሎ ያስቃኘናል….
*…..ሌስተር ሲቲ ከሻምፒዮንሺፕ ዳግም ወደ ነገሰበት ፕሪሚየር ሊጉ ተመልሷል ዳግምስ ይደምቅበት ይሆን…? መረጃዎችን ይዘናል….
….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…
….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ…