Google search engine

“በእግር ኳስ ጨዋታ ዘመኔ እንዲህ ያለ የሊግ ፉክክር ተመልክቼም አጋጥሞኝም አያውቅም፤ ቅ/ጊዮርጊሶች ዋንጫውን ቢያነሱት ደስ ይለኛል” “ከእግር ኳሱ የተማርኩት ነገር ቢኖር ቅንና ዲስፕሊን ተጨዋች መሆኔ፣ ራሴን መጠበቄና ሙያውን ማክበሬ ለረጅም ዓመታት በብቃት እንድጫወት አድርጎኛል” ሳላህዲን ሰይድ /ሲዳማ ቡና/

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የዘንድሮ የውድድር ዘመን ሻምፒዮና እውቁ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ሳላህዲን ሰይድ የመጀመሪያው ዙርን በዝውውር መስኮቱ መዘጋት ምክንያት ለመጫወት ባይችልም የሁለተኛው ዙር ላይ ግን ወደ ሲዳማ ቡና በማምራት እየተጫወተ ይገኛል። በክለቡ የእስካሁኑ ቆይታውም 7 የሚደርሱ ጎሎችን በማስቆጠር የኮከብ ግብ አግቢነቱን ከሚመሩት ተጨዋቾች በግማሽ በመበለጥ እየተከተላቸው ይገኛል።
የሲዳማ ቡናው የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች በሁለተኛው ዙር ላይ ብቻ ተጫውቶ ካስቆጠረው ግብ በመነሳትም ብዙዎቹ አድናቆታቸውን እየቸሩት ይገኛል።
የሲዳማ ቡናውን እውቁ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ሳላህዲን ሰይድን የሊግ ስፖርቱ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ ስለ ቡድናቸው፣ ስለ ራሱና በሌሎች ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ አናግሮት ተጨዋቹ የሰጠውን ምላሽ በሚከተለው መልኩ አቅርበንሎታል፤ ተከታተሉት።
ሊግ፦ እስኪ ቅድሚያ ከእዚህ ጥያቄ እንነሳ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉን በሁለተኛው ዙር ነው የተቀላቀልከው፤ የመጀመሪያው ዙርን እንዴት በአንድ ክለብ ውስጥ ሳትጫወት እና ሳናይህ ቀረህ?
ሳላህዲን፦ የአንደኛው ዙር ላይ በወቅቱ በሜዳ ላይ ላታዩኝ የቻላችሁት በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ላይ የተለያዩ ክለቦች ለእኔ ጥሪ አድርገውልኝ ነበር፤ ከእነዛም ቡድኖች መካከል ጅማ አባጅፋር አንዱ ቡድን ነበር። ጅማዎች በጊዜው እኔን ሲያናግሩኝ ከእነ ስማቸው በቂ እና ጥሩ ጥሩ ችሎታ ያላቸውን ተጨዋቾች እንደሚያመጡና በፋይናንሱ ረገድም አቅማቸው ጥሩ እንደሆኑም ነበር የነገሩኝ። ከእኔ ጋር በተያያዘም በጥቅማ ጥቅም ደረጃ ለእኔ በምፈልገው መልኩ የተሻለ ነገር እንደሚያደርጉልኝ ብንስማማም፤ ለክለቡ ለመፈረም ብጠብቅም እኔን ጨምሮ የሚፈልጓቸውን ተጨዋቾች ለማምጣት ጊዜ ስለወሰደባቸው፤ እኔም ለእነሱ ታማኝ ሆኜ እስኪያስፈርሙኝ ብጠብቃቸውም የዝውውሩ መስኮቱ በመዘጋቱ ምክንያት ነው ወደ ሌላ ቡድን ገብቼ ሳልጫወት እና ሳታዩኝ የቀራችሁት።
ሊግ፦ በሁለተኛው ዙር ወደ ሲዳማ ቡና ካመራ በኋላ እስካሁን 7 ግቦችን አስቆጥረሃል፤ ይህን ከተመለከትክ በኋላ ግብ ከማስቆጠሩ ጋር ተያይዞ ምነው የመጀመሪያው ዙር ላይስ በተጫወትኩ አላልክም? አልቆጨህምስ?
