Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“የላይሰንስና የውጤት ችግር የልምድ ክፍተት የስነ ምግባር ችግር ሳይኖርብኝ እንድገፈተር ተደርጌያለሁ” “የስኬታችን መነሻ ተከታታይ ያደረግነውን አምስት ጨዋታ አሸንፈን አስራ አምስት ሙሉ ነጥብ ማግኘታችን ነው” አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ /ኢትዮ ኤሌክትሪክ/

ለመሞዳሞድ  በዝውውር ገበያው  እጁን ሙስና ውስጥ ላለመክተት  ሲጥር  ይታያል አይበሉም አያስበሉም ተብለው በጎራሾቹ ከሚተቹ ጥቂት አሰልጣኞችጠመሃል አንዱ ነው። ለዲሲፕሊን  ለመልካም ባህሪና ለትጋት ቅድሚያ ይሰጣል ይሉታል የሚያውቁት በአሰልጣኝነት ህይወቱ  ውጤት ቢኖረኝም በስነምግባር አክራሪነቴ ወደጎን ተገፍቼ ኖሬያለሁ ሲልም ይናገራል.. በተጨዋችነት ዘመኔ ሰፊ ስለነበር ወደ አሰልጣኝነቱ ለመመለስ ኮርስ መውሰድ ላይሰንስ መያዝ  ከታች ጀምሮ ከወጣቶች ጋር እየሰራሁ ወዱላይ ከፍ ማለት የሚለው አቋሜ ብዙ ነገር ላይ አጉላልቶኝም ቢሆን አሳክቻለሁ ሲል ይናገራል ወደ አሰልጣኝነት ሲመጣ ከምክትል አሰልጣኝነት ጀምሮ እስከ ዋና  አሰልጣኝነት ከሱፐር ሊግ እስከ ፕሪሚየር ሊግ ሰርቷል። የመጀመሪያ የአሰልጣኝነት ህይወቱን በዋና አሰልጣኝነት  የሰራው  ለሃረር ቢራ አንድ አመት ረዳት ሁለት አመት ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ሰርቷል…፣ ከዚያ የአሰልጣኝነት ጉዞው ሲቀጥል  በዳሽን ቢራ፣ በስሁል ሽረ፣  በድሬዳዋ ከተማ የአሰልጣኝነት ጉዞ ካደረገ በኋላ የዘንድሮ የውድድር አመት ለሶስት አመት ኢትዮ ኤሌክትሪክን ለማሰልጠን ተስማምቶ በ2015 ወደ ከፍተኛ ሊግ ወርዶ ከአንድ አመት ቆይታ በኋላ ወደ ፕሪሚየር ሊን  እንዲያድግ አድርጎታል.. ይሄ አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ይባላል ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ባደረገው ቆይታ ለቀረቡለት ጥያቄዎች ምላሹን ሰጥቷል።

ሊግ:-  ለትንሳኤውም ሆነ ለዳግማዊ ትንሳኤ  እንኳን አደረሰህ..?

ሳምሶን:- እንኳን አብሮ አደረሰን አመሰግናለሁ…ትልቅ በዓል መሆኑ ይታወቃል ዓቢይ ጾምን  እንደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት አማኝነቴ ረጅሙን ጾም ጾሜ ጨርሻለሁ በዚህም ደስ ብሎኛል  የዘንድሮ ፋሲካ ደግሞ ድርብ ደስታ ውስጥ ሆኜ ነው። ያከበርኩትና ትልቅ ትርጉም የነበረው ነው የውድድር አመቱ ላይ በስኬት በመጨረሴ በአሉን በጋራ ድል አክብሬዋለሁና ትልቅ ደስታ ላይ ነበርኩ  በዚሁ አጋጣሚ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ መልካም የዳግመ ትንሳኤ በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

ሊግ:- ስሁል ሽረን እንዳሰለጠነ ባለሙያ ሶስቱ የትግራይ ክለቦች ወደ ፕሪሚየር ሊጉ እንዲመለሱ መደረጉ ምን ትርጉም ይሰጥሃል….?

