Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ቅዱስ ጊዮርጊስ ድሮም ዘንድሮም የማወራለት ክለቤ በመሆኑ እናትም አባቴም ነው ማለት ይቻላል” “ኢትዮ ኤሌክትሪኮች አስቤውም አልሜውም የማላውቀውን ጥሩ አቀባበል አድርገውልኛል” አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ /ኢትዮ ኤሌክትሪክ/

ፈረሰኞቹ ሁለት ጊዜ በተከታታይ በ2014 እና በ2015 የፕሪሚየር ሊጉ የዋንጫ አሸናፊ ሲሆኑ አሰልጣኙ የመልበሻ ቤት አለቃው እሱ ነበር… በ2016 በተከታታይ ጨዋታዎች ውጤት ሲጠፋ በእግር ኳስ ውለታ የሚባል ነገር የለምና ታግዶ ከቆየ በኋላ አመቱ ሲያልቅ ከክለቡ ለቋል… አሰልጣኙ በሌላ የህይወት ምዕራፍም የኢትዮ ኤሌክትሪክ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ለሌላ ታሪክ መልበሻ ቤቱን በይፋ ቀይሯል.. አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ… ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር በነበረው ቆይታ ከፈረሰኞቹ  እንዴት ለቀቀ..?፣ ከክለቡ ጋር በመለያየቱ ምን ተሰማው ..?  አሁንስ በኢትዮ ኤሌክትሪክ ሃላፊነቱ ምን አለመ..?  ስለ ረዳቶቹና ሌሎች ጉዳዮች የሰጠው ምላሽ የሚከተለውን ይመስላል።

ሊግ:- እረፍቱ እንዴት አለፈ..?

ዘሪሁን:- አሪፍ ነበር ጥሩ እረፍት ከቤተሰቤ ጋር አሳልፌያለሁ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የተፈጠረው ነገር ቅር ቢለኝም ከቤተሰቤ ጋር የማሳለፍ እድሉን ቅሬታዬን መርሺያ አድርጌ ተዝናንቼበታለሁ፡፡ በጣሞ ጥሩ ጊዜ ነበረኝ ማለት ይቻላል… ከዚያም በተጨማሪ ብዙ ተምሬያለሁ ፈተና ሊመጣ እንደሚችልና እንዴትም ማለፍ እንዳለብኝ አስተምሮኝ አልፏል፡፡ ለራሴ ክስተት ነው፡፡ አሰልጣኝ ስትሆን መቼ እንደምትቆይ አታውቅም ለሹመቴም ለስንብቴም መዘጋጀት እንዳለብኝ ተምሬያለሁ ከእረፍቱ መልስ ደግሞ ወደ አዲስ ምዕራፍ የምገባበትን ዕድል ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሰጥቶኝ፡፡ በአሁኑ ወቅት ጠንካራ ትግል ለሚገጥመኝ ለአዲሱ ፈተና እየተዘጋጀሁ እገኛለሁ፡፡

ሊግ:– በዚሁ አጋጣሚ እንኳን ደስ አለህ ባለቤትህ ወልዳለች፡፡ ለቤተሰቡ ተጨማሪ ሃይል መጥቷል…

ዘሪሁን:- /ሳቅ በሳቅ/ አዎ ባለቤቴ በሰላም ተገላግላለች ደስ ብሎናል ለመልካም ምኞትህ ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡

ሊግ:- ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ከመነሻው የዕገዳ ውሳኔ ሲተላለፍ ውሳኔያቸውን ሲነግሩህ ምን ተሰማህ ..?

ዘሪሁን:- በጣም ቅር ያሰኛል ክለቤም ሆነ አመራሮቹ አላናገሩኝም፡፡ በጣም የተከፋሁት በሱ ነው፡፡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ከሃላፊነቴ መታገዴ የተነገረኝ በ30 ሰከንድ የስልክ ንግግር ነው። ይሄ ደግሞ ያበሳጫል ያም ሆኖ ጊዮርጊስ ብዙ ታሪክ የሰራሁበት የምወደው ክለቤ ነው ብዙ ደስታ የሰጠኝ ቤቴ ነው ስለዚህ ምንም ቢሆን ክለቤን ልጠላ አልችልም፡፡ ጊዮርጊስን ከልቤ እወደዋለሁ ህይወት ግን  ይቀጥላል…

ሊግ:- ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ያላደረኩት ነገር አለ ብለህ ታስባለህ ..? ያልጨረስከው የቤት ስራ እንዳለ ይሰማሃል..?

