Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“የፈጠረውን ጌታ አይሆንም ብሎ የሰቀለ ሰው ባለበት ምድር ላይ ኖሬ ሁሉም ይወደኛል ማለት ይከብዳል” “ከታች ካሉት መራቅ ከላይ ካሉት መቅረብ ዋናው ዕቅዳችን ነው” አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው /ሞውሪንሆ/ /ሲዳማ ቡና/

ሲዳማ ቡና ከተከታታይ ደካማ አቋሙ የተመለሰ ይመስላል …የክለቡ አመራሮች አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው /ሞውሪንሆ/ ካስፈረሙ  በኋላ ክለቡ በተከታታይ እያሸነፈ ነው በተለይ ባህርዳር ከተማን የመሰለ ጠንካራ ክለብ ማሸነፉ ትኩረት ስቧል…በ12ኛ ሳምንት መርሃግብር  ዛሬ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ከአምበሪቾ ዱራሜ ጋር  ጨዋታ ያለባቸው አሰልጣኙ ይህን ትልቅ ክለባችንን ወዳስፈሪነቱ ይመልሱት ይሆን የሚል ጉጉት በደጋፊው ልብ ውስጥ አስጭረዋል። አሰልጣኝ ዘላለም  ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር በነበራቸው ቆይታ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሚከተላቸውን ምላሽ ሰጥተዋል…

ሊግ:- ወደ አሰልጣኝነቱ ስትመለስ ለውስጥህ ምን

ነገርከው..?

ዘላለም/ ሞውሪንሆ/:- ለውስጤ የነገርኩት ሲዳማ ቡና በርካታ ደጋፊ ያለው ተወዳጅ ክለብ ነው። ይህን ክለብ አሁን ካለበት አውጥቼ ወደነበረበት ከፍታ እንደውም በተሻለ መንገድ ጠንካራ ተፎካካሪና ወደ አስፈሪነቱ እመልሰዋለሁ ብዬ ነው  የነገርኩት እንደሚሳካም ተስፋ አደርጋለሁ ክለቡን ከያዝኩ ደምሮ ሶስት ጨዋታ ያደረኩ ሲሆን ሁለት አሸንፌ አንድ አቻ ተለያይቻለሁ። ማግኘት ካለብኝም 9 ነጥብ 7ቱን አሳክቻለሁ። 3 ግብ አስቆጥረን  ምንም አልተቆጠረብንም ለኔ ጥሩ አጀማመር ነው..

ሊግ:- የሲዳማ ቡና ውጤት መጥፋት  ምክንያቱ ምን ነበር ..?

ዘላለም/ ሞውሪንሆ/:- ቡድኑ የስብስብ ችግር የለበትም ትልቁ ችግር  የነበረው ሁለት ጉዳይ ላይ ነበር። የመጀመሪያው የፊትነስ ሁለተኛው የቡድን መንፈሱ  ጠንካራ አልነበረም ገብቼም ያረጋገጥኩት ይህን ነው በሁለቱ ላይ ጠንክረን እየሰራን ነው።

ሊግ:- ባህርዳርን አሸነፋችሁ … ሲዳማ ቡናን ወደጥንካሬው እየመለስኩ  ነው ማለት ትችላለህ…?

ዘላለም/ ሞውሪንሆ/:- ገና ነው በሶስቱ ጨዋታዎች ውጤት ድምዳሜ ላይ መድረስ ይከብዳል ብዙ ርቀት መጓዝ አለብን። ብዙ መስራት ይጠበቅብናል አሁን ወደ ጥንካሬው እየተመለስን ነው አልልም ግን ሙሉ ለሙሉ ለመንደርደር እየተነሳን እንዳለ አድርጌ ነው የምቆጥረው

ሊግ:-  ያገኘኧው እረፍት  ምን ትምህርት ሰጠህ..?

ዘላለም/ ሞውሪንሆ/:- ለኔ ወቅቱን የማየው የጽሞና ጊዜ አድርጌ ነው…በዚህን የጽሞና ጊዜ ወደ ኋላ ተመልሼ ራሴን በደንብ እንዳይ አድርጎኛል ድክመቴነ ጥንካሬዬን ገምግሜ በየትኛው መቀጠል የትኛውን ማስወገድ እንዳለብኝ  ምን አይነት አካሄድ መሄድ አለብኝ የሚሉትን ነገሮች በደንብ አይቼበታለሁ ከበቂ በላይ ራሴን የማየት  ዕድል ፈጥሮልኛል በዚህም ደስተኛ ነኝ።

ሊግ:- ከቤተሰብ ጋርም ከረጅም  ጊዜ በኋላ እድል ያገኘህበት ይመስልሃል ..?

