Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ኳሷን ከእግራችን የሚነጥቁን ተከላካዮች ብቻ ሳይሆኑ ሜዳው ጭምር ነው” “አንድ ሃያል ቡድን በብዙ ነጥብ እየራቀ ሻምፒዮን የሚሆንበት ጊዜ ያበቃ ይመስለኛል” ሱራፌል ዳኛቸው /ፋሲል ከነማ/

የቅጣት ምት ስፔሻሊስት፣ ጣጣቸውን የጨረሱ ኳሶችን ለአጥቂ የሚያቀብል፣ ለተጋጣሚ ስጋት የሆኑ እግሮች ባለቤት፣ የምርጥ ድሪብል የማራኪ ጎል ባለቤት….ማነው ቢባሉ ለመልሱ ይቸገራሉ ተብሎ አይጠበቅም…

ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት በፕሮፌሽናል እድል  ለመጫወት ወደ አሜሪካ  ጉዞ ለመጀመር ከተዘጋጀው ከሱራፌል ዳኛቸው ውጪ የለምና ሲሉ ብዙዎች ይመሰክራሉ….መርቲ ጀጁ የምትታወቀው በመርቲ ምርቷ ነው ..ይቺ ስፍራ ግን ሱራፌል ዳኛቸውን አፍርታለች …ወደ አሜሪካ ተጉዞ ለዲሲ ዩናይትድ መጋቢ ቡድን  ሎንደን ዩናይትድ ለመጫወት በቀናቶች ወደ ዋሽንግተን የሚያቀናው ሱራፌል በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የሆነውን ቃለምልልስ ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር አድርጓል።

ሊግ:-የፋሲል ከነማ ለሱራፌል ምን ትርጉም አለው..?

ሱራፌል:– ፋሲል ከነማ ለኔ እንደ ቤተሰብ ሁሉ ነገሬ የምለው ብዙ ነገር  ያየሁበት ክለቤ ነው  ህይወቴን ያስተካከልኩበት ክፉ ደጉን ያየሁበት ቤቴ ነው ለፋሲል ትልቅ ፍቅርና ክብር አለኝ፡፡

ሊግ:- የፋሲል ከነማ ደጋፊዎችስ ..?

ሱራፌል:- አሁን ለደረስኩበት ትልቁ ምስጢር የክለቤ ደጋፊዎች ናቸው ማለት እችላለሁ…ከፈጣሪና ከቤተሰቤ ቀጥሎ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች በድካሜም በብርታቴም ከግኔ ሆነው አብረውኝ 6  አመት ውስጥ በውጣ ውረዴ ያልጠፉ ናቸው ከጎኔ ሆነው እንድሰራ እያበረታቱ እየደገፉ ለዚህ አብቅተውኛል ብል አላጋነንኩም…በዚህ አጋጣሚ ከልቤ አመሰግናቸዋለሁ…

ሊግ:- የፋሲል ከነማ የ6 አመት  ቆይታህን እንዴት ትገመግመዋለህ..?

ሱራፌል:- በስኬታማነትና በመልካም ጎኑ ነው የማየው ባለፉት 6 አመታቶቼን መለስ ብዬ ስመለከት  ብዙ መልካም የደስታ ጊዜያትን አሳልፌያለሁ  ከፋሲል ከነማ ጋር ኢትዮጵያ  ውስጥ ሁሉንም ዋንጫ አንስቻለሁ   2011 ኮከብ ተብያለሁ ሀገሬን ወክያለሁ አሪፍ አሪፍ ጊዜያቶችን በማሳለፍ አሁን ድረስ የደረስኩበት ምርጡ ክለቤ ነው በፋሲል ማሊያ ደስታ አጣጥሜያለሁ፡፡

ሊግ:- ለቲየሪ ኦነሪ ቬንገርን ከጠራን ለሱራፌል ዳኛቸውስ..?

ሱራፌል:-  /ሳቅ በሳቅ/ በመጀመሪያ በመርቲ ጀጁ መነሻዬ አሰልጣኝ ሱልጣን መሀመድ ምንም ሳይኖረው በጣም ተንከባክቦኛል አሰልጣኝ ሃይሉ ካሱ ከዚያ አሰልጣኝ ፈቀደ ትጋን መጥራት እችላለሁ አዳማ ያለው ኤፍሬም ከዚያ ከቢ ቡድኑ ያሳደገኝ አሸናፊ በቀለ፣ ስዩም ከበደ፣ ውበቱ አባተ፣ አብርሃም መብራቱ የኔ አርሴን ቬንገር ናቸው /ሳቅ በሳቅ/ ባለውለታዎቼ ናቸውና ሁሉንም አመሰግናለሁ፡፡

ሊግ:- የአበበ ቢቂላ ስታዲየም በደጋፊው የሞቀ ሽኝት ምን ተሰማህ…የቡናም ደጋፊ በደንብ ሸኝቶሃል አይደል…?

