Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ኢትዮጵያ ቡናን ለማሸነፍና ክለባችንን ከፍ ለማድረግ ተዘጋጅተናል” አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ /ቅዱስ ጊዮርጊስ/

 

ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ…. የአገሪቱ ትልቁ ደርቢ ይሉታል፡፡ ፈረሰኞቹ ከቡናማዎቹ ጋር የሚያደርጉትን ፍልሚያ….. እንደ አዲስ አበባ ከተማ ክለብነታቸው የከተማው እግር ኳስ አፍቃሪ ይህን ደርቢ ለማየት አልታደለም… በአቡበከር ናስር ሀትሪክ የታገዘው ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን 3ለ2 ከረታበት የ2013 የደርቢ ጨዋታ በኋላ  ባለፉት… የተካሄደው የሁለቱ ፍልሚያ በክልል ከተሞች በመካሄዱ “ስደተኛው ደርቢ” የሚል ቅጽል አግኝቷል። ሁለቱ ክለቦች በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ከ1991 ዓ.ም ጀምሮ 45 ጊዜ እርስ በርስ ተፋልመዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ 22 ጊዜ በማሸነፍ የበላይነቱን ይዟል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና 8 ጊዜ ሲረታ 15 ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል። በ45ቱ ጨዋታ 89 ኳሶች ሲቆጠሩ ቅዱስ ጊዮርጊስ 61 ጎሎችን ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ 28 ጎሎችን ከመረብ አሳርፈዋል…. ዛሬ 9 ሰዓት ላይ ለ46ኛ ጊዜ የሚደረገውን ጨዋታ ኢንተርናሽናል አርቢትር ቴዎድሮስ ምትኩ በመሃል ዳኝነት ይመራዋል ተብሎ ይጠበቃል። ይህን 46ኛ ፍልሚያ ማን ያሸንፋል በሚል የሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ የቅዱስ ጊዮርጊሱ አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታና የኢትትዮጵያ ቡናውን አምበል በረከት አማረን አነጋግሯቸዋል…..

——–/////////———-

 

ሊግ:- እረፍቱና ዝግጅቱ ምን ይመስላል..?

ዘሪሁን:– በእኛ በኩል እረፍት አልነበረም፡፡ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ከሀዋሳ ከተማና ከሻሸመኔ ከተማ  ጋር  አድርገን አሸንፈን ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈን ለቅዳሜው የደርቢ ጨዋታ ራሳችንን አዘጋጅተናል… ከውድድር ወደ ውድድር ነበር የገባነው.. በደርቢ ጨዋታው ጥሩ ውጤት ይገጥመናል ብዬ አምናለሁ።

ሊግ:-  የፕሪሚየር ሊጉና የጥሎ ማለፉ ዋንጫን ለማሸነፍ ቆርጣችሁ ተነስታችኋል….?

ዘሪሁን:- በእኛ በኩል በሁሉም ውድድር ዝግጁ ሆነን ለመገኘት ጠንክረን እየሰራን ነው፡፡ ስራና ስራ ላይ ብቻ አተኩረናል… የቅዱስ ጊዮርጊስን ውጤታማነት ለማስቀጠል ደረጃውን ከፍ ለማድረግ እየሰራን ነው  ከዚህ በላይ ለመገኘት እየሰራን ነው።

ሊግ:- ሰባቱን ጨዋታ ስናይ 5 ድል 1 አቻና 1 ሽንፈት ነው የገጠማችሁ… እንዴት አየኸው..?