ዘሪሁን:- ለምወደው ክለብ  አደረኩ የምለውም አለ አላደረኩለትም የምለውም አለ.. ግን ማንም ሰው አደረኩ ከሚለው በላይ ለክለቤ እንዳደረኩ ይሰማኛል…  ቡድኑን ሻምፒዮን ማድረግ ስራዬ ቢሆንም በተከታታይ ሁለት አመታት የፕሪሚየር ሊጉ ባለድል በማድረጌ ግን ደስተኛ ነኝ .. ነገር ግን ብዙ የሚገቡት ድሎች ነበሩ ብዬ ስለማስብ  አልረካሁም.. ስለክለቤ ለኔ ከእኔ በላይ ሆኖ የሚነግረኝ የለም፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድሮም ዘንድሮም የማወራለት ክለቤ በመሆኑ እናትም አባቴም ነው ማለት ይቻላል.. ስራ ላይ አሰሪና ሰራተኛ የሚባል ነገር በመኖሩ የመሰላቸውን ርምጃ ወስደዋል፡፡ ያም ሆኖ ክለቤን ማንም አልሰጠኝም ማንም አይነጥቀኝም፡፡ ከዚህ ክለብ ጋር የማልረሳው ተደጋጋሚ ደስታ በማግኘቴ አልረሳውም ሁሌም እኮራለሁ፡፡

ሊግ:– የኤ ላይሰንስ ያላችሁ አሰልጣኞች ስልጠና እየወሰዳችሁ ነው ….ተመቻችሁ..?

ዘሪሁን:- የፊታችን ቅዳሜ የሚጠናቀቅ ነው የሚሆነው የኤ ላይሰንስ ላለን አሰልጣኞች የተሰጠ የሪፍሬሽመንት ኮርስ ነው፡፡ አሪፍ ጊዜ እያሳለፍን ጥሩ እውቀት እያገኘንበት ነው ተመችቶኛል /ቃለ ምልልሱን ያደረግነው ረቡዕ ምሽት ነው/ ጥሩ ውይይት እያደረግን የእውቀት ልውውጥና ሽግግር እያደረግን ነው፡፡ ጥሩ ስልጠና ነው አቅም ፈጥሮብናል፡፡ እነ ኤሊት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ከቴክኒክ ክፍል እነ ደረሰን ጨምሮ ስልጠናው ላይ ያሉትን ባለሙያዎችን በሙሉ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡

ሊግ:- ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት በኋላ የመጀመሪያ የአረልጣኝነት ክለብህ ሊሆን ነው ምን ተሰማህ..?

ዘሪሁን:- ከቅዱስ ጊዮርጊስ የለቀኩበት መንገድ ቅር ያሰኛል፡፡ ነገር ግን ውስጤ ቅር ቢለውም ህይወት ይቀጥላልና በጥሩ ሁኔታ ወደ ተቀበሉኝ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሄጃለሁ፡፡ የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነቱ ይመቻል ደስ ብሎኛል.. እውነት ነው የተለየ ስሜት ይፈጥራል፡፡ ያው ግን ስራን አክብሮ በመስራት ጉዞውን መቀጠሌ የግድ ነው፡፡ እዚያ የቆየሁት ስራዬን በደንብ አክብሬ በመስራቴ ነው እንጂ እስካሁንም አልቆይም ነበር፡፡ አሁንም ይህን እምነትና የስራ ባህል በኢትዮ ኤሌክትሪክ መቀጠል የግድ ይላል… ከእግዚአብሄር ጋር እንደሚሳካ ተስፋ አደርጋለሁ…. ቡድኑ በሙሉ አዲስና ከተለያዩ ቦታ በመምጣታቸው እነሱን የማዋሃድ ከባድ የቤትስራ ይጠብቀኛል፡፡ ከቦርዱና ከረዳቶቼ ጋር ሆኜ ያሰብነው እንደምናሳካ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ አሁን ያለው አጀማመር አሪፍ ነው ያንን ማስቀጠል  እፈልጋለሁ፡፡

ሊግ:- ምን አሰባችሁ..? ምንስ አቀዳችሁ..?

