Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“አስክሬኔ ላይ ሳይሆን በህይወት እያለሁ አበባ አንገቴ ላይ በመጠለቁ ተደስቻለሁ” “ኢትዮጵያ ቡና ማለት ይሰሀቅ ይስሀቅ ማለት ኢትዮጵያ ቡና ነው” ይስሃቅ ሽፈራው /ፊዚዮቴራፒስት/

እርስዎ ቤትዎ ገብተው ስንት ሰዓት ላይ ይተኛሉ..? እንግዳችን ግን  ባለፉት 38 አመታት  ከ3.30 እስከ 4.00 ሰአት ባለው ወደ አልጋው ያቀናል …. “ወደስራ ለመሄድ ለሊት 8.15  ላይ ከእንቅልፌ እነሳና ከለሊቱ 9 ሰአት ላይ ወደ ስራ ቦታ እጓዛለሁ “ይለናል…. ይቀጥላል “በየቀኑ ስራ ከመግባቴ በፊት ቤ/ክ እሄዳለሁ  ገብርኤል ከሆነ አጠገቤ አለ ..ልደታ ከሆነች ልደታ ቤ/”ክ ኪዳነምህረት ከሆነች እንጦጦ እጓዝና  ወደስራ እገባለሁ  ቤ/ክ ሳልሳለም ስራ ስገባ ቀኑን ሙሉ ሲቀፈኝ እውላለሁ የማክመው ሰውም የሚሞትብኝ ወይም የሚጎዳብኝ ይመስለኛል፡፡ ቤ/ክ ሄጄ መሳለሜ ራሱ ሃይሌ ነው” ሲልም ይናገራል …. ርግጠኛ ነኝ በእንግዳችን ማንነት ግራ እንደማትገቡ …ከ38 አመት በላይ በሰጠው አገልግሎት የእግርኳሱ ማህበረሰብ በአንድነት ያለውን ሰጥቶ ከሀገር ውስጥና ውጪ ተረባርቦ 5 ሚሊዮን ብር የምታወጣ መኪና ሸልሞታል…ፊዚዮቴራፒስቱ ይስሃቅ ሽፈራው … በሆሊዴይ ሆቴል የተካሄደው የምስጋና ፕሮግራም የፈጠረው ስሜት ገና አልበረደም  የሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ  በዚህ የምስጋና ፕሮግራም  የፈጠረው የደስታ ስሜት ሳይበርድ ጨርቆስ ቤ/ክ አካባቢ ወደሚገኘው የፊዚዮቴራፒስቱ ይስሃቅ ሽፈራው የህክምና ስፍራ በመጓዝ የሚከተለውን ቃለምልልስ አድርጓል ተከታተሉት….መልካም ንባብ፡፡

ሊግ:– ይሴ በቅድሚያ እንኳን ደስ አለህ ማለት እፈልጋለሁ…የሆሊዴዩን የምስጋና ፕሮግራም ጠብቀኧው ነበር…?

ይስሀቅ:- በሃሳቤም በውኔም የማልጠብቀው  ክስተት ነበር በጣም ተደስቻለሁ  አምላኬን አመሰግናለሁ ይሄ የእሱ እንጂ የሰው አይደለም እሱ ሲያግዝ ወርዶ አይደለም ሰው ነው የሚልከው….ኮሚቴዎቹን ለዚህ ነው ያዘጋጃቸው ብዬ አምኛለሁ… በአጠቃላይ ደንግጫለሁም ተደስቻለሁም …. ደግሞ  ይሄን ክብር ያገኘሁት የተወደድኩት በምሰራው ስራ ነው፡፡ ቢደክመኝ እንኳን በእንብርክኬ እሰራለሁ እንድል አድርጎኛል ትልቅ ጉልበት ፈጥሮልኛል  ኢነርጂ  አገኘሁ  ማለት እችላለሁ

ሊግ:- አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ይስሃቅ “ሰው ነው” አሉ … በእሳቸው አገላለጽ ተስማምተሃል..?