ሳምሶን:- ምንም ጥርጥር የለውም ደስ ብሎኛል በክልሉ ያለውን የእግርኳስ ፍቅር ያለውን ህዝባዊ ተቀባይነት ስለማውቅ በመመለሳቸው  ተደሴቻለሁ ትልቅ ውሳኔ ነው  ክለባቸውን ከመውደድ አሸናፊ እንዲሆንላቸው ከመፈለግ አንጻርም ደጋፊዎቹ ትልቅ ፍቅር አላቸው ይህን ታዝቤያለሁ አሁን  በተሀይ ከፋይናንስ  አንጻር  ያሉበት ሁኔታ ላይ ጥያቄ ቢኖረኝም ለፕሪሚየር ሊጉ ከፍታ ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው ነው በመመለሳየውም ክለቦቹን ሆነ ማህበረሰቡን እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ።

ሊግ:-  ተሞዳሟጅ አይደለም  አይበላም አያስበላም ይሉሃል ይሄ ባህሪህ አልጎዳህም…?

ሳምሶን:– በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው ያነሳኧው  አመሰግናለሁ… እግር ኳሳችንን ከጎዳውና ቁልቁል እንዲሄድ ካደረገው አንዱ መስጠት መቀበልና መሞዳሞዱ ይመስለኛል በተለይ ከአሰራር ጋር ተያይዞ ክፍተት አለ…ይሄን ለማድረግ ባህሪና አስተዳደግ ይወስነዋል እኔ ደግሞ እንዲህ አላደኩም ሁሌ ሙግቴ ከህሊናዬ ጋር ነው ገንዘብ የማይፈልግ የለም። አመጣጡ ግን ለሰላምህ ትልቅ ትርጉም አለው። የስራና የነገ ነጻነቴን የሚያሳጣኝ በመሆኑ መቼም አልቀበለውም በነጻነት እንዳልንቀሳቀስ  እስከገደበኝ ድረስ ገንዘቡ ለኔ የጤናዬ ጠንቅ ነው። አመጣጡ ጤነኛ ካልሆነ ሰላም የሚነሳ የሚያውቁብኝ ጓደኞቼን ቤተሰቤን አንገት የሚያስደፋ በመሆኑ አልፈልገውም። እንደ ግለሰብ አፌን እንድዘጋ የሚያደርግ እኔድደበቅ የሚያደርግ በመህኑ አልተቀበልኩትም መቼምም  አልቀበለውም።

ሊግ:– ብዙ ጊዜኮ ቤት ተቀመጥክ..?

ሳምሶን:- አዎ በደንብ መረጃ ይዘሃል … በተለያየ ጊዜ ከስራው እየወጣሁ ቤቴ የምቀመጥበት ጊዜ ብዙ ነው ሰላም ግን ነበረኝ  የላይሰንስና የውጤት  ችግር የልምድ ክፍተት የስነ ምግቤባር ችግር ሳይኖርብኝ እንድገፈተር ይደረጋል። በቅርብ የሚያውቁኝ አንዳንዶች በመጣህበት እውነት ቀጥል አይዞህ ሲሉኝ ሌሎቹ ደግሞ እስከ መቼ እንዲህ ትቀጥላለህ ቤተሰብ አለህ መኖር አለብህ  እንደ ሁኔታው ሁን  ጊዜው ከሚፈልገው ጋር እንድስማማ ወደዛኛው መንገድ  እንዳዘነብል ይመክሩኛል ይህንንም እረዳለሁ አዝነውልኝ ነው።  ሁሐቱ ሀሳቦች  ለኔ ፈተና ነበር…ሰው ይጠቀም ያግኝ  ግን እስከ ሰራ ብቻ ነው አለበለዚያ አልስማማም። የስራ ነጻነቴን የሚያሳጣ ክብሬን የሚነካ ከሆነ በንጽናዬ መጓዝ የሚያስችል አመራር እስኪመጣ ብዬ ቤቴ ተቀመጥኩ እንደ አጠቃላይ ያለው ይሄ ነው። ወጣት ከመቀየር እንደ ሀገር ድጋፍ  ከማድረግ ያገደኝ አሰራር ስላልተመቸኝ ነው ወደፊት ተመሳሳይ ችግሮቹ እየቀነሱ እንደሚመጡ አውቃለሁ እኔን ግን ጎድተውኛል።

ሊግ:- ኢትዮ ኤሌክትሪክ ላይ አሁን ያልነው  ችግር  አልገጠመህም…?

