Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ከባህርዳር ከተማ ይበልጥ በኢትዮጵያ ቡና የደረሰብን ሽንፈት አበሳጭቶኛል” “ተጋጣሚ ክለቦች ከእኛ አንድ ነጥብ ለማግኘት በመከላከል ላይ ያተኩራሉ” ምንተስኖት አዳነ /መቻል/

በአሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራና በቴክኒክ ዳይሬክተሩ ኢንስትራክተር አብርሃምም መብራቱ የተዋቀሩት መቻሎች የኢትትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አንደኛ ዙርን በመሪነት ጨርሰዋል። በቡድናቸው ጥንካሬና ተፎካካሪነት የመቻል ደጋፊዎች ቡድናቸው ላይ ተስፋ ጥለዋል። ከነልምዱ ይህን ክለብ እየጠቀመ ያለው ምንተስኖት አዳነ ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር በነበረው ቆይታ ጥሩ ቡድን እንዳላቸው መሪነታቸው በከፍተኛ የራስ መተማመን ውስጥ እንዲገኙ እንዳደረጋቸው ገልጿል።  ሙሉ ቃለምልልሱን ይከታተሉት፡፡

 

ሊግ:– ምንተስኖት ከሚዲያ ጠፋ.. .ምክንያት አለው..?

ምንተስኖት:– /ሳቅ በሳቅ/  ኧረ አልጠፋሁም፡፡ ውድድሩ አዲስ አበባ ስላልሆነ መሰለኝ….። ለነገሩ ሚዲያ ላይ የምቀርብበትም ምክንያት አልነበረም ለዚያ ይመስለኛል በነገራችን ላይ ለሚዲያ አልቀርብም ያልኩበት አጋጣሚም የለም …ሚዲያ ላይ ጠፍቼ ሳይሆን ሚዲያዎች ጠፍተው ነው../ሳቅ /

:- መቻል አንደኛውን ዙር  በ33 ነጥብ በመሪነት ጨርሷል…ምን ስሜት ይፈጥራል..?

ምንተስኖት:– ስሜቱ ደስ ይላል በአንደኛ ዙር ስለመራን ግን  ዋንጫ አንወስድም ዋንጫ አመቱ ሲጠናቀቅ በሚገኝ የነጥብ ብልጫ የሚገኝ  እንደሆነም እናውቃለን ያም ሆኖ  መሪ  ሆነን መጨረሳችን ትልቅ በራስ መተማመን ፈጥሮልናል ተጋጣሚዎቻችንም አክብረውን እንዲገቡ ያደርጋል ጥሩ  ተፎካካሪ እንደሆንን እንዲሰማን አድርጎናል  አሁንም ግን  በነጥብ ባለመራቃችን ሰለመራን ብቻ አንዘናጋም ሁለተኛ ዙር ጠንካራ ፉክክር እንደሚገጥመን እናውቃለን።

ሊግ:- ግን መሪ ሆኖ መጨረስ  በራስ መተማመናችሁን ይጨምራል አይደል..?

ምንተስኖት:- አዎ በራስ መተማመንንማ ይፈጥራል…

በራስ መተማመናችን እንዳለ ሆኖ  ለቀጣዮቹ ጠንክረን መዘጋጀት አለብን። በፕሪሚየር ሊጉ ሁለት ተከታታይ ጨዋታ መሸነፍ ታች እንደሚወስድ ካሸነፍን ወደላይ በደንብ ከፍ እንደምንል ስለምናውቅ መዘናጋት የለም ቀሪ  15 ጨዋታ አለ በዚህ ደግሞ የምንችለውን አድርገን ውጤት ማስጠበቅ ይጠበቃል።  ደግሞ ሰግተንም አንገባም

ሊግ:- መቻል 1ኛ ዙሩን መሪ መሆኑ ተጋጣሚዎቹ  እንዲያከብሩት  አያደርግም…?