ይስሀቅ:– ስለራሴ መናገር አልፈልግም… ሰው ይናገር እንጂ… አሰልጣኝ ሰውነት ሲናገር ተደስቻለሁ  እንደዚህ ነኝ ወይ ብዬ እንድጠይቅ አድርጎኛል እንደውም ለምን ከዚህ በላይ አልሆንም ብዬ እንድነሳሳ ኘው ያደረገኝ  አሰልጣኝ  ሰውነት ለሰጠኝ ክብር አመሰግናለሁ፡፡

ሊግ:– በነጋታው ስራ እንደገባህ ሰማሁ ያን ቀን ብታርፍስ ምን ችግር ነበረው..?

ይስሀቅ:– በእውነት በመግባቴ ራሱ ደስ ይለኛል  አመት በአል በሆነ ሰአት ስራ ከሌለኝ ቤተክርስቲያን ሄጄ እሳለማለሁ ከዚያ ነው ወደ ቤት የምሄደው  በእለቱሞ ዝግጅቱን ከፈጰምን በኋላ በተለመደው የስራ ሰአቴ ተገኝቻለሁ ፕሮግራሙ የተሰጠኝ ክብር ራሱ ቻርጅ አድርጎኛል ኢነርጂ ሰጥቶኛል ሰውን በይበልጥ እንድረዳ እንዳግዝ  አድርጎኛል  በዚህም ደስተኛ ነኝ፡፡

ሊግ:– ታካሚዎችህ ስራ ስትገባ ምን አሉህ…?

ይስሀቅ:- ስራ በመግባቴ ተገርመዋል እንደውም የተለመደው መግባዬ 9 ከሩብ አካባቢ ነው ያን ቀን ግን ለዘጠኝ ሩብ ጉዳይ ስራዬ ቦታ ደርሻለሁ  ኢነርጂ ሆኖኝ በጊዜ  አምጥቶኛል ትገባለህ ብለን አልጠበቅንም እዚያ እንዳመሸህ ስለምናውቅ አልጠበቅንም  ብለውኛል.. ታካሚዎቹ በጣም ተደስተናል ሲያንስ እንጂ አይበዛብህም ብንካተትና የአቅማችንን ብናደርግ ደስ ይለን ነበር ብለውኛል አባባሉ ትልቅ ሞራል ሆኖኛል አዘጋጆቹ  የሰሩት መልካም ስራ ያስመሰግናል  የተረሱ መልካም የሰሩ ሰዎችን አስታውሰው ይህን በማድረጋቸው  ክብር ይገባቸዋል ብለውኛል…በአጠቃላይ የማይረሳ ክስተት በመሆኑ ደስ ይላል፡፡

ሊግ:– የቤተሰብ ደስታስ እንዴት ይገለጻል..?

ይስሀቅ:– ቤተሰቦቼ አጠቃላይ  ተደስተዋል ያልተደሰተ የለም ታካሚዎቼም ተደስተዋል ከኔ በላይ የተደሰቱም  አሉ ዝግጅቱ ላይ ከፊት ለፊቴ ሳያቸው ደንግጫለሁ የሚያለቅሱ ነበሩ.. ከውስጣቸው የፈነቀላቸው ነበሩ አንዱ በማግስቱ እኔ ጋር መጥቶ ምነው ስለው በቃ አላውቅም ስሜቴን ፈነቀለኝ መቆጣጠር አልቻልኩም መናገር ፈልጌ አንዴት ልናገር  በማለት ነግሮኛል በቃ ያለው ስሜት የሚገርም ነበር  ቤተሰቤም ከምለው በላይ ተደስቷል…በህይወት ኖሬ መሸለሜ መከበሬ ለቤተሰብ ደስታም ኩራትም ነው  በጣሞ ደስተኛ ናቸው ለዚህም ዋጋና ክብር  እግዚአብሄርን  አመሰግናለሁ

ሊግ:- መኪናዋን ለመድካት ..?