ሳምሶን:- የለም የለም …በዚህም ደስ ብሎኛል  ለተገኘው ድልና ለውጥ  አመራሩ  በቁርጠኝየት  የሰራው ሪፎርም  ትልቅ ሚና ነበረው። የዘመናዊ  የኢትዮጵያ እግርኳስ ፒላሮች ከሚባሉ ክለቦች መሃል አንዱ ኢትዮ ኤሌክተሪክ  ነው። የአደረጃጀትም ህነ የፋያናንስ ችግር የለበትሞ የታሪክ የውጤት መሠረት ችግር አታገኝበትም ነገር ግን ውጤት ከራቀው ቆይቷል  አመራሩ ግን እንቀጥል አንቀጥል ከቀጠልን እንዴት የሚለው ፊፎርም ሰርቶ እንድናልፍ  ትልቅ እገዛ አድርጓል።

ሊግ:- ሃላፊነቱን ከተረከብክ በኋላ ግን ወደ ሊጉ እንደምታድጉ እምነት ነበራችሁ..?

ሳምሶን:-  ሪፎርሙ ከተሰራ በኋላ  በአጭር ጊዜ ቡድኑን ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መመለስ የሚል አቅጣጫ ያዘ… ተከታታይ ስራ በመስራት  ወደነበረበት ትልቅነቱ መመለስም የሪፎርሙ አንዱ አካል ነው ከዚያ አሰልጣኝ ወደ መቅጠር ነው የገቡት… በፕሪሚየር ሊጉም ይሁን ከፍተኛ ሊግ ላይ የሰራ ውጤታማ  የሆነ ውጤታማነቱን በሌሎች ክለቦች ያሳየ ከቡድኑ ጋር በፕሪሚየር ሊጉ አብሮ የሚቆይ ስነምግባር  ያለው የሚል መመዘኛ አስቀመጠ።  እንደ እቅድ ሶስት አመት ይሰጠዋል አንደኛው አመት ቡድኑን ወደ ፕሪሚየር ሊግ ማሳደግ፣ ሁለተኛው አመት በፕሪሚየር ሊጉ ማቆየት ሶስተኛው አመት ደግሞ  ለዋንጫ ከሚፎዠካከሩ ክለብች አንዱ ማድረግ የሚል ነው።  ከነበሩት አሰልጣኝች ጋር ተወዳድሬ አልፌ ነው የተረከብኩት…. ይህን ተከትሎ በምርጫው በማሸየፌ ተደራደርን… በተጨዋች ምልመላ ላይ  በነጻነት እንድሰራ የፈለኩትን መምረጥ የአሰልጣኝ ቡድን አባላትን ማሳወቅ  የዝግጅት ጊዜንና ቦታን ማሳየት  የሚሉት ሁሉ በውሉ ውስጥ ተካትቶ ተስማማን። የተሟላ የተጨዋቾች  ምልመላ አድርጌያለሁ በዚህም ተሳክቶልኝ ወደ ፕሪሚየር አደግን።

ሊግ:– ለስኬታችሁ አይነተኛ ምክንያት ምንድነው..?

ሳምሶን:– ሰፊ ጊዜና በቂ የዝግጅት ጊዜ ነበረን የማች ፊትነሳችንን ለመጠበቅ  የወዳጅነት ጨዋታ አደረግኝ። ቡድን በሚባል ደረጃ አደራጅተን ወደ ውድድር ገባን የስኬታችን  መነሻ  ተከታታይ አምስት ጨዋታ አድርገን 15ት ሙሉ ነጥብ ማግኘታችን ነው። ከውድድሩ ባህሪና ክብደት አንጻር ከአምስት ጨዌታ ሙሉ 15 ነጥብ ማግኘት አልተለመደም ይሄ ትልቅ እመርታ ነበር  በቀጣይ ለምንሰራቸው ስራዎችም ትልቅ ድጋፍ አድርጓል። የኔን ጉልበትና በራስ መተማመን ያመጣ የተጨዋቾችን መንፈስና ጥንካሬ  ታክሎበት ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ማደግ ችለናል።

ሊግ:- ውድድሩ አንድ ቦታ መሆኑ ለማለፋችሁ ትልቅ  ጥቅም አልነበረውም….?