ዘሪሁን:- ሃላፊነት ሲሰጥህ ያለ ዕቅድና ግብ መቀጠል አይቻልም፡፡ እንደ አንደኛ አመት ግን ጥሩ ተፎካካሪ ቡድን ለመገንባት ማቀድ የግድ ይላል… አዳዲስና  ወጣቶቹን አቀናጅቶ ውጤታማ ለመሆን ትልቅ ስራ ይጠበቅብኛል፡፡ ያን ለማድረግ አቅደን ተነስተናል…

ሊግ:- አምበሪቾን ከከፍተኛ ሊግ ያሳደገውን አሰልጣኝ ደጉ ዱባሞን ምክትልህ አድርገኧዋል .. የሚረዳውን የማይሰረስረውን ታማኝ አሰልጣኝ ነው ረዳቱ ያደረገው በሚል ሲያደንቁህ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ አየሁ…!

ዘሪሁን:- አዎ … አሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ ኤ ላይሰንስ አለው፡፡ ጎበዝ አሰልጣኝ ነው እንደሚረዳኝ እምነቴ የጸና ነው፡፡ በአምበሪቾ የሰራውን  ምርጥ ቡድን አቃለሁ፡፡ በማሸነፍና መሸነፍ ውስጥ አይደለም የምገምተው.. የክለቡ ችግርና ውጤት ማጣት ከአደረጃጀትና ከፋይናንስ ጋር የተገናኘ እንጂ ከእሱ የአቅም  ማነስ ነው ብዬ አላምንም፡፡ ተጋግዘን  እንደምንሰራ ተስፋ አለኝ፡፡

ሊግ:- ረዳቶችህን  ይዘህ መጥተሃላ..?

ዘሪሁን:- ከአሰልጣኝ ደጉ ውጪ ሌላው ምክትል አሳምነው ገ/ወልድ፣ የበረኛ አሰልጣኙ ውብሸት፣ አንድ አናሊስት አብሮን አለ… አዲስ አበባ ከተማ የነበረው አዲስ የህክምና ሰው በቀለ የሚባል አለ እሱም ተካቷል፡፡ በጋራ ሆነን እንደቡድን ጠንካራ ስራ እንደምንሰራ ተስፋ አደርጋለሁ.. ጠንካራ ቡድን ስለማዋቀር ምክንያት የማቀርብበት ጉዳይ የለም፡፡ እንደ አንድ ዋና አሰልጣኝ ሙሉ የኮቺንግ ስታፌን ይዤ ነው የመጣሁት … በዚህ አጋጣሚ  የኢትዮ ኤሌክትሪክ አመራሮችን አመሰግናለሁ።

ሊግ:– በእኛ ሀገር ዋናው ሲባረር ረዳቱ ይተካል፡፡ ይሄ ማለት በአብዛኛው ረዳቱ አልረዳውም ሰረሰረው ወይም ክለቡ ለምን እንዳመጣቸው አያውቅም ማለት ነው ይህን አልታዘብክም..?

ዘሪሁን:– ረዳቶቹ ተጠሪነታቸው ለዋና አሰልጣኙ መሆኑ የተዘነጋ ይመስለኛል… ለዚህ ነው ሰበብ የማይጠፋው እሱ እንዲህ አለ..እነኚያ እንዲህ ነው አሉ እየተባለ የሚነገረው… ረዳቶቹ ተጠሪነታቸውና ረዳትነታቸው ለዋና አሰልጣኙ  መሆን አለበት …ይሄ መስተካከል አለበት… እኔጋ ያሉት ረዳቶቼ የምር የኔ ረዳት እንደሚሆኑ ለራሳቸውም ሆነ ለቡድኑ ታማኝ እንደሚሆኑና እንደሚሰሩ እምነቱ አለኝ፡፡ የቡድኑ ማናጅመንት የተቀየረ ይመስላል አዲስ የቡድን መሪ ተመድቦልኛል… ሁሉንም አመሰግናለሁ፡፡

ሊግ:- የቡድኑን ቦርድ ማኔጅመንትና ሰራተኞች እንዴት አገኘሃቸው…!