ይስሀቅ:-,/ሳቅ/ አዎ  በነገራችን ላይ በታሪኬ አውቶማቲክ የተባለ መኪና ነድቼ አላውቅም ነበር  መኪናዋ ስትሰጠኝ  እንዴት ነበር የምነዳው ብዬ አሳብ ይዞኝ ነበር በማግስቱ መኪናዋ ያለችበት ስፍራ ድረስ ሄጄ አየኋት ነዳኋት ከማኑዋሉ በጣም የቀለለ የምትመች  የምትነዳ ሁሉ አይመስልም ነበር  አንዴ ቁልፍ ያጠፋሁ መስሎኝ ወረድኩ ድምጽ የለውም ሞተሩ ግን ይሰራል በሩን ሎክ ሳደርግ እንቢ አለኝ አንድ ሰው መጥቶ ሞተሩ አልጠፋ ይሆን ብሎኝ ገብቼ ሳየሁ ፕሬስ የሚደረገውን ሳላደርግ ነው የወረድኩት እሱን ሄጄ አስተካከልኩ..

መኪናዋ ትመቻለች  አሁን ለምጃታለሁ /ሳቅ/..

ሊግ:– መኪናው ውስስጥ ስትገባ ሰርግህንን አላስታወሰህም …?

ይስሀቅ:– /ሳቅ በሳቅ/ እኔኮ ሌላ አለም ውስጥ ነበርኩ በውኔም በሃሳቤም  አልጠበኩትም  ለዚህ ነገር አበቃለሁ ብዬ አላሰብኩም መኪና ውስጥ ስገባ እንባ ተናንቆኛል ካባ ለብሼ ነበር ራሱን የቻለ ድምቀት ፈጥሯል የሰርጉን ስሜት ያመጣል ደስታው ግን የተለየ ስሜት ነው ያለው.. ኮሚቴዎቹ  ሚዜ ይመስሉ ነበር …/ሳቅ/ እዚህ ያሉት ኮሚቴዎች አድምቀውኛል ይደመቁልኝ ደጋግመው…  ውጪ ያሉት ደግሞ የሚገርሙ ናቸው  ቀን ሰርቼ ቤት እገባና አርፋለሁ ባለፉት 3 ወራት ግን እነሱ እንደዚያ አልነበሩም ቀን ሰርተው ማታ ለውይይት ቀጥታ ፕሮግራም ላይ ገብተው ሲያወሩ አይደክሙም ብዬ እሳቀቅ  ነበር ሶስት ወር ሙሉ ያለእረፍት ሲታገሉ የነበሩ ወዳጆቼ ናቸው በጣም አመሰግናለሁ ለነሱ እንዲህ የሚቆም ሰው ይስጣቸው ነው የምለው…

ሊግ:– ጌታነህና ሳላህዲን የሰጡህን ማስታወሻ  አይረሳም አይደል..?

ይስሀቅ:- ሳላህዲን ሰይድና ጌታነህ ከበደ  ስጦታ አበርክተውልኛል ሰው ከልቡ ስለሚሰጥ የስጦታ ትንሽ የለውም ውስጣዊ ስሜታቸው አስገድዷቸው ያደረጉትን ነገር በክብር ነው የተቀበልኩት ስጦታ አላበላልጥም .. ቆየት ቢልም አሁንም አመሰግናቸዋለሁ.. . ደግሜ የምናገረው ግን ያስደነገጠኝ ሳልጠብቀው የሆነልኝ  ይሄ ፕሮግራም መቼም ከአዕምሮዬ የማይጠፋ ክብር ነው የተሰጠኝና አዘጋጆቹን ደጋግሜ አመሰግናቸዋለሁ… ይሄ ደግሞ ያስታወሰኝን ልናገር …ከዚህ በፊት ለሀገራቸው ትልቅ ስራ ሰርተው ደክመው የተረሱ አሉ ምንም ነገር ሳያገኙ ዋጋና ክብር ሳይሰጣቸው ያለፉ የማቃቸው ብዙ ሰዎች አሉ…የአስፕሪን መድሀኒት መግዢያ አጥተው ተሰቃይተው የሞቱ አሉ ይህን ክብር መጎናጸፍ  የነበራባቸው እንዲሁ ሳይታሰቡ የሞቱትን እንዳስብ አድርጎኛል ምነው በኖሩ ብዬ አሰብኩ ይህን ክብር ሳገኝ እነሱን እያስታወስኩ ነበር ይሄን ነገር መለመድ አለበት በቁሜ ይህን ማየቴ ያስደስታል አሰልጣኝ ሰውነት እንዳለው አስክሬኔ ላይ ሳይሆን በህይወት እያለሁ አበባ አንገቴ ላይ በመጠለቁ ተደስቻለሁ ትልቅ ትርጉም  አለው የሰራሁት ሲወሳ ሲሞገስ ሲከበር እያየሁ መሆኔ ለስራዬ ለቀጣይ ዘመኔ ትልቅ ደስታ የፈጠረልኝ  ሆኗል።

