Google search engine

ዋሊያዎቹ በወዳጅነት ጨዋታ በሌሴቶ ተረቱ *….አሰልጣኝ ገብረ መድህን የመጨረሻ ቀን ልምምዱን ሳይመራ ድሬዳዋ ሄዶ መድንን ልምምድ ማሰራቱ ጥያቄ ተነሳበት…

አበባ ስታዲየም  ከ40 ወራት ክልከላ በኋላ  ነገ ከቀትር በኋላ ሁለተኛውን   የዋሊያዎቹና የሌሴቶ ጨዋታን ያስተናግዳል። በ2013 የኢትዮጵያና የኒጀር ጨዋታ  በዋሊያዎቹ 3ለ0 አሸናፊነት መጠናቀቅን ተከቴሎ  ምንም ጨዋታ ሳይካሄድበት  ከ3 አመት ቆይታ በኋላ ከትላንት በስቲያ ሃሙስ  በኢትዮጵያና በሌሴቶ ብሄራዊ ቡድኖች መሃል የተካሄደው ጨዋታ አስተናግዶ  ሌሴቶ 2ለ1  አሸንፋለች።  ቶቦንሶ ጆንና ግብጠባቂው ሴክሆኔ ሞሮኔ ለሌሴቶ መስፍን ታፈሰ ለዋሊያቹ ግቦቹን ከመረብ አሳርፈዋል በተለይ ግብ ጠባቂው ከግብ እስከ ግብ ለግቶ ያስቆጠረው ግብ አሁን ድረስ አነጋጋሪ ሆኗል።

ከመጀመሪያው 45 ሁለተኛው 45 የተሻለ ቢሆንም ከጨዋታው  ሂደት   በላይ ትኩረት የሳበው ቡድኖቹ መሃል የተከሰተው ድብድብ ነው  የሌሴቶው ተጨዋች ረመዳን የሱፍን በመምታቱ አሰልጣኝ ገብረ መደህን ሃይሌ መሪነት የታጀበው ጸብ  በተጨዋቾች ጉንተላ መቀጠሉ አነጋጋሪ ነበር።

ከጨዋታው በኋላ አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሃይሌ” እግርኳስ ስሜታዊ ያደርጋል በባህሪዬ ዝምተኛ ነኝ ነገር ግን ዳኛው የእነሱን የሃይል አጨዋወት መቆጣጠር አሌቻለም ተጨዋቹ ሲማታ አጠገቡ ስለነበርኩ  በዚያ ስሜታዊ  ሆኛለሁ ያም ግን ልክ አይደለም” በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል።

ከሃሙሱ ጨዋታ ዋዜማ አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሃይሌ  የመጨረሻውን የዋሊያዎቹን ልምምድ  በመተው ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ የመድንን ልምምድ መምራቱ ጥያቄ ያስነሳ ሰሆን ሁለት ቦታ ሃላፊነት መያዝ ትርፉ ይሄ ነው በሚል ቅሬታ እየተሰማበት መሆኑ ታውቋል።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this:
P