ዘላለም/ ሞውሪንሆ/:- ዋው ምርጡ ጊዜዬ ነው በስራችን ባህሪ ከልጆቼ ጋር ተራርቄ ነበር ብዙም አንገናኝም አመቱን ሙሉ እንራራቅ ነበር በዚህ በእረፍቱ ጊዜ ቤተሰቦቼን ቀን በቀን ስለማገኛቸው ደስተኞች ነበሩ ከፍተኛ መላመድ ውሰጥ ገብተን አሁን ስራው ሲመጣ ሌላው ከባድ ፈተና የሆነውም  መራራቁን ማመንና ማሳመኑ ነበር  ወደ ስራው ስመለስ የተወሰነ መደበት ገጥሞኝ ነበርና  ቆይታዬ ጥሩ ቢሆንም መለያየቱ ደግሞ ፈተና ነበር።

ሊግ:- ፕሪሚየር ሊጉን እንዴት  ገመገምከው ….? ባንተ ዕይታ ጠንካራ ነው ቀላል…?

ዘላለም/ ሞውሪንሆ/:- አማራጩ ብዙ ከመሆኑም የተነሳ ፕሪሚየር ሊጉ አንድም ጨዋታ አላመለጠኝም  የየክለቦቹ  ጥንካሬ የተጨዋቾች የግል አቋም ምንድነው የሚለውን  የማየት ዕድል አግኝቻለሁ..እንደሌላው ጊዜ ይሄ ክለብ ጠንካራ ያኛው ደግሞ ደካማ ማለት አይቻልም ሁሉም ክለቦች ጠንካራ ተፎካካሪ ናቸው ጠንክረው መጥተዋል ይህን በደንብ አይቻለሁ።

ሊግ:- አሰልጣኞች እንደሚባረሩ ሲገመት ተተኪ ለመሆን አሰፍስፈው የሚጠብቁ አሉ ይባላል ይሄን ታዝበሃል..?

ዘላለም/ ሞውሪንሆ/:- ለውጦች እንደሚኖሩ እጠብቃለሁ.. ይሄኮ በመላው አለም  ያለ እውነት ነው አዲሰ ነገር  አይደለም  የትኛውም ሊግ ላይ ይከሰታል ዛሬ አንድ አሰልጣኝ ሲፈርም ነገ እንደሚለቅ እያሰበ ነው የሚፈርመው…በፍላጎት መልቀቅ ..ቃል የገባውን ባለመፈጸም ተሰናብተህ እንዲያውም የሚፈልጉትን አሳክተህ መልቀቅም አለ ይሄ አዲስ ነገር አይደለም…

ሊግ:- የኛ ሀገር የክለብ ሃላፊዎችኮ ለማሰናበት ይቸኩላሉ  ጊዜ አይሰጡም ይባላል..ይህን አልታዘብክም..?

ዘላለም/ ሞውሪንሆ/:- ጫና ውስጥ የሚከቱ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። ዋናው ግን አሰልጣኙ አሳካለሁ ብሎ ያስቀመጠው ግብና ዕቅድ ምንድነው የሚለው ነው..? ለዋንጫ፣ ላለመውረድ፣ ተፎካካሪ ማድረግ፣ አሊያም አጋማሽ ላይ እጨርሳለሁ ብሎ እቅድ ያወጣል… ነገር ግን ሰባት ወይም ከዚያ በላይ ጨዋታዎች ላይ የተመዘገበው ውጤት አሰልጣኙ ግቡን እንደማያሳካ ካሳመነ ክለቦች አሰልጣኙን ሊያሰናብቱ ይችላሉ… ባለሙያው ሊያኮርፍ አይገባም እቅዱን ካላሳካና ክለቦች ሌላ አሰልጣኝ ቢያዩ መቀየም የለበትም ባይ ነኝ

ሊግ:- አንተ  በእስካሁኑ የአሰልጣኝነት ቆይታህ ስትሰናበት አልተከፋህም..? አላዘንክም ….?

ዘላለም /ሞውሪንሆ/:- በእስካሁኑ የአሰልጣኝነቴ ህይወቴ የተሰናበትኩበት ክለብ የለም ማለት ይቻላል ….ከሁለት አመት በፊት በነበርኩበት ክለብ የነበረው ሁኔታ ነው ጥሩ ነገር ያልነበረው …በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ አጠቃላይ የስፖርት ቤተሰቡ የሚያውቀው ነው… የተጨዋቾች ደመወዝ ያልተከፈለበት ሂደት ነበረው

ሊግ:- ሰበታ ከተማ ነው አይደል ..?

ዘላለም ሞውሪንሆ:- እና የነበረው ችግሩ ምን ነበር የሚለው ስለሚታወቅ ጥሩ  ባልሆነ ሁኔታ የወጣሁት ከዚያ ነው። ሌሎቹ ያሰለጠንኩባቸው ክለቦች  አመራሮች መሃል ውጣ ብሎ ያስወጣኝ የለም…..

ሊግ:- ደጋፊውን እንዴት አገኘህ..?