ሊግ:– የህብረተሰቡ ደስታና አቀባበልን እንዴት አገኘኧው ..?

ይስሀቅ:- ይሄ ስጦታና ክብር የኔ ብቻ አይደለም የስፖርት አፍቃሪው የስፖርት ቤተሰቡ በእለቱ ፕሮግራም የክብር እንግዳ ሆነው የመጡትን ጭምር የሚያጠቃልል ስጦታ ነው የተሰጠኝ .. ስፖርተኛውና የስፖርት ቤተሰቡ ድጋፍ ባያደርግልኝ እኔ ለዚህ ክብር ባልበቃው ነበር፡፡ ለኔ የሰጡኝ ከበሬታ እኔን ያበረታታኛል ለስራዬ በጎ ጎን ይሆናል የስራ ምስክሬ ስፖርተኛው በመሆኑ ደስተኛ ነኝ ስራዬን እንድወደው በክብር እንድሰራ ያደረጉኝ ስፖርተኞች የሰጡኝ ክብር ነው በዚህም ደስተኛ ነኝ፡፡ አጠቃላይ የስፖርት ቤተሰቡ ለሰጡኝ ክብር አመሰግናለሁ፡፡

ሊግ:-  እንኳን ደስ አለህ ከሚለው ልብህን የነካው የማን የደሰስታ አገላለጽ ነው..?

ይስሀቅ:- በጣም በርካታዎች እንኳን ደስ አለህ የሚል የስልክና የቴክስት መልዕክት አድርሰውኛል ሶስት ቀን ሙሉ ከውጪ ከሀገርም  ስልኬ ይህን ሲየስተናግድ ነበር  ከሁሉ ደግሞ አንዲት እናት አንድ አበባ ይዘው መጥተው ሸሚዜ ውስጥ ከትተው እንኳን ለዚህ አበቃህ እንደ አቅሜ ያለኝ ስጦታ ይሄ ነው  አምላኬን ከአንተ በላይ ነው ያመሰገንኩት ያሉትን አልረሳውም በጣም ምስኪን እናት ናቸው፡፡  በርሳቸው ልቤ ተነክቷል…

ሊግ:– ሁሉም ሰው  እንዴት በይስሃቅ ተመሳሳይ አንድ አይነት አቋም ይኖረዋል..በሁሉም መወደድህን እንዴት ትገልጸዋለህ..?

ይስሀቅ:– ይሄ እግዚአብሄር የሰጠኝ ስጦታ ነው ብዬ ነው የማስበው  አንዳንዱ ደክሞ ሰርቶ ለፍቶ  የማይመሰገኑ አሉ..እኔ ሰርቼ በመመስገኔና በመወደዴ ደስተኛ ነኝ እኔ የምሰጠው ህክምናና ድጋፍ ህዝቡን አንድ ያደረገና ያስማማ በመሆኑ ፈጣሪዬን አመሰግናለሁ…በስራዬ ማንንም አልለይም  ሁሉም እኩል ነው   ታሞ የመጣ ሰው ካለ ቁርሴና ምሳዬን ሳልበላ የእራት ሰአቴ ይደርሳል እንጂ ሳልጨርስ አልሄድም ውሃ ብቻ ነው ቀኑን ሙሉ የምጠጣው ..ስራዬን በጣም አከብራለሁ በዚህ ደስ ይለኛል ቀጥሬው ያልመጣ ሰው ካለ ለምን ቀረ ብዬ ጉዳቱን  ነግሬ እሱ እንደታመመ  ሳይሆን እኔን እንዳመመኝ አድርጌ ነው የምሰራው ..አቅም የሌላቸው የማግዛቸው አሉ  ከክፍለ ሀገር መጥተው አቅም ሳይኖራቸው ሆቴል ይዤላቸው በሙያዬ የምረዳቸው አሉ  ይሄም አምላኬ ለኔ ያደረገልኝ ስለሆነ ነው… እናም ደግሜ አመሰግናለሁ አልሰለችም  ስለሁሉ አምላኬ ይመስገን፡፡