ሳምሶን:-በትክክል እንጂ ….ይሄማ አያጠራጥርም ከዚህ በፊች ሶስት ምድብ ነበር እኛ ስንመጣ ግን በገጠመኝ ምድቡ ሁለት ሆነ በዚህም ተጠቅመናል።  እጣውኮ ሲወጣ ጠንካራ የነበሩ ክለቦች ማለትም እኛን ጨምሮ  እነ ነቀምት፣ እነ ወልዲያ  እነ ቤንጅ ማጂ፣ እነ ሀላባ   እነ ንብን ጨምሮ አንድ ምድብ ውስጥ ነበርን  ያም ሆኖ  ጠንክረን ተጫውተን አልፈናል ከዚያም በላይ  የመጀመሪያወ ዙር ብቃት ይወስነዋል አንደኛ ዙርን በ7 ነጥብ ልዩነት  ጨርሰን  አልፈናል።

ሊግ:- የሀዋሳ ቆይታችሁ ውጤታማ ነበር..?

ሳምሶን:- ሀዋሳ እያለን ትልቅ ውጤት መጥቷል በተጨማሪ  በቡድናቿው ይናደዱ አይናደዱ የሀዋሳ ስፖርት አፍቃሪያን ግን ጥሩ ለተጫወተ የሚደግፉ  የሚከታተሉ  ድጋፍ የሚያደርጉ በመሆናቸው በነሱ ድጋፍም  ተጠቃሚ ነበርን።

ሊግ:- ኢትዮ ኤሌክትሪክን ወደ ፕሪሚየር ሊጉ አሳድገሃል ያም ሆኖ በ2017 የክለቡ አሰልጣኝ ሆነህ እንደምትቀጥል ርግጠኛ ነህ..?

ሳምሶን:- አንድ ፐርሰንት አልጠራጠርም ስጋት የለብኝም ምክንያቱም ሶስት አመት ታቅዶ ሪፎርም ሲሰራ ሳምሶን ታስቦ አይደለም  ለሚመጣው ማንኛውም አሰልጣኝ  ነው ግን በተቀመጠው ሶስት አመት ውስጥ የታሰበውን ይፈጽማል  ወይ የሚለው ነው ዋናው … አንደኛውን ግብ በስኬት ጨርሰናል ሁለት ሶስተኛው ደግሞ በቀጣይ የምናየው ነው… 2010 ወደ ከፍተኛ ሊግ ከወረደ በኋላ ለመመለስ አራት አመት ፈጅቷል 2014  ወደ  ፕሪሚየር ሊጉ ተመልሶ  በአመቱ ነው የወረደው  ዘንድሮ በአንጻራዊነት ከሀሜት የጸዳ የተጨዋቾች ምልመላ አድርጀናል በቂ ዝግጅችት ነበረን። ውድድሩን ከጀመርንበት እስከ አሁን ድረስ እየመራን ነው ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደግነው አምስት ጨዋታ እየቀረን ሪከርድ በሆነ ውጤት ነው። ይህንን ያሳካ አንድም ክለብ የለም ወደኋላ ሄደህ ብታይ ሻሸመኔ ከተማ አራት ጨዋታ እየቀረው አምና ያለፈበት ታሪክ አለ ከየትኛውም መንገድ ውጫዊ እገዛና ድጋፍ ውጪ በአቅሙና በአቅሙ የመጣ ቡድን ነው ያለን…ይህም ወደፊት ብሩህ ጊዜ እንዳለን ያሳያል ስለዚህ የመሰናበት ስጋት የለብኝም በአመራሩ በሰራተኛው ትልቅ ድጋፍ እንዳለኝ አውቃለሁ።

ሊግ:- የአዲስ አበባ ክለቦች ቁጥር ጨምሯል  ከ16ቱ የሊጉ ክለቦች 6ቱ የአዲስ አበባ መሆኑን  እንዴት አየኧው..?

