Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ጥሩ ሜዳ የለም ጥሩ ክለብ ነው ብዬ የምጠራውም የለም” “መጫወት እንጂ የምንፈልገው ፕሮፌሽናሊዝምን የማናውቅ ብዙ ነን” ሽመልስ በቀለ /መቻል/

በዋሊያዎቹ  ግልጋሎት  ላለፉት የ15 አመታት የማይጠፋ ፊት  ነበር፡፡ አሁን ግን ይህን ፊት በብሄራዊ ቡድኑ መሃል ላይ ላናይ በይፋ በቃኝ ብሎ ተሰናብቷል.. በሀገር ውስጥ የሀዋሳ ከተማና ቅዱስ ጊዮርጊስ ከውጪ አራት የግብጽ ክለቦችን ማሊያ የለበሰው እንግዳችን አሁን ደግሞ በመቻል ማሊያ በአሰልጣኝ ገ/ክርስቶስ ቢራራ ስብስብ ውስጥ ተካትቶ እየተጫወተ ይገኛል.. መቻሎች በእስካሁኑ አስር ጨዋታ 7 ጊዜ አሸንፈው 2 ጊዜ አቻ ወጥተው አንዴ ተሸንፈው በ23 ነጥብ  ከመሪው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነጥባቸውን አስተካክለው ለዋንጫው እየተፋለሙ ለመገኘታቸው የእንግዳችን የመሃል ሜዳ ኮከቡ ሽመልስ በቀለና ጓደኞቹ ከፍተኛ ጥረት ወሳኝ ሚና ተጫውቷል በሚል ብዙዎች ይመሰክሩለታል…. ሽመልስ በቀለ ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር በነበረው ቆይታ ለቀረቡለት ጥያቄዎች ድፍረት የተሞላበትን ምላሹን ሰጥቷል።

ሊግ:-  በአዳማ የነበረው የሽኝቱ ፕሮግራም ስሜት ምን ይመስላል..?

ሽመልስ:- የሽኝቱ ፕሮግራም ከጠበኩት በላይ በጣም አሪፍ ነበር… ምክንያቱም ከኔ በላይ የነበሩ በጣም ብዙ የሚሆኑ ሌጀንዶች አሉ… ሳላህዲን ሰይድ፣ አዳነ ግርማ፣ ምንያህል ተሾመ እንዲሁም አዲስ ህንጻን የመሰሉ ኢትዮጵያ ከ31 አመት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ስታልፍ አብረውኝ የነበሩ የቡድን ጓደኞቼ ነበሩ፡፡ በዚያ የሽኝት ፕሮግራም ባልጠበኩት መንገድ ተከናውኖ በጣም ተደስቻለሁ… ወደፊት የሚመጡ ተጨዋቾችም ይህን አይተው ትልቅ መነሳሳት እንደሚፈጠርባቸው ርግጠኛ ነኝ፡፡ ከእኔ በላይ ለሀገራቸው ሰርተው ከእኔ በተሻለ መልኩ አሸኛኘት እንደሚደረግላቸው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ሽኝቱ እንደዚያ ይሆናል ብዬ አልጠበኩም፡፡ በዚህም ደስተኛ ነበርኩ በተሰጠኝ ዋጋና ክብር ያህል ለሀገሬ ሰርቻለሁ ብዬ አልጠበኩም፡፡ ከሰራሁት በላይ ነው የተደረገልኝና በጣም ተደስቻለሁ ለወደፊት ለልጆቼ የምነግረው ታሪክ ነውና በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ በዚህች አጋጣሚ ሽኝቱን ያደረጉትን የፌዴሬሽኑን ፕሬዝዳንትና የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን አመሰግናለሁ፡፡ ዋናው የስፖርት ትጥቅ አምራች ድርጅት ለኔ ሽኝት ይህን ያህል ተጨንቆ ማሊያ ሰርቶ ለደጋፊ እንድሰጥ ስላደረገኝና ለኔ ማስታወሻ እንዲሆን  የፎቶ ሽልማት ስለሰጡኝ ከልብ አመሰግናለሁ እግዜር ይስጥልኝ፡፡ በአጠቃላይ ሽኝቱ ምርጥ የሚባልና መቼም የማልረሳው ቀን ነው ….