ሊግ:– ይስሃቅ የሚለው ስም በስፖርት ቤተሰቡ ልብ ውስጥ እንዴት ገባ..?

ይስሀቅ:– ጥሩ ጥያቄ ነው …ለዚህ ሁሉ መታወቅ ያበቃኝ ኢትዮጵያ ቡና ነው  ኢትዮጵያ ቡና ማለት ይሰሀቅ ይስሀቅ ማለት ኢትዮጵያ ቡና ነው የኢትዮጵያ ቡና አመራሮች ለኔ የሚሰጡኝ ክብርና እገዛ እምነት የተለየ ትርጉም አለው ስራዬ እንዲያድግ በደንብ አክብሬው እንደሰራ ያደረጉኝን  የቡና ማህበረሰብን አመሰግናለሁ  አመራሮቹን ደጋፊዎቹን  አመሰግናለሁ  ሜዳ ስገባ አንድ አይነት ድጋፍ የሚሰጡኝ የሁሉሞ ክለቦች ደጋፊዎችንም አመሰግናለሁ በሁሉም ደስተኛ ነኝ ለነሱም ትልቅ ክብር አለኝ።

ሊግ:– በጣም ተጎድቶ የመራመድ ስጋት ውስጥ ኖሮ ያዳንከው  ስታየው የምትደሰትበት ሰው አለ..?

ይስሀቅ:- ብዙ ናቸው… ከሁሉ ግን …በአስቸኳይ ይተኛ  ከዚህ ወር በኋላ መራመድ አይችልም እግሩ ይበላሻል የተባሉ እኔ ጋር መጥተው በእግዚአብሄር ሃይል የተፈወሱ አሉ… ከፍተኛ ብር ተጠይቀው  በትንሽ ብር እኔ  ጋር  የዳኑ አሉ…በዚህ ደስተኛ ነኝ ….በነገራችን ላይ እኔ ጋር ሊታከሙ  ክፍያ የምጠይቀው እንደ ህብረተሰቡ ሁኔታ ነው  በክፍያ  ተለያይተን  ሳይታከሙ የተመለሱ የሉም፡፡ አንድ እንጀራ  እስካገኘሁ ድረስ ለሁለት ለሶስት ብዬ   መሯሯጥ አልወድም የህብረተሰቡ አቅምን አያለሁ ትልቅም ትኩረት እሰጣለሁ…. እግዚአብሄርም ይህን ሁሉ ያደረገው  ከእነዚህ ሁሉ የአንዱ ጸሎት ተሰምቶልኝ ይሆናል ብዬ አምናለሁ..ለዚህ ክብር ያበቃኝ ያ ይመስለኛል… ያኔ በፕሮግራሙ ማግስት ወደስራ ቦታ ስሄድ..ወደ ሰባት የሚጠጉ ችግረኞችን ረድቻለሁ ያን ክብርና ስጦታ እነሱ እንዳደረጉልኝ ነው የምቆጥረው፡፡

ሊግ:– ባለፉት 38 አመታት ይሄ ስራ ላይ ነበርክ ..ድንገት አቁም ብትባል ትችላለህ..?