ሳምሶን:- ጥሩ ጥያቄ ነው….ወደኋላ መለስ ስታይ የከተማው ክሐቦች በጥራት በአደረጃጀት ለእግርኳሱ እንደመሪ ይታዩ ነበር። እንደሀገር አዲስ አበባ ድሬዳዋ  ከኤርትራ ክለቦች እየተባለ የመሪነት ሚና እንደነበራቸው  ይነገራል  የሀገሪቱ ዋና ከተማና  ማእከል ነበረች ባለፉት ጥቂት አመታት  ከአመት ወደ አመት ወርደው ወደ ሁለት ደርሰው ማየት ያማል የአቅምም የታሪክ ችግርም  አልነበረም ከእለት እለት ግን ለእግር ኳሱ ሳይሆን የግል ፍላጎታቸውን ለማሟላት  አላስፈላጊ ጣልቃ ጠብነት መጨመሩ በራሱ ትልቅ ችግር  ነበር  እግር ኳሱን እየበሉት እየበሉት ቁጥሩን ቀንሰው ችግር ፈጥረው ነበር…. አሁን እያንሰራራ ቁጥሩ ጨምሯል ይህን መጠበቅ ያስፈልጋል የዘመናዊ እግርኳስ መሠረት ከሚባሉት ቅዱስ ጊዮርጊስ መቻል ኢሌክትሪክ ብለህ ነው። ኢትዮጵያ መድን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮጵያ ቡና እያልክ የምትመጣው… የሀገሪቱን እግርኳስ እንደ ፒላር ከፍ አድርገው ተሸክመው ከሚችሉት ክለቦች ከመሆናቸው አንጻር የአዲስ አበባ ከተማ ክለቦች ቁጥር መጨመር ያስደስታል።

ሊግ:- አርባምንጭ ከተማ እንደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ቱሉ በመጡበት አመት ዳግም ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ተመልሰዋል…የምትላቸው ነገር አለ..?

ሳምሶን:-  የእግርኳስ ጥንካሬ መለኪያዎች ብዙ ናቸው   አርባምንጭ ከተማ  ሲወርድ በጣም አዝነን ነበር በጥቃቅን ምክንያቶች መውረዱ የነበረው ሀዘንን አስታውሳለሁ በርካታ ደጋፊ ያለው በክልል ክለቦቼ ላይ በጎ ተጽዕኖ የነበረው ጥሩ ቡድን በመሆኑ መውረዱ ያሳዝን ነበር አሁን ግን እንደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በአንዴ መመለሱ ጥንካሬውን ያሳየ በመሆኑ የክለቡን አሰልጣኞችና ተጨዋቾች  አመራሮቸና ደጋፊዎች ይገባችኋል። እንኳን ደስ አላችሁ ማለት  እፈልጋለሁ

ሊግ:-  ወደፕሪሚየር ሊጉ ስትመለሱ የነበረው የቤተሰቦችህ ደስታ  ምን ይመስላል..?

ሳምሶን:- በጣም ከባድ ጊዜ ነበር ኢትይ ኤሌክትሪን ወደ ሚመጥነው ሊግ መመለስ ማህበረሰቡን የማስደሰት ትልቁ ሃላፊነት የኔ ነበረና ቤተሰቦቼ ላይ ጫና ነበረው በከፍተኛ ሊግ ከአንድ አንድ ኤሌክትሪክን አሳልፋለሁ ብሎ ሃላፊነቱን መውሰድ ከባድ ነው ጭንቀቱም ደስታውም ተፈራርቋል በመርፌ ቀዳዳ እንደመሹለክ አድርጌ  ነው የምቆጥረው።  ያንን ለማድረግ ትልቅ ትግል ውስጥ ስገባ አብረውኝ ቤተሰቦቼ ጓደኞቼ የቅርብ ሰዎቼን ጭንቀት አልረሳውም።  በመጣው  ድል በተፈጠረላቸው ደስታ ደስ ብሎኛል ለድጋፋችሁም እግዜር ይስጥልኝ ማለት እፈልጋለሁ።

 

ሊግ:-  ከውጪ አሰሕልጣኞች የማን ፍልስፍና ይመችሃል..?