ሳላህዲን፦ በእግር ኳስ ጨዋታ ዘመኔ እኔ ብዙም ወደ ኋላ የማይ እና የምመለከት አይነት ተጨዋች አይደለሁም፤ ሁሌም ስኬታማ መሆን የምትችለው የፊት ለፊቱን ስትመለከት ነው። በእርግጥ እንደ ተጨዋች የሚያስቆጭህ ነገር ሊኖር ይችላል። በተቃራኒው ስትመለከት ደግሞ ወይ በጉዳት አለያም በሌላ ነገር ሳይሳካልህ ቀርቶ እና ተጠባባቂም ሆነ ላትጫወት ትችላለህና ያን ያክል እኔ ስለ እንደዚህ አይነት ነገሮች ፈፅሞ አላሰብኩም። ከእዚህ በፊት በቅ/ጊዮርጊስ እያለው ለአንድ ዓመት ያህል በጉዳት ያልተጫወትኩበት እና የተቀመትኩበት ጊዜ ነበር። ያንን ያንን ሳስብ እኔ በቂ ልምምድ እያደረግኩ የነበረበት ጊዜ ነበርና ስላለፉት ጊዜያቶች ሳይሆን ከፊት ከፊት ስላሉብንና በቀጣይነት ውጤታማ ስለምሆንበት ጊዜያቶች ስለማስብ ብዙም የሚያስቆጨኝ ነገር አልነበረም።
ሊግ፦ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የሁለተኛው ዙርን በብቃት ለመቅረብ የመጀመሪያው ዙር ላይ ራስህን በብቃት አዘጋጅተኸው ነበር?
ሳላህዲን፦ አዎ፤ ልምምዴን በጥሩ ሁኔታ ስሰራ ነበር፤ ምክንያቱም ሙያህን ከውስጥህ የምትወደው ከሆነ ሁሌም እዛ ቦታ ላይ ማለትም በጥሩ አቋምህ ላይ ትገኛለህ። እኔ ደግሞ እግር ኳስን በጣም ነው የምወደውና ለስራዬ ክብር ስለምሰጥ ለዛም ነው በጥሩ ብቃት ላይ እንድገኝ ያደረገኝ።
ሊግ፦ የእግር ኳሱን በስኬታማነት የመጫወትህ የተለየ ሚስጥር አለ?
ሳላህዲን፦ ከእግር ኳሱ የተማርኩት ብዙ ነገር አለ፤ ከሁሉም በፊት በማንኛውም ቦታ ላይ ስኬታማ ለመሆንና መጨረሻክም እንዲያምር ከተፈለገ ቅንነት መጀመሪያ ይቀድማል። ቅንነት የሁሉም በር ነውም ብዬ ነው የማስበው። የሁሉም ስኬታማ የምትሆንበት ቁልፉ ነገርም ነው። ከዛ ውጪ ራስን መጠበቅ ነው። ሌላው ሙያህን በደንብ አድርገህ ማክበር እና ዲስፕሊን መሆንም ነው። እነዚህ ሶስቱ በመገናኘታቸውም ነው እስካሁን እየተጫወትኩ ያለሁት።
ሊግ፦ በሙገር ሲሚንቶ የጀመርከው የኳስ ህይወት በቅ/ጊዮርጊስ፣ በብሄራዊ ቡድን ደረጃ እና ወደ ባህርማዶ ክለቦች ማለትም ወደ ግብፅ ሊግ ቀጥሎም አሁን ላይም በሲዳማ ቡና ክለብ ውስጥ እንድትጫወት አድርጎሃል፤ ባሳለፍካቸው አጠቃላይ የኳስ የህይወት ቆይታህ በጣም ደስተኛ ነህ?