ዘላለም/ ሞውሪንሆ/:- ደጋፊውማ የማውቃቸው የሚያውቁኝ ናቸው አንድ አካባቢም አይደለን ..? ከዚህ ቀደምም የማውቀው  ለሲዳማ ቡና ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ ነው  ከሌላ ክለብ ደጋፊ የተለዩ ለክለባቸው ዋጋ የሚከፍሉ ናቸው። እንዲደግፉን አብረውን ለሚወዱት ክለብ ድል በጋራ እንድንሰራ እጠይቃለሁ

ሊግ:- ሁሉም በደስታ ተቀበሉኝ ማለት ትችላለህ..?

ዘላለም /ሞውሪንሆ/:-  እውነት ለመናገር አቀባበላቸው ሁለት አይነት ነው… እምነት ኖሮት እንደማስተካከል የሚያምኑ አሉ። ጥቂት የማይባሉ ደጋፊዎች  ደግሞ እምነትአልጣሉብኝም…  ተጨዋች ከውድድር ሲርቅና አሰልጣኝ ሲርቅ አንድ አይደለም አለም ላይም ተመሳሳይ ነው እኛ ሀገር ግን እንደተጨዋች አሰልጣኝ ሲርቅ ከአሰልጣኝነት ስለራቀ ውጤታማ አይሆንም ብለው የሚያስቡ አሉ ይሄ  ልክ አይደለም ይሄን የተሳሳተ አስተሳሰብ የሚቀበሉ ደግሞ ቅሬታ ይኖራቸዋል በዚህም ሁሉም ሰው  ሊወደኝ አይችልም ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ  ክርስቶስ የፈጠረውን ጌታ አይሆንም  ብሎ የሰቀለ ሰው ባለበት  ምድር ላይ ኖሬ ሁሉም ይወደኛል ማለት ይከብዳል።

ሊግ:- በውሳኔህ ተጸጽተህ ይህን ባላደርግ ጥሩ ነበር  የምትለው ነገር አለ..?

ዘላለም /ሞውሪንሆ/:- በአሰልጣኝነት  ህይወቴ ለምን ይሄን አደረኩ ባላደርግ ጥሩ ነበር ብዬ የተጸጸትኩበት ነገር የለም ነገር ግን  እግርኳሱ ላይ አንዳንዴ አይተህ እንዳላየ ሰምተህ እንዳልሰማ የምትሆንባቸው ጉዳዮች ይኖራሉ ባላንስ  ማድረግ ላይ ትንሽ ይቀረኛል የሚል አስተሳሰብ አለኝ  በጽሞና ጊዜዬ ራሴን አየሁ የምልበት አንዱ ጉዳይ ይሄ ነው….

ሊግ:- ቀጣይ እቅድ… ምን አሰባችሁ..?

ዘላለም /ሞውሪንሆ/:- እግዚአብሄር ይመስገን አሀን ትንሽ ከፍ ብለናል… ይዘን የጀመርነውን ጥንካሬ ማስቀጠል ይጠበቅብናል በዋናነት ከታች ካሉት መራቅ ከላይ ካሉት  መቅረብ ዋናው ዕቅዳችን ነው…ሁለተኛው ዙር ላይ ደግሞ  መስተካከል ያለባቸው ሲስተካከሉ ደግሞ ምን አይነት አቅም ይኖረናል የምንመጣበት ቁመና ምን ይመስላል የሚለውን የምናይ ይሆናል …

ሊግ:-  ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ የአመቱ የፊፋ ኮከብ ተባለ ምን ትላለህ…?

ዘላለም /ሞውሪንሆ/:- በእኛ ሁኔታ ሜሲ ኮከብነቱ ይገባዋል አይገባውም የሚለው ላይ ብዙ መናገር አልደፍርም… በምርጫው እንደ ግለሰብ ለኧርሊንግ ሃላንድ ቅድሚያ እሰጣለሁ ነገር ግን ምርጫውን ያደረጉት በሂደቱ የተሻሉ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች በመሆናቸው  በድምጽ ምርጫ ስለሆነ ውሳኔውን ከመቀበል ውጪ ምን አማራጭ አለ..?

ሊግ:- መራጮቹ ባለሙያዎች የተሻለ ልምድ ስላላቸው አይሳሳቱም ማለት ይቻላል..?

ዘላለም /ሞውሪንሆ/:-/ሳቅ/ ሁሌ ትክክል ናቸው ማለትማ አይቻልም ግን የምንቃወምበት ሂደቱ ብዙም ስለማይመስጠኝ ነው።

ሊግ:- የመጨረሻ የምታመሰግነው-ሰው ካለ..?

ዘላለም /ሞውሪንሆ/:- በሲዳማ ቡና ሃላፊነት አምነው ለሰጡኝ የክለቡ የቦርድ አመራሮችን አመሰግናለሁ… ተጨዋቾቹን ረዳቶቼንም ከልብ አመሰግናለሁ…ደጋፊው አሁንም አይናችን ነው ከጎናችን እንዲሆን ጥሪ አደርጋለሁ።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

P