ምንተስኖት:- አዎ ያደርጋል የሚጠበቅም ነው.. መቻል ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ካደገ ጀምሮ ተከታታይ ሁለት አመት ላለመውረድ ነበር ሲጫወት የነበረው …9ኛ አካባቢ ነበር ያጠናቀቀውም …አምና ተጋጣሚዎቻችን ነጥብ ለመውሰድ አጥቅተው ነበር የሚጫወቱት አሁን ግን በተቃራኒው ሆኗል… ከእኛ 1 ነጥብ ለማግኘት በአብዛኛው መከላከል ላይ ያዘነበለ አጨዋወት ነው ይዘው ነው የሚመጡት ያ ደግሞ ጥንካሬያችንን ማወቃቸውን ያሳያል። እኛም ከ3ኛ በታች አልነበርንም ዝቅ ካልን   3ኛ ወይም 2ኛ  ብንሆን ነው ረጅም ጊዜ የቆየው ሁለተኛነት ላይ ነው  ያ ደግሞ ስለኛ እንዲጠነቀቁ አድርጓቸዋል ማለት ነው…  ትልቅ ግምት እንዲሰጡን አድርጓል በዚህም ደስተኞች ነን ሁለተኛ ዙር ላይ ከዚህ በላይ ጠንክረው ስለሚመጡ እኛም እንዘጋጃለን።

ሊግ:- ስብስቡ ምርጥ የሚባል ነው..?

ምንተስኖት:- አዎ ጠንካራ ስብስብ አለን ….ብዙ ልምድ ያላቸው፣ የዋንጫ ማሸነፍ ታሪክ ያላቸው፣ በየክለቡ ውጤታማ የነበረ፣ በብሄራዊ ቡድንም ጥሩ ስኬት ያላቸውና ለድል የተራቡ ወጣቶችን የያዘ ስብስብ በመሆኑ ተፎካካሪ ሆነናል። በተቃራኒ  በሚገኙ ክለቦችም ጥሩ ጥሩ ተጨዋቾችን የያዙ አሉ…ያም ሆኖ ቡድናችን ጠንካራ አቋም ላይ መገኘቱን መካድ አይቻልም።

ሊግ:- በባህርዳር ከተማና በኢትዮጵያ ቡና  ብቻ ተሸነፋችሁ…የትኛው ያስቆጫል..?

ምንተስኖት:- በሁለቱም ሽንፈት ተበሳጭቻለሁ… በሽንፈት ደስ አትሰኝማ… በባህርዳር ከተማ የተሸነፍነው በሊጉ ሁለተኛ ሳምንት ላይ ነው  ገና ስላልተቀናጀን  የውድድሩ ጅማሬ ስለሆነ  ተምረንበት አልፈናል ከዚያ በኋላ ነው ተከታታይ ጨዋታዎችን ያሸነፍነው  በኢትዮጵያ ቡና የደረሰብን ሽንፈት ግን በይበልጥ አበሳጭቶኛል  ጥሩ ብቃት ላይ እያለን  ደረጃችን ከፍ ባለበት የመሪነት ልዩነቲታችንን ማስፋት በምንችልበት  ሰአት በመሆኑ ቅር አሰኝቶኛል።

ሊግ:- በዋንጫ ፉክክሩ ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ የምትለው ማነው…?

ምንተስኖት:– 15ቱም ክለቦች የመቻል ተፎካካሪ ናቸው ብዬ ነው የማስበው… አጠገባችን ያሉትም ሆኑ ታች ያሉት የእኛ ተፎካካሪ ናቸው ብዬ ነው አስባለሁ… ታች ያሉት በተከታታይ ካሸነፉ ወደላይ ስለሚመጡ  እድላቸውን ለመጠቀም ጠንካራ ፍልሚያ ስለሚያደርጉ ለኛ ተፋላሚ መሆናቸው አይቀርም  ብዙ ክለቦች ከ20 ነጥብ በላይ በመሆናቸው መፋለማቸው አይቀርም።

ሊግ:- ፕሪሚየር ሊጉ ጠንካራ ሆኗል ማለት ይቻላል..?

ምንተሴኖት:– ዘንድሮም በተለየ መንገድ ጠንክሯል ብዬ አላምንም ግን ቡድኖች አስተሳሰባቸውን ቀይረዋል ዋንጫ ማንሳት እንደሚቻል አምነው ቡድኖች መቅረብና መፋለም ጀምረዋል ብዬ አስባለሁ በተረፈ ውድድሩ ላይ የተለየ ጥንካሬ አላየሁም

ሊግ:-  ቅዱስ ጊዮረሰጊስ ለ3ኛ  ጊዜ ዋንጫ ቢያነሳ ለ15ታችሁ ኪሳራ አይሆንም..?