ይስሀቅ:- ከ38 አመት በላይ  ሰርቻለሁ… የምስጋናው ፕሮግራም ትልቅ ቻርጅ አድርጎልኛል….ቻርጅ ያደረገኝ ነገር  እስከሚያልቅ የማገለግል ነው የሚመስለኝ  እስከ መቼ ካልከኝ አቅሜ እስከፈቀደ ድረስ ..በጋሪ ላይም ሆኜ መስራት እችላለሁ…ችግር ቢደርስብኝም መስራቴ አይቀርም  ህይወቴ  እስካለ ድረስ ይህን ህብረተሰብና የስፖርቱ ቤተሰብን ባገለግል ደስ ይለኛል  ፕሮግራሙ በድጋሚ ቃል እንዳስገባኝ ነው የማምነው.. ስራዬን አወደዋለሁ ሱስ ሆኖብኛል…ስራውን ከጠላሁ ግን ገና ሳስበው ይደብረኛል…ይሄ ደግሞ አይሆንብኝም… ስራዬን አክብሬ ስለምሰራና ስለምወደው ለመስራት ከፍተኛ ተነሳሽየት ስላለኝ ሁልጊዜ  በሰአቱ እነሳለሁ …

ሊግ:– ባለፉት 38 አመታት አርፍደህ አታውቅም..?

ይስሃቅ:- በፍጹም…አንዳንድ ሰው ለመነሳት አላርም ይጠቀማል… የኔ ሰውነት ግን አላርም ሆኗል። በፈለኩት ሰአት ነው የምነሳው… ለሊት 8 ሰዓት ካልኩ 8 ሰአት ላይ እነሳለሁ.. አበቃ፡፡

ሊግ:- ጨረስኩ  የምታመሰግነው  ካለ ዕድሉን  ልስጥህ..?

ይስሃቅ:- በዋናነት አምላኬን ፈጣራዬን አመሰግናለሁ… ከዚያም ውድ ቤተሰቦቼን፣ መላው የኢትዮጵያ ህዝብን፣  የኢትዮጵያ ቡና  ቤተሰብ ደጋፊውን ቡድኑን ቦርዱን / መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ፣  አቶ ይስማሸዋ  ከዚህ በፊት የነበሩ እነ አቶ ወርቁ፣  እነ አብዱራዛቅ፣  አሁን ያሉትንም በፊት የነበሩትንም ደጋፊ ማህበር አመራሮች/  በአጠቃላይ  የማውቃቸውን በሙሉ አመሰግናለሁ ስራዬ እንዲያድግና   እንዲጠነክር ያደረጉኝ እነሱ ናቸው  ለስራዬ  ሃላፊነቱን የሰጡኝ  እነሱ ናቸው ፊት የሚነሳኝ የለም ሁሉም አክብረው ነው የሚያገኙኝ እኔም አከብራቸዋለሁ  እነሱን በጣም አመሰግናለሁ ከኢትዮጵያ ቡና ውጪ ያለውን የስፖርት ቤተሰብ አመሰግናለሁ የሁሉም ኮለቦች ደጋፊዎችን ከልብ አመሰግናለሁ፡፡

ሚዲያውን አመሰግናለሁ ብዙ ጋዜጠኞች  ኢንተርቪው ሲጠይቁኝ አልፈቅድም ምክንያቱም  የንግግር ሰው ባለመሆኔ ነው  በጣም ሊከፉ ይችላሉና  ይቅርታ እጠይቃለሁ  ቅር ይላቸዋል ብዬ ስጋት ሲያድርብኝ በተቃራኒው ፍቅራቸውን መውደዳቸውንና መልካም አስተያየታቸውን  ነፍገውኝ አያውቁምና  ከልብ አመሰግናለሁ  ሚዲያ ጠይቆኝ እሺ ማለት ህብረተሰቡን ማክበር ነው  ግን  ፍቃደኛ የማልሆነው ካለኝ የጊዜ እጥረት የተነሳ ነውና ደግሜ  ይቅርታ እጠይቃለሁ…ይኧው እግዚአብሄር  በጊዜው ሲያደርግ  ሲያሳውቀኝ ለመገናኘት በቅተናልና ሙሉ ሚዲያ አመሰግናለሁ እወዳችኋለሁ… አሁን ሙሉ ክብር ለሰጡኝ እኔን በሀገር ውስጥና ውጪ ሆነው  ላከበሩኝ የኮሚቴው አባላትና አስተባባሪዎች ፈጣሪ ያክብርልኝ ክብር  ያልብስልኝ ማለት እፈልጋለሁ …

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

P