ሱራፌል:- ከሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በፊት ነው የሸኙኝ…ምርጥ ሽኝት ድባቡ ደስ የሚል ነበር ስሜቴ ተነክቷል ሰርተህ በክብር በፍቅር ከክለብህ ጋር ስትለያይ ደስ ይላል…ለሁሉም ተጨዋች ሽኝት እንዲህ እንዲሆን ብዬ ተመኘሁ ሽኝቱን ያዘጋጁትን አመሰግናለሁ  እግዚአብሄር ይስጥልኝ ሰው እንኳን ከክለብ ጋር ሁለት ሰው ጋር አብሮ መኖር በከበደበት ዘመን በፍቅር በመለያየቴ ለኔ  ይሄ መታደል ነው  ምን ያህል ቤተሰባዊ እንደነበርን ነው ያሳየኝ  በተቃራኒው የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ከወንበራቸው ተነስተው አጨብጭበው ዘምረው ነው የሸኙኝ እግዜር ይስጥልኝ እንዳከበሩኝ ኪዳነምህረት ታክብራቸው  ተቃራኒ ቡድን ደጋፊ ቢሆኑም ለሰራ ሀገሩን ላገለገለ ክብር እንደሚሰጡ አሳይተውኛል ለነሱ ትልቅ ክብር አለኝ ከወንበሬ ተነስቼ ዝቅ ብዬ እጅ እነሳለሁ እግዚአብሄር ይስጥልኝ እላለሁ  አጠቃላይ ደጋፊዎቹን የነበሩትን የስፖርት ቤተሰብ ለተሰጠኝ ክብር ማመስገን እፈልጋለሁ

ሊግ:-  የልጅነት  ተምሳሌት አለህ..?

ሱራፌል:- የመጀመሪያ ሀ ብዬ የጀመርኩባት ተወልጄ ያደኩባት በጣም ጠባብ ካምፕ ናት መርቲ ጀጁ… በድልህ በመርቲ ጣሳዋ ነው፡፡ የሚያውቃት … እግርኳስን ሀ ብዬ የጀመርኩባትም ናት ከጓደኞቼ  በባዶ እግሬ ስጫወት ያደኩባት የከረምኩባት ትውልድ ቦታዬ መርቲ ጀጁ ናት ሁሌም ትናፍቀኛለች በዚህች ስፍራ ደግሞ  እዲ አበራ እንዳለ መለዮ/ የበዛብህ መለዮ ወንድም/  ሲጫወቱ እያየሁ ነው ያደኩትና እነሱ  ተምሳሌት ሆነውኛል፡፡

ሊግ:- እግር ኳስን ከመውደድህ የተነሳ ለሊት ለሊት ትጫወት ነበር አሉኝ… እውነት ነው..?

ሱራፌል:- አዎ../ሳቅ/ መርቲ እያለሁ እውነት ነው… አሸዋ ተራ የሚባል ሜዳ አለ…በዚህ ሜዳ ስጫወት ነው ለእይታ ያበቃኝ ..ለብቻዬ እሰራ ነበር እንደ ገጠመኝ ሆኖ እነ እጊና እንዳለ ለሊት ወጥተው ልምምድ  ይሰሩ ነበር.. አንድ ቀን እይታ ውስጥ እንደምገባ ተስፋ ነበረኝ  ወጥቼ ስሰራ የነበረበት ጥንካሬዬ ለዚህ አድርሶኛል…

ሊግ:- ግንኮ ጠንካራ ልምምድ አትወዱም ተብሎ ትታማላችሁ…ሱራፌልስ በጠንካራ ልምምድ ያምናል..?

ሱራፌል:-  አዎ አምናለሁ …የፈለገ ተሰጥኦ ይኑርህ  ጠንከረህ የተሻለ ልምምድ ካልሰራህ የፈለከውን ሜዳው ላይ መተግበር አትችልም…ጠንካራ ልምምድ ስትሰራ ነው ጌሙ የሚቀልህ ሁሉም በዚህም ማመን አለበት አሁን አሁን ግን ለውጥ አለው ተጨዋቾችን ጂም ውስጥ ማግኘት የተለመደ ሆኗል  ተጨማሪ ልምምድ እየተሰራ ነው አለም ላይ የሚሰራበት ነው እኛም ጋር ለውጥ አለ ክህሎት ብቻ ምንም ለውጥ እንደማያመጣ የተረዳን ይመስለኛል…. ፊትነስ ለእግርኳሱ ምን ያህል እንደሚያስፈልግ እያወቅነው መጥተናል

ሊግ:-  የቅጽል ስምህ ነብሮ ነው …ለምን ተባልክ..?

ሱራፌል:- የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ናቸው ያወጡልኝ… 2011 የተነሳሁት አንድ ፎቶ ላይ ነው ነብሮ ተብሎ የተለጠፈው …ነብር ደግሞ ደስ ይላል…እንደ ቅጽል ስም ተመችቶኛል….

ሊግ:-. እግርኳስ ተጨዋች ባትሆን ምን ሙያ ላይ ትገኝ ነበር..?