ዘሪሁን:- በጣም ጥሩ እንደነበሩ ነው የምናሰበው፡፡ አልተከፋንም በማራኪ እንቅስቃሴ በተደጋጋሚ ወደ ጎል እንደርሳለን ይሄም ተመችቶኛል.. ውጤታማነቱን ለማስቀጠልም እየሰራን ነው… በሰባቱም ጨዋታዎች ተጨዋቾቼን ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡ በተሸነፍንበት የባህር ዳር ከተማ ጨዋታ ሲጀመር  ጥሩ ነበርን፡፡ ተጨዋች በቀይ ካርድ ወጥቶብን የተወሰኑ ጊዜያቶች በጎዶሎ በድን ነው የተፋለምነው… በዚህ ጨዋታ ላይ ተጨዋቾቼ ከ90 ደቂቃ በላይ መጫወት እንደምንችል ስላሳዩኝ አመሰግናለሁ… ትልቅ ኩራት ተሰምቶኛል፡፡

ሊግ:- በወጡ ተጨዋቾች አልተጎዳችሁም..?

ዘሪሁን:- አልተጎዳንም… የትኛውም ተጨዋች ከክለባችን አይበልጥም፡፡ ለሰጡት ግልጋሎት ግን እናመሰግናለን… ማንም ወጣ ማንም የቅ/ጊዮርጊስን ባህል ማስቀጠል የሚችሉ ተጨዋቾች አሉን እንደ ቡድንም  ጠንካራ  ለመሆን እንሰራለን … ከዚያ ውጤቱ በተሻለ አቅምና ፍጥነት የሚመጣ ይሆናል… የአሸናፊነት ባህላችንም ቀጥሏል፡፡ ቀድመው የገቡትም ተቀይረው የሚገቡትም ጥሩ ናቸው፡፡ በዚህም ደስተኛ ነኝ፡፡

ሊግ:- ከዚህ በላይ የተሻለውን ቅዱስ ጊዮርጊስ የማሳየት አቅሙ አላችሁ..?

ዘሪሁን:- አዎ… ሰባት የፕሪሚየር ሊግና ሁለት የጥሎ ማለፍ ጨዋታን ተጫውተናል… ቅዱስ ጊዮርጊስ ምን አይነት አቅም እንዳለው ምን ማድረግ እንደሚችል አሳይተናል፡፡ በጥሩ እንቅስቃሴ ውጤት እየተመዘገበ ነው፡፡ በጥሎ ማለፉ ሻሸመኔ ከተማን 5ለ2 የመጨረሻ የሊጉን ጨዋታ ሀዋሳን 3ለ0 ረተናል፡፡ ይሄም ቡድኔ ያለውን አቅም ያሳያል፡፡ በቀጣይ ከዚህ የተሻለውን ለማድረግ እንጥራለን ምንም አይነት ክፍተት የማይሰጥ የተሻለውን ቅዱስ ጊዮርጊስን በቀጣይ ለማሳየት እንጥራለን፡፡

ሊግ:- አቤል ያለው ሀዋሳ ከተማ ላይ የሰራውን ሃትሪክ እንዴት አገኘኸው …?

ዘሪሁን:- ብዙ የሚጥር የሚለፋ ታጋይ ተጨዋች ነው፡፡ ከዚህ በላይ ክለባችንን የሚጠቅም እንደሚሆን  አምናለሁ… በሱ እምነቱ አለኝ ሃትሪኩ ብቃቱን ያሳየበት ነው… ወደ  ቅዱስ ጊዮርጊስ ያመጣሁትም እኔ ነኝ ከሱ ብዙ እጠብቃለሁ።

ሊግ:- ተፎካካሪዎዩ ብዙ ናቸው ማለት ይቻላል..?

ዘሪሁን:- ንግድ ባንክን ጨምሮ ተፎካካሪ ጥሩ ቡድኖችም አሉ…. ሊጉ ገና ተጀመረ እንጂ ግማሽም አልሞላም፡፡ ስለዚህ አሁን ላይ ሆኖ ስለዋንጫ መናገር አይቻልምና ብዙም መናገር አልሻም፡፡ 19ኙም ግን ለኛ ጠንካራ ተፋላሚ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ጠንካራ ተፎካካሪ ነው፡፡  ጥሩ ስብስብ ይዟል.. ከቅዱስ ጊዮርጊስና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውጪ ባህርዳር ከተማ፣ መቻልና  ፋሲል ከነማ ጥሩ ናቸው፡፡  በዚህ ሰአት ግን ዋንጫውን እገሌ ይወስደዋል ማለት አይቻልም፡፡ ሁሉም በጥሩ ሁኔታ ፉክክር እንደሚያደርግ አምናለሁ፡፡ በቀጣዮቹ 22 ጨዋታዎች ጥሩ ፉክክር እንደሚኖር መጠበቅ ይቻላል።

ሊግ:- ከ16ም ክለቦች ብቸኛው ያልተሸነፈ ክለብ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው… ይሄስ የተሻሉ መሆናቸውን አያሳይም….?

