Google search engine

.. የሊግ ጉዞ ቀጥሏል …..

 

በየሳምንቱ ቅዳሜ ለንባብ የምትበቃው ሊግ ጋዜጣ  በነገው ዕለት ምርጥ ምርጥ ዘገባዎችን አካትታ እጅዎ ትገባለች….

በነገው ዕትም ከሀገር ውስጥ በሴቶችም እግርኳስ ላይ  ውጤታማ  የነበረውና ፊቱን ወደ ወንዶቹ እግርኳስ አዙሮ የአሁኑ የድሬዳዋ ከተማ ወንዶች ቡድን  አሰልጣኝ ሆኖ እየሰራ ያለው አሰልጣኝ አስራት አባተ  እንግዳችን ነው…  አሰልጣኙ የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ምክትል ሆኖ ዋሊያዎቹ ወደ ካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ ሲያልፉ የበኩሉን ሚና ተወጥቷል….. በድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኝነቱ ዙሪያ  ስጋት እንደሌለበት ቡድኑን ውጤታማ ለማድረግ እንደሚጥር ያስረዳው አሰልጣኝ አስራት ሌሎች ትኩረት የሚስቡ ምላሾችን ሰጥቷል …በወንዶች እግርኳስ ላይ  መቀጠል እንደሚፈልግ የሚገልጸው አሰልጣኝ አስራት “ስኬታማ ሆኜ ሉሲዎቹን ያልያዝኩ እኔ ብቻ በመሆኔ በሴቶች እግርኳስ  ተስፋ ቆርጫለሁ” ሲል የልቡን ቅሬታ ለሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ገልጿል። ቃለምልልሱን ይዘናል….

……በውጪ ዘገባ ደግሞ:…..

*** ዘንድሮ  ከመድፈኞቹ  አይነኬ ተጨዋቾች መሃል አንዱ  የመሃል ሜዳው ኮከብ ዴክላን ራይስ ነው… ስለዚህ አይነኬ ተጨዋች የምንላችሁ ነገር አለ…..

***  በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እያደር እንደ ወይን የጣፈጠ ተጨዋች ማነው ብትባሉ ማንን ትጠራላችሁ…? በርካቶችን ስለሚያስማማው እያደር ጣፋጩ ፈርኦን መሃመድ ሳላህ ያዘጋጀነው ዘገባ ተካቶበታል ….

*** ሰር ቦቢ ቻርልተን እንግሊዝና ማን .ዩናይትድ የሚኮሩበትን ታሪክ ከስተው ይቺን አለም በሞት ተለይተዋል ….ስለ ቦቢ ቻርልተን ትሩፋት የምንላችሁ አለ…

*** ሰማያዊያኑ ቸልሲዎች አዲስ ኮከብ አግኝተዋል እየተባሉ ነው …. ስለ አዲሱ ኮከብ ከሲቲዚኖች መንደር የተገኘው ፓልመር  ያዘጋጀነው ዘገባ አለን ….

***  ብራዚላዊው ኮከብ ኔይማር ከሜዳው  ውስጥ ጉዳት ባሻገር ከሜዳ ውጪም እክል ገጥሞታል … በብራዚላዊው ኮከብ አጠቃላይ  ከሜዳ ውስጥና ውጪ ጉዳትና እክል  ዙሪያ የምንላችሁ አለ…

….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን አካተናል …

ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም  ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…

….ቅዳሜና እሁድዎ  የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ….

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this:
P