ሊግ:– ዞር ብለህ የብሄራዊ ቡድን ቆይታህን እንዴት ትገልጸዋለህ..?

ሽመልስ:– ወደ ኋላ ዞር ብዬ ያሉትን 15 አመታትን ስቃኝ ለኔ ድንቅ ነበር… ብሄራዊ ቡድኑን እንዳገለግል የሚደረግልኝ እያንዳንዱ ጥሪ ለኔ ልዩ ትርጉም ነበረው፡፡ ከመጀመሪያው ቀን ጥሪ ጀምሮ የሚሰማኝ ደስታ እስካሁን መጨረሻ እስከተጠራሁበት እስከ አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሃይሌ ድረስ የነበረው ጥሪ ጋር  ደስታዬ ተመሳሳይ  ነበር፡፡ ሀገርን ማገልገል ክብር ነው፡፡ ባለፉት 15 አመታት ብዙ ነገር ያገኘሁበት ጊዜ ነው ፡፡ ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ሀገሬን አሳልፌያለሁ ብዙ ጥሩ ጓደኞች አግኝቼበታለሁ፡፡ እኔ ጋር የሌለውን የኳስ ክህሎት ከነሱ ተምሬያለሁ፡፡ ከሀገር ወጥቼ እንድጫወት እድሉን ያገኘሁት ለብሄራዊ ቡድን በመጫወቴ ነውና እያንዳንዱ ጊዜዬን እወደዋለሁ፡፡ በርግጥም የሚያስደስትም የሚያሳዝንም ገጠመኞችን አይቻለሁ፡፡ ኢትዮጵያን ከ31 አመት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ያሳለፈው ቡድን አባል በመሆኔ ክብር ይሰማኛል፡፡ በጣም ያዘንኩበት ጊዜ ደግሞ ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ የመጨረሻ ደረጃ ደርሰን በናይጄሪያ ተሸንፈን ሳናሳካ የቀረንበት ጊዜ የሚቆጨኝና የማልረሳው ገጠመኝ ነው፡፡ ከብዙ አሰልጣኞች ጋር ሰርቼ ከነሱ ብዙ ተምሬያለሁ፡፡ ትላልቅ ጨዋታዎች ላይ ተሳትፌ ትላልቅ ተጨዋቾችን አውቄያለሁ፡፡ ደስታ የፈጠሩ ግቦችን አስቆጥሬያለሁ፡፡ እንደ አጠቃላይ ያሳለፍኳቸውን 15 አመታት አሳልፋቸዋለሁ ብዬ አስቤም አላውቅም፡፡ እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁንና ከመጀመሪያው ጀምሮ እስከ መጨረሻው እጅግ ያማረ ነበር፡፡ ሁሌም የማስበውና ውስጤ ደስታን ጭሮ የሚሄድ ነገር  አለውና ደስተኛ ነኝ።

ሊግ:– በግብጽ  የነበረህ ቆይታ እንዴት ነበር …? ፕሮፌሽናሊዝም ከሚለው ሃሳብ ጋር ስንነሳ እኛ ምን ይቀረናል…?

ሽመልስ:- በግብጽ የነበረኝ ቆይታ አስደናቂ የነበረ ነው… ባለፉት 10 አመታት ፕሮፌሽናል ሆኜ ተጫውቻለሁ… በግብጽ ለየት ያለ ጊዜ አሳልፌያለሁ፡፡ አራት ለሚሆኑ የግብጽ ክለቦች ተጫውቻለሁ… በጣም ብዙ ነገር የተማርኩባቸው፣ ያገኘሁባቸውና ያጣሁባቸው ጊዜያቶችን አሳልፌያለሁ….የእግር ኳስ ፕሮፌሽናል ህይወቴ በጣም የሚያስደስትና ህይወቴን የለወጠልኝ ነው ….ፕሮፌሽናሊዝም ከሚለው ሃሳብ ጋር ስንነሳ  ላልከው ገና ነን፡፡ እነሱን ከእኛ ጋር ማወዳደርም አንችልም፡፡ የሀገራችን ሊግ በምን አይነት ሁኔታ ላይ እንዳለ የምታየው ነው፡፡ ወደፊት ይስተካከላል ያድጋል ብዬ አስባለሁ፡፡ አሁን ግን በጣም ብዙ ነገር ይቀረናል፡፡ መጫወት እንጂ የምንፈልገው ፕሮፌሽናሊዝምን የማናውቅ ብዙ ነን ወደፊት ግን የሚስተካከል ይመስለኛል