ሳምሶን:- ያለኝን አቅም ለማሳደግ ከምችልባቸው መንገዶች አንዱ ውድድሮችን ማየት ነው። ሴሪ ኤ ፕሪሚየር ሊግ ላሊጋውን ቡንደስሊጋውንም አያለሁ ግን በቀጥታ የክለብና የግል የተጨዋቾች ደጋፊ አይደለሁም። የአስተሳሰብ  ምርኮኛና አድናቂ ግን ነኝ  በዚህም የፔፕ ጋርዲዮላ ፍልስፍናና አስተሳሰብ አድናቂ ነኝ የሱን የተለያዩ ቪዲዮዎችን እመለከታለሁ።

ሊግ:- ከከፍተኛ ሊግና ፕሪሚየር ሊጉ ከፍተኛ  ትግል የሚገጥመው  የትኛው ላይ ነው…?

ሳምሶን:–  በከፍታ ደረጃ ካየነው  ፕሪሚየር ሊጉ የሀገሪቱ ትልቅ የሊግ ውድድር ነው  እንደ ፈተና ግን ካየነው ከፍተኛ ሊጉ ከባድ ነው በተለይ ከእቅድና ከሃላፊነትህ አንጻር ትልቅ ትግል ያለው እዚህ ነው ፕሪሚየር  ሊግ ላይ ለዋንጫ የሚጫወቱት ክለቦች  ላለመውረድ የሚጫወቱት በሚል ከነምክንያቱ ማስቀመጥ ይቻላል  ፕሪሚየር ሊጉ ላይ ሶስት እድል አለ ማሸነፍ አቻ መውጣት ሶስተኛው መሸነፍ የሚለው ግን አይመከርም አይፈለግምም እንደ ተጋጣሚህ   የሚሆን እቅድ ይዘህ  ትገባለህ ፕላን ኤ ባይሳካ ፕላን ቢ ትጠቀማለህ።  ነገር ግን በከፍተኛ  ሊግ አንድ እድል ብቻ ነው ማሸነፍ ሁለተኛ እቅድ አይኖርህም።  የማሸነፍ እቅድ ብቻ ነው የሚኖርህ  በአንድ ጨዋታ እስከ ሶስት እቅድ ይዘህ መምጣት ይጠበቅብሃል  ሌላው እግርኳሱ የወጣቶች ነው። ከፍተኛ ሊጉ በወጣት የተሞላ ነው ለማስቆጠርም እንዳይቆጠር  ለመከላከልም መሮጥ መሮጥ የግድ ይላል ግብህን ለማሳካት ብትነሳም ከእገሌ ሶስት ነጥብ እወስዳለሁ ብለህ አትመጣም የጌም ፕላን ኤ እና ቢ መያዝህ የግድ ነው። ሁሌ ማሸነፍ ብቻ ነው አቻ መውጣት አይፈለግም አይመረጥምም። አንድ ነጥብ ይዘህ ሁለት ነጥብ ጥለህ ሻምፒዮን መሆን ማለፍ አይቻልም በአጠቃላይ ካየን ከባድ ትግል ያለው ከፍተኛ።

ሊጉ ላይ ነው ብዬ አምናለሁ… ይሄን መናገር የሚችሉት ደግሞ ያዩት ብቻ ናቸው ሳታይ አይቻልም..

ሊግ:–  የምታመሰግነው ካለ…?

ሳምሶን:- እውነት ለመናገር እኔ ጋር ያለውን የስራ ዲሲፕሊን እያደገ የሚሄድ አቅምና ፍላጎት  አውቀው እድል ስላጣ ነው እንጂ መለወጥ ይችላል ለሚሉ ወዳጆቼ ምስጋና ማቅረብ  እፈልጋለሁ።  በትልቁ ክለብ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በመሳካቱ እንኳን ደስ አላችሁ ለነበራችሁ መልካም ምኞት አመሰግናለሁ። ለቦርድ አመራሮቹ ለሰጡኝ የስራ እድል ለማበረታታቸው ሁለተኛ ዙር ላይ ቡድኑን ለማጠናከር ለሰጡኝ ድጋፍ ማመስገን እፈልጋለሁ ለኮቺንግ ስታፍ ለተጨዋቾቼ  ለክለቡ ሰራተኞችና አብረውን ለነበሩት ደጋፊዎች ምስጋና አቀርባለሁ እንደዚሁም ለቤተሰቦቼ ለጓደኞቼ እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ። አንተም ሊግም ለሰጣችሁኝ እድል አጠቃላይ ምስጋና አቀርባለሁ።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

P