ዘሪሀን:- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እስካሁን አልተሸነፈም ማለት ነገም አይሸነፍም ማለት አይደለም፡፡   ውድድሩ ገና 22 ጨዋታ ይቀረዋልኮ እውነት ነው ጠንካራ ቡድን ነው ያላቸው… በቀጣዮቹ ጨዋታዎች የሚመዘገቡት ውጤቶች ግን ወሳኞች ናቸው፡፡  ጠንካራ ፉክክርም ይታይበታል ብዬ አስባለሁ።

ሊግ:- ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ላላችሁ የደርቢ ትንቅንቅ  ተዘጋጅታችኋል…?

ዘሪሁን:- ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ላለው ጨዋታ እየተዘጋጀን ነው፡፡ ጥሩ ፉክክር እንደሚኖር አሸናፊነቱ ግን የቅዱስ ጊዮርጊስ እንደሚሆን ርግጠኛ ነኝ፡፡ ደርቢው የሚደረገው በሜዳችን ቢሆን ጥሩ ነበር፡፡  አዲስ አበባ ላይ ቢደረግ የተሻለ ደርቢ ይሆን ነበር፡፡ አዳማ ላይ መካሄዱ ግን ቅዘቅዝ አድርጎታል፡፡  15ቱም ክለቦች ሲገጥሙን ጠንክረው ስለሚመጡ በኛ በኩል ለአጸፋው መዘጋጀት ብቻ ነው የሚጠበቅብን..።

ሊግ:- ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የምታደርጉትን ጨዋታ ክ14ቱ ክለቦች ጋር እንደምታደርጉት ጨዋታዎች የሚቆጠር ነው…..?

ዘሪሁን:- ደርቢ ስለሆነ ትርጉሙ እኩል አይደለም፡፡ ግን ደርቢ የሚባለው በሜዳችን ስንጫወት ነው፡፡   ግን አልሆነም፡፡ ቅርብ ከተማ ላይ በመደረጉ በርካታ ተመልካች ሊኖር ይችላል፡፡ በሜዳችን እንደ መጫወት ግን አይሆንም ደርቢ ነው ስለሚባል ጠንካራ ጨዋታ ሊኖር ይችላል.. ግን ተጋጣሚዎቻችን ሲገጥሙን ጠንክረው መጥተው ስለሚሆን በእኛ በኩል ለደርቢውም ተጠናክረን በመግባት እንደምናሸንፍ ተስፋ አደርጋለሁ።

ሊግ:– ለደጋፊው የምትለው የመጨረሻ መልዕክት ካለ…?

ዘሪሁን:- የሁለቱም ክለቦች ደጋፊዎች ሰላማዊ በሆነ መንገድ ክለቦቻቸውን ደግፈው የተመዘገበውን ውጤት በጸጋ እንዲቀበሉ አደራ እላለሁ… ለእኛ ደጋፊዎች ደግሞ እንደ ሁሌው በዲሲፕሊን ቡድናቸውን 90 ደቂቃ ደግፈው 12ኛ ተጨዋችነታቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ አደርጋለሁ፡፡ በኛ በኩል በጨዋታው ለማሸነፍና ክለባችንን ከፍ ለማድረግ  የምንችለውን ለማድረግ ተዘጋጅተናል፡፡

ሊግ:- ለቆይታችን በጣም አመሰግናለሁ…..

ዘሪሁን:- ኔም ከልብ አመሰግናለሁ….

 

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

P