ሊግ:– ፕሪሚየር ሊጉን እንዴት አገኘኧው…?  ምርጡ ቡድን ማነው…?

ሽመልስ:- ፕሪሚየር ሊጉን  እኔ ከነበርኩበት ጋር ላነጻጽረው አልችልም፡፡  እኔ እያለሁ ሊጉ በጣም ጠንካራ ጥሩ ጨዋታ የምታይበት አሁን ካለው ሁኔታ አንጻር ያኔ ጥሩ ስታዲየም የነበረበት ነው፡፡ አሁን ላይ ላወዳድር አልችልም፡፡ ጥሩ ሜዳም የለም ጥሩ ክለብ ነው ብዬ የምጠራውም የለም፡፡ ምክንያቱም ጥሩ ሜዳ ከሌለ ጥሩ ክለብም አታገኝም፡፡ ለማወዳደር የምጠቅሰውም የለም፡፡ እግርኳስ የሚለየው በነጥብ ነውና ነጥብ ላይ ከፍ ያለ ቡድን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከውጤት ጋር ጥሩ ነው፡፡ የኛው ክለብ መቻልም ጥሩ ነው፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስና ባህርዳር ከተማም ጥሩ ናቸው፡፡ ሌሎቹ ስብሰባቸውን አሪፍ ነው፡፡ ሜዳ ቢኖር ብዙ ክለቦችን ለመምረጥ ይቻል ነበር፡፡  ሜዳ በሌለበት ክለብ መምረጥ አልችልም።

ሊግ:– ከመቻል ጋር  ያለህ ቆይታ ተመቸህ .. ? ምንስ  አቅዳችኋል…?

ሽመልስ:- ከመቻል ጋር ያለኝ ቆይታ ተመችቶኛል፡፡ ጥሩ ጥሩ አቅም ያላቸው ተጨዋቾች ተካተውበት ምርጥ አቋም እያሳየን ነው …. እንደ እቅድ ከሌላው ጊዜ የተሻለ ደረጃ ላይ መገኘትን አቅደን ነው የተነሳነው… እያንዳንዱን ጨዋታ ላይ ትኩረት አድርገን የማሸነፍና  ከ1-3 ያለውን ደረጃ ይዘን የማጠናቀቅ እቅድ ይዘናል እንደሚሳካም ተስፋ አደርጋለሁ….

ሊግ:- ለቲየሪ ኦንሪ  አርሴን ቬንገር ካልን ለሽመልስ በቀለስ ማነው ባለውለታ ..?

ሽመልስ:- ለኔ ባለውለታዎቼ ብዙ ናቸው፡፡ በመጀመሪያው የሚጠሩት ጋሽ ከማል ናቸው፡፡ አዲሴ ካሳም አለበት፡፡ ለቢ ስሰራ ሹሬ አለ፡፡ በብሄራዊ ቡድኑ ደረጃ አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው፡፡ አሰልጣኝ ኦፌም ኦኑራ ሁሉም በኔ የእግርኳስ ህይወት ላይ ትልቅ ስራ ሰርተዋል፡፡ ሁሉም አሰልጣኞች ለኔ ቅርብ ስለሆኑ ለይቼ የማወጣልህ አሰልጣኝ የለም፡፡ እንደ አንድ አድርጌ ነው የምወስዳቸው…

ሊግ:- ከዚህ በኋላ በብቃት እስከ መቼ እጫወታለሁ ብለህ ታስባለህ …?