ዘሪሁን:- አስቤውም አልሜውም የማላውቅ ጥሩ አቀባበል አድርገውልኛል … ውይይት ስናደርግ ትልልቅ ሆቴሎች ውስጥ  ነው ጥሩ ተነጋግረን ተመካክረን ነው የምንሰራው … ያልተጠበኩት ክብርና ዋጋ ለሰጡኝ አመራሮቹ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡ ሁኔታዎች በጥሩ መልኩ እየሄዱ ይገኛሉ ሁሉም ቡድኖች ተመሳሳይ ድርጊት ቢያደርጉ ለኳሱ ትልቅ እመርታ ይሆናል ብዬ አስባለሁ..

ሊግ:– ቡድኑን የማጠናከር ስራው ምን ይመስላል ..?

ዘሪሁን:- ሙሉ ቡድኑ በሚያስችል መንገድ በወጣቶች የተሞላ ነው….ምናልባት 3 ሲኒየሮች ቢኖሩበት ነው… ተፎካካሪ ለመሆን መጠናከር  አለበት …. አዲሱ የፋይናንስ ህግ ያዘኝና ፈተና ሆኖብኛል… ወጣቶች ሆነው ልምዳቸውን መስጠት የሚችሉ ልጆችም አሉኝ .. ያው ግን እነሱን የማዋሃድ ሃላፊነቱ በእኔና በአሰልጣኞች ቡድኔ ትከሻ ላይ አርፏል ..

ሊግ:- የመጨረሻ የተቀመጠውን ትልቁን በጀት 57 ሚሊዮን ብር የመጠቀም መብት ካላቸው 5 ክለቦች መሃል አንዱ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ነው… እንዴት ገንዘቡ አነሳችሁ..?

ዘሪሁን:- ተጨዋቾቹ የሚጠሩትን ክፍያ ማሰብ ነዋ .. ተጨዋቾቹ 400 ሺህ ብር ይከፈለን ቢሉ ግሮሱ ወደ 500 እና 600 ሺህ ይጠጋል አምስት ተጨዋቾችን ብንገዛ ስንት እንደሚመጣ አስብ በአራትና አምስት ተጨዋቾች ደግሞ እስከ 25 ሚሊዮን ብር ይሄዳል። ወጣቶችን ሳይጨምር አንድ ቡድን ከ1-25 ተጨዋቾችን ይይዛል፡፡ በጀቱ በአስገዳጅ መንገድ በመያዙ ተቸገርኩ እንጂ ነገ የተሻለ ውጤት የሚያመጡ ወጣቶችን ይዘናል ያሉበትን ክለብ እና ሀገራቸውን እንደሚጠቅሙ ተስፋ አደርጋለሁ…. ውጤታማ ለመሆን ጠንክረን እንሰራለን የማሸነፍ አዕምሮ ያላቸውን ልጆች መያዝ የግድ ይላል ይሄ ደግሞ በስራ የሚመጣ ነው ጥሩ ውጤት ይመጣልና መትጋት የግድ ነው፡፡

ሊግ:– ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዋንጫ አሸናፊ ሆኖ ሊጉ አዲስ አሸናፊ አሳይቶናል ይገባቸዋል …?

ዘሪሁን:- አዎ.. በደንብ ሰርተው ጥሩ ታግለው አሸንፈው ዋንጫ አሳክተዋል ይገባቸዋል … አሰልጣኝ በጸሎት የምወደውና ጠንካራ የሆነ አሰልጣኝ ነው፡፡ ትልቅ ድል አሳክቷል አሸናፊነቱን እንዳረጋገጠ እንኳን ደስ አለህ ብዬዋለሁ …. አሁንም  በአጋጣሚው እንኳን ደስ አለህ ማለት እፈልጋለሁ.. በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒየንስ ሊግ ሀገር ወክሎ እየተጫወተ ነው እንዲሳካላቸው እመኛለሁ፡፡

ሊግ:- የዋንጫ ፉክክሩ እስከ መጨረሻ ሳምንት ሄዶ ነበር ..ለውጥ እድገት ነው ማለት ይቻላል ..?