ምንተስኖት:– ኪሳራ ነው ብዬ አላስብም….ቅዱስ ጊዮርጊስ ልምድ ያላቸውና ወጣቶችን ተጨዋችች አቅፏል ከዚህ በፊት የነበረው ባህል ብዙ ኮከቦችን ብዙ ልምድ ያላቸውን ይይዛል አሁን ደግሞ ቁጥሩን ቀነስ አድርገውታል  ከመጀመሪያዎቹ ምርጥ 11 ተጨዋቾች ካየን ግን በብሄራዊ ቡድን ሳይቀር ልምድ ያላቸውን ነው  የያዘው….ተቀያሪ ቦታ ላይ ብዙ ወጣት ተጨዋቾች አሏቸው ምንም ጥያቄ የለውም ከሌሎች ክለቦች በተለየ  ብዙ ወጣት ተጨዋቾችን ይዘዋል። ዋንጫ የለመዱ ልጆችን እንደመያዛቸውም አሸናፊ ሊሆኑ የማይችሉበት ምክንያት የለም። ወጣቶቹም ከልጅነታቸው ጀምረው ቤታቸው ስለሆነ የማሸነፍ ስነልቡና ውስጥ ሆነው ነው የሚገቡት ይህም ተጠቃሚ ያደርጋቸዋል ብዬ አስባለሁ።

ሊግ:- በሊጉ ዘንድሮ  የተለየ ጠንካራ የምትለው ቡድን ገጥሞሃል..?

ምንተስኖት:- በመጀመሪያ ዙር በስብስብም ሆነ በሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጥሩ ቡድን ሆኖ አይቻለሁ… ጥሩ 11 አለው ተቀይረው ገብተው ክለቡን  ውጤታማ ማድረግ የሚችሉ ተጨዋቾችንም ይዟል የኛም ቡድን ሳይረሳ ማለቴ ነው።

ሊግ:-  ከሀድያ ሆሳዕና  ጋር ያለባችሁን ቀጣይ ጨዋታ እንዴት ትገልጸዋለህ..?

ምንተሴኖት:– ጠንካራ ፉክክር ይጠብቀናል ጠንካራ ቡድን እንደሆነ እናውቃለን ትንሽ ግብ የተቆጠረበትም ሃድያ ሆሳዕና ነው የመጀመሪያ ዙር ላይ 3ለ2 ነው ያሸነፍነው… በዚህኛው ግንኙነታችንም ለማሸነፍ ጠንክረን ገብተን  መሪነታችንን የምናስጠብቅበት ድል እናስመዘግባለን  ብዬ አምናለሁ

ሊግ:- አቤል ያለው ወደ ግብጽ ሄዷል …ሱራፌል ዳኛቸው ደግም ወደ አሜሪካ ሊጓዝ ነው …ምን ትመኝላቸዋለህ..?

ምንተስኖት:-  በጣም ደስ ብሎኛል …ብዙ ተጨዋቾች ወደ ውጪ የሚሄዱበት ዕድል እየተፈጠረ ነው በጣም ደስ ይላል ለሁለቱም  መልካም እድል እንዲገጥማቸውና ወደ ተሻለ  ሊግ ሄደው ራሳቸውን የሚያሳዩበት ሀገራቸውን የሚጠቅሙበት እንዲሆኑ እመኝላቸዋለሁ።

ሊግ:- አመቱ ሲያልቅ ለማሳካት የያዛችሁት እቅድ ምንድነው..?

ምንተስኖት:- ከጥሎማለፉ  ፉክክር  በጊዜ ነው የወጣነውና ሙሉ ትኩረታችን ፕሪሚየር ሊጉ ላይ ነው …የሚከፋፍለን ሌላ ውድድር ስለሌለ በትኩረት የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት እንጥራለን …እስካሁን ያለንበት ደረጃ  ጥሩ ነው ዋንጫ ለመውሰድ የሜዳ ላይ ፉክክር ብቻ ሳይሆን ጠንካራ አዕምሮ ይጠይቃልና  የአሸናፊነት ስነልቦና ያስፈልጋል ቡድናችን ደግሞ ቀስ በቀስ እያገኘ ነው በራስ መተማመኑና የአሸናፊነት ስነልቦናችን 100 ፐርሰንት ከደረሰ ጥሩ ድል ይኖረናል ብዬ አስባለሁ።

ሊግ:- አመሰግናለሁ….

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

P