ሽመልስ:- /ሳቅ በሳቅ/ እሱን አላውቅም …ራሴን የምጠብቅ ከሆነ ጤንነቴን ከጠበኩ ከፈጣሪ ፍቃድ ጋር  የምጫወት ይመስለኛል፡፡ ሁሉን ነገር የሰጠኝ ፈጣሪ ነው። አቅሜ እስከፈቀደ እስከ መጨረሻው  ድረስ እጫወታለሁ ብዬ አምናለሁ፡፡ ከአራት አመት በኋላ ነው የማቆመው ብዬ መናገር አልችልም፡፡ የኳሱ ሂደት አቁም በቃህ ሲል ሲመጣ የግድ አቆማለሁ፡፡ ብቃቴን ይዤ ከቡድን ጓደኞቼ ጋር ሆኜ ጥሩ ነገር እሰራለሁ ብዬ አስባለሁ፡፡ ለጊዜው ግን አላቆምም ለማቆምም አላሰብኩም።

ሊግ:– በሀገር ውስጥ ይሁን በውጪ በቦታህ ምርጡ ማነው..?

ሽመልስ:- በዚህ በኩል ለብራዚላዊው ሮናልዲንሆ ጎቾ ዲ አሲስ ሞሪየራ ቅድሚያ እሰጣለሁ….. አሁን ካሉት ደግሞ ሉካ ሞድሪች ኬቨን ደብሮይነ ጥሩ ናቸው ብዬ አስባለሁ።

ሊግ:_ የመጨረሻ ጥያቄ ይሁንና የምታመሰግነው..?

ሽመልስ:- የቅድሚያ ምስጋናውን እግዚአብሄር ይወስዳል .. ከዚያ በመቀጠል ቤተሰቦቼ… በኔ ውስጥ የገጠመኝን ደስታም ሆነ ሀዘን አብረውኝ ስለተካፈሉ እዚህ ደረጃ እንድደርስም ትልቁን አስተዋጽኦ ስላበረከቱ እነሱን በጣም ማመስገን እፈልጋለሁ… የልጅነት ጓደኛዬ አሁን ደግሞ ሚስቴና የልጆቼ እናት የሆነችው እናትን በጣም አመሰግናለሁ፡፡ በኔ ህይወት ውስጥ ትልቅ አሻራ አላትና ማርሲላስ አየለን በጣም አመሰግናለሁ፡፡ በጣም ነው የምወዳት የማከብራት በጥሩም በመጥፎም ጊዜ ከጎኔ ስለሆነችም አመሰግናታለሁ… በእስካሁኑ የተጨዋችነት ህይወቴ ለነበሩ አሰልጣኞች ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ፡፡ ከፍተኛ አክብሮትና ፍቅር ላሳዩኝ የስፖርት ቤተሰቡ፣ የሀዋሳ ከተማና የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለቦች አመራሮችና ደጋፊዎች እንዲሁም መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ አመሰግናለሁ። በክለብም ሆነ በብሄራዊ ቡድን ደረጃ አብረውኝ ለተጫወቱ ተጨዋቾች የነሱም ትልቅ እገዛ ጠቅሞኛልና ለነበረን ጊዜ ማመስገን እፈልጋለሁ። ባለፉት 15 አመታት በፌዴሬሽን ደረጃ ለነበሩ ፕሬዝዳንቶችና ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት አሁን ያሉት አቶ ኢሳያስ ጅራ ዶክተር ዳኛቸው አቶ ባህሩን ጨምሮ ላሉት የፌዴሬሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች ላሳዩኝ ፍቅርና አክብሮትን እግዜር ይስጥልኝ ለነሱ ያለኝን ክብርና ምስጋና መግለጽ እወዳለሁ፡፡ በነበርኩበት የ15 አመት የብሄራዊ ቡድን ግልጋሎቴ  ሲያበረታቱኝ ለነበሩ የስፖርት ጋዜጠኞችም ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ አመሰግናለሁ።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

P