በወቅቱ አበበ ምርጥ ብቃት ላይ የምትገኝበት እና ለአሸናፊነቱ ቅድሚያ ግምት የነበራት አትሌት ነበረች። ይሁንና በሙጨረሻዉ ዙር 300 ሜትር አካባቢ ሲቀረው ተጠልፋ ወድቃለች።ተስፋ ባለመቁረጥም ከወደቀችበት ተነስታ 5ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
ተከታትለው የገቡት ሁለቱ የቱርክ አትሌቶች አስሊ ካፊር እና ጋሚዝ ብሉት የአበረታች ቅመም ተጠቅመው መገኘታቸው ስለተረጋገጠ ሜዳሊያቸውይ በመቀማታቸው አበባ አረጋዊም ለራሷም ለአገሯም በዛሬው እለት በፓሪስ ኤፍል ታወር አካባቢ በተዘጋጀ ደማቅ ስነስርዓት የነሃስ ሜዳሊያዋን በክብር ተቀብላለች።
በዚህም በለንደን 2012 ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ አስመዝግባ የነበረው ሜዳሊያ በአንድ ነሃስ ጨምሮ 3 ወርቅ፣ 2ብር እና 3 ነሃስ መሆን ችሏል።
በዚህ የዉጤት ሽግሽግ መሰረት ለባህሬን የምትሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊት ማሪየም የሱፍ ጀማል ወይም ዘነበች ቶላ 3ኛ ወታ የነበረ ሲሆን አሁን የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሆናለች። ሩሲያዊቷ ታቲያና ቶማሾቫ ደግሞ ከ4ኛ የ2ኛ ደረጃን የብር ሜዳሊያን ተረክባለች።
አበበ አረጋዊ ከለንደን ኦሊምፒክ በኋላ ዜግነቷን ለሳዊዲን ቀይራ የተለያዩ አለም አቀፍ ውድድሮችን አድርጋለች።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በቤጂንግ 2008 ኦሊምፒክ የ5000ሜትር ውድድር ጥሩነሽ ዲባባን ተከትላ 2ኛ የወጣችው ሌለኛዋ ትውልደ ኢትዮጽያዊት የቱርክ አትሌት ኤልቫን ዐቢይ ለገሰም በተመሳሳይ ችግር ሜዳሊያውን ተቀምታ በምትኩ ሶስተኛ ላይ ለነበረችው መሰረት ደፋር ተወስኗል። መሰረት ላሁኑ ልክ እንደ አበባ ሁሉ ሜዳሊያዋን ያልተቀበለችው ስነስርዓቱ እንዲመቻች የአለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጥያቄ በአግባቡና በጊዜ ምላሽ ማግኘት ባለመቻሉ ነው። በቀጣይ ሌላ ዝግጅት ግን የብር ሜዳሊያዋን እንደምትቀበል ለማወቅ ተችሏል።
የኢትዮጵያ የቤጂንግ 2008 ኦሊምፒክ ሜዳሊያ ብዛትም በአንድ ብር ከፍ ብሏል።