ሳላህዲን፦ አዎን እንጂ! እንዴት ደስተኛ አልሁን፤ ምክንያቱም እንደ አንድ የእግር ኳስ ተጨዋች የወደፊት ምኞት እኔ በጨዋታ ዘመኔ የሊጉን ዋንጫ ማግኘት ስለምፈልግ ይህን ድል ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር ለማንሳት ችያለሁ። የሀገሪቱ ኮከብ ግብ አግቢ ተብዬ ተሸልሜያለሁ። ሀገሬን ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዋንጫ ለማሳለፍ እና በውድድሩም ላይ ለመጫወት ችያለሁ። ከዛ ውጪም ወደ ባህርማዶ በመጓዝም በፕሮፌሽናል ተጨዋችነት ኳሱን ለመጫወት ችያለሁ እና ይህን ሁሉ ስመለከት እንዴት ነው ደስተኛ የማልሆነው።
በእግር ኳስ ህይወት ውስጥ በእርግጥ የደስታም የሀዘንም ጊዜ አለ። አንዳንዶቹ ደስተኛ ሲያደርጉ አንዳንዶቹ ደግሞ መራራ ናቸው። የሁለቱንም ስሜት ማለትም የሆይ ሆዩንም የአስቸጋሪውንም ስሜት የምታጣጥመውም ቢበዛ ለአንድ ሳምንት ነውና እኔ ያሳለፍኩት የኳስ ህይወት ግን በአብዛኛው በደስታ የተሞላ ነው።
ሊግ፦ በቅ/ጊዮርጊስ ክለብ የጨዋታ ዘመንህ በአንድ ወቅት ከደጋፊዎች ጋር አለመግባባትን እና ጥልን ፈጥረህ በመበሳጨት እና ራስህንም መቆጣጠር አቅቶህ የክብር ትሪቩኑን መስታወት እስከ መስበርና በግቢው ውስጥም “እኔ ለቅ/ጊዮርጊስ እንዲህ ነኝ?!” እስከ ማለትም በመድረስ ከእነ ደምህ መሬት ላይ ተፈጥፍጠህ በመውደቅ መነጋገሪያ ሆነህ ነበር? እስኪ ወደ ኋላ መለስ በማለት ስለ እዛ ጉዳይ አንድ ነገር ብትል?

ሳላህዲን፦ የእግር ኳስ ሜዳ ውስጥ ገብተህ ስትጫወት አንድ አንዴ ስሜታዊ የሚያደርጉህ ነገሮች አሉ፤ እኔም ከወላይታ ድቻ ጋር በጊዜው በነበረን ጨዋታ ሶስት ነጥብ ያስፈልገን ስለነበር ያን ለማሳካት ብዙ ጥረቶችን እያደረግን ነበር። በእዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ እያለንም ሳለ ከውሳኔ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ከዕለቱ አልቢትር ጋር ለመስማማት ሳልችል ቀረውና በቢጫ ካርድ ከዛም በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ ወጣው። ቡድናችንም የፈለገውን ሳያገኝ በመቅረቱና ጨዋታውም በመጠናቀቁ እኔ በጣም ተናድጄ እና ስሜታዊ በነበርኩበት ሰዓት ላይ ሁለት በጣም የሚቀርቡኝ የቡድናችን ደጋፊዎች ናቸው ከመልበሻ ክፍል እየወጣው በነበርኩበት ሰዓት በንግግር ሲያበሳጩኝ እና ሊመቱኝም ሲሞክሩ ነው ከላይ የጠየቅከኝን ድርጊት ልፈፅም የቻልኩት። ምክንያቱም እኔ በቅ/ጊዮርጊስ ቤት ኳስን ስጫወት ቡድኑን እንደ ክለብ ብቻ አይደለም የምመለከተው፤ በቆይታዬ በጣም ደስተኛ
ለብሰህ ስትጫወት ስሜቱ ከፍተኛ ደስታን ስለሚሰጥህም በተለይ እኔን በጣም ያስደሰተኝ የአባይ ጉዳይ ስላለም እሱን ጨምሮም ነው። የብሄራዊ ቡድን ሲባል የሚታሰበው በኳስ ብቻ አይደለም። የሚገርምህ ነገር የሁለቱ ሀገራት ጨዋታ በገለልተኛ ሜዳ ሲባል እነሱ ሀገር ላይ ምን አስበው እንደሆነ አይታወቅም እንድንጫወት ፈልገው ነበር። ያ ሳይሆን ቀርቶ ማላዊ ላይ በኳስ ብልጫም በውጤትም ስናሸንፋቸው በጣም ነው ደስ ያለኝ እና ይህን ላሳኩት የብሄራዊ ቡድን አባላቶችን ማመስገን እፈልጋለሁ።
ሊግ፦ በመጨረሻ?
ሳላህዲን፦ በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመኔ በክለብም ሆነ በብሄራዊ ቡድን ደረጃ ጥሩ ጊዜያቶችን አሳልፌያለሁ። በጥሩም ሆነ በአስቸጋሪ ወቅቶች ያሳለፍኳቸው ጊዜያቶች ነበሩ። ያኔ ታዲያ ሁሉንም ነገር ተቋቁሜ ኳሱን አሁን ድረስ በጥሩ ሁኔታ እንድጫወት ቤተሰቦቼ ከጎኔ ሆነው ብዙ ነገሮች አድርገውልኛልና በተለይ በጣም የምወዳትን እናቴ ሲቀጥል ባለቤቴንና ሌሎችን ወዳጆቼን ማመስገን እፈልጋለሁ።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this:
P