ሱራፌል:- የባጃጅ ሹፌር/ ሳቅ/ በወቅቱ ቤተሰቤ ባጃጅ እንድነዳ ይፈልግ ነበር  ቤተሰብ ስር ሆነህ እምቢ ማለት ይከብዳል ግን እኔ በጭራሽ አይሆንም የምፈልገው ኳስ ተጨዋች መሆን ብዬ ነው  አመጽኩ… እነሱም ግን ሰሙኝ  በተለይ እናቴ ፍላጎቴን ታከብራለችና ለዚህ መድረሴ ትልቁ ስራ የርሷ ነው፡፡ ኳሱ ካልተሳካ ባጃጁን ትነዳለህ ብላ ፈቀደችልኝ ስሜቴን ስለተቀበለች ይኧው ለዚህ በቅቻለሁ በዚህ አጋጣሚ አመሰግናታለሁ

ሊግ:- ለዚህም የእናትህ ፍቃድ ኮከቡን ሱሬ አይተናልና እኛም  አመስግነናል

ሱራፌል:- ተቀብያለሁ  የሷ ድጋፍም ትልቅ ነው ይገባታል/ሳቅ/

ሊግ:- መጫወት ፈልገህ  ያልተጫወትከው  ከማን ጋር ነው..?

ሱራፌል:- ኢትዮጵያ ውስጥ በቦታዬ በጣም የምወዳቸው ዳዊት እስጢፋኖስና ሽመልስ በቀለን ነው በጣም ነው የምወዳቸው ከሽመልስ  ጋር  በብሄራዊ ቡድን አብሮ የመጫወትና አብረንም ለአፍሪካ ዋንጫ የመጫወት እድሉን አግኝተናል በዚህም ደስተኛ ነኝ ዳዊት እስጢፋኖስ ጋር ግን እድሉን አላገኘሁም የሀገር ውስጥ ሞዴሌ ዳዊት እስጢፋኖስ ነው በኮቪዱ ጊዜ ለብሄራዊ ቡድን ተጠርተን ልምምድ ሰርተናል ግን አብረን አልተጫወትንም እግዜርም አልፈቀደም ግን ዳዊትን ሲጫወት እያየሁ አድጌያለሁ እወደዋለሁ

ሊግ:- በፕሪሚየር ሊጊ ጠንካራ ቡድን  ገጥሞሃል..?

ሱራፌል:- የአዳማ ሜዳ  አለመመቸት ጠንካራና ደካማ በቡድንን እንዳንለይ አድርጎናል ሜዳው ተመችቶን ብንጫወት የቡድኖቹን ደካማና ጠንካራ ጎን እለይ ነበር አሁን ግን አልቻልንም ሜዳው ከተጋጣሚ ቡድን ተጨዋቾች ጋር አብሮ ኳስ እየነጠቀን ነው የተጋጣሚ ተጨዋች ኳስ ሊነጥቅህ ሲመጣ ሜዳውም ለመነጠቅ ያመቻልና ተቸግረን ነው የተጫወትነውና ሀሀ ጠንካራ ቡድን ማውጣት ከብዶኛል….በተመቻቸ ሜዳ ላይ ተጫውቶ ቅሬታ ማቅረብ አይሆንም ይሄ ሜዳ ግን ሳይመቸን እየነጠቀን ተጫውተን ጠንካራ ቡድን እንዴት ይለይ ..?  ኳሷን ከእግራችን የሚነጥቁን ተከላካዮች ብቻ ሳይሆኑ ሜዳው ጭምር ነው

ሊግ:- ፕሪሚየር ሊጉስ ጠንካራ ፉክክር አለው ማለት ይቻላል..?

ሱራፌል:– አዎ ጠንከር ብሏል…ሻሸመኔ ከተማና አምበሪቾ ዱራሜ ውጤት ስላጡ ደኪማ ይመስላሉ  እንጂ በጣም ተፎካካሪ ናቸው  ውጤት መጥፋቱ ካልሆነ በቀር ከባድ ናቸው…ለኔ ሊጋችን ወደ ጥንካሬው እየመጣ ይመስለኛል። ነጥቦቹ ተቀራራቢ መሆናቸው በራሱ ፉክክሩን ያሳያል… ውድድር ደግሞ አብሮ በመሄድ ነው ያምራል  አንድ ሃያል ቡድን በብዙ ነጥብ እየራቀ ሻምፒዮን የሚሆንበት ጊዜ ያበቃ ይመስለኛል….

ሊግ:- አርሰናልና ሊዮኔል ሜሲ  ይመቹሃል …የሞትለው አለ..?

ሱራፌል:- /ሳቅ/  የአርሰናል ደጋፊ ነኝ ….በጣም እወዳቸዋለሁ…. ለመደገፌ ምክንያ፣ቴ ደግሞ ሴሴክ ፋብሪጋዝ ነው በጣም ነው የማደንቀው የምወደው …..

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

P