ዘሪሁን:- አዎ በየጊዜውማ ለውጥ ነው፡፡ ጥሩ ፉክክር አይተናል የሊጋችን መገለጫ ባህሪ እየሆነ ነው አሪፍ ለውጥ ነው፡፡ በዘንድሮው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና መቻል ያሳዩት ፉክክር በ2014 እኛና ፋሲል ከነማ መሃል የነበረውን ፉክክር ያስታውሳል እኛ ከአዲስ አበባ ከተማ ፋሲል ከነማ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ያደረግነው ፍልሚያ አይረሳም ያ ጥንካሬ እየተላበስን እንደመጣን ያሳየን ነው፡፡ ዘንድሮም የነበረው ፉክክር በጥሩ ጎኑ የሚታይ ነው፡፡ ትልቅ ትኩረት እንደሚያስፈልግ መማሪያም ይመስለኛል፡፡

ሊግ:- በሊጉ የተለየ የምትለው ቡድን ገጥሞሃል ..?

ዘሪሁን:- ሁሉንም ቡድኖች ነው የማደንቀው… በፋይናንስ ችግር ውስጥ ሆነውም  ለክለባቸው ድል ለማሊያቸው የሚታገሉ ቡድኖችን አይቻለሁ ለነኚህ ክብር አለኝ .. ትልልቆቹ ቡድኖች ጋርም ሲጫወቱ የነበራቸው አቋም ያስደስታል ላለመሸነፍ የሚደረገውን ጥረት ሳይ ሁሉንም ቡድኖች ማክበር እፈልጋለሁ..

የወረዱት ቡድኖች ላለመውረድ ያደረጉትን ትግል ማየት በቂ ነው.. እነዚህ ነገሮች ለሊጉ ጥሩ ግብአት ነው፡፡ ከአራት በላይ የገባ ጎል ብዙም የለም ይሄ ነው መታየት ያለበት ብዬ አስባለሁ..

ሊግ:- የታዘብከው ለውጥ የሚያስፈልገው ለአንተ ምንድነው..?

ዘሪሁን:- ያለጥርጥር ሁለቴ የማላስብበት የሜዳዎቻችን ጉዳይ ነው .. ከፋይናንሺያል ህጉ በላይ ሜዳው ላይ መተኮር አለበት ባይ ነኝ …. ሜዳ የለንም በቀጣይ በጣም መሰራት ያለበት ጉዳይ ነው… የበጀት ገደቡ ሜዳ ከማሰራት ጋር ቢያያዝ ጥሩ ነበር፡፡ በጀቱ በሂደት ቢመጣ ጥሩ ይመስለኛል፡፡ ድንገት ህግ መሆኑ ክፍተት እንዳይፈጥር ያሰጋኛል …የሚቀድመው ሜዳ ነው እንኳን ውድድር የምናደርግበት የልምምድ ሜዳ ተቸግረናል ..ትኩረት ለሜዳዎቻችን ለማለት እፈልጋለሁ.. ገንዘቡ በጀቱ መገደቡ ላይ ብዙም አልተከፋሁም ግን ሲመጣ ሂደት ቢኖረው ጥሩ ነው ባይ ነኝ … መቅደም ያለባቸው ጉዳዮቻችን ቢቀድሙ እመርጣለሁ.. ፕሮሰስ አለመኖሩ ህጉን  የሚተገብርና ህጉን የሚያፈርስ ክለብ እንዳይኖር ያሰጋል። ውሳኔውን የማይተገብር እያለ ህጉን የሚተገብረው  ይጎዳል ይሄን ቀዳዳ ማጥፋት ይገባል.. አምና የሚፈልጉትን ተጨዋች ያስፈረሙት ክለቦች ተጠቅመዋል ማለት ነው፡፡ ብር የሌላቸው ተጨዋቾቻቸውን ሊቀሙ ነው..? ይሄ ነው የበጀት ገደቡ ክፍተት… ግን ለሀገሪቱ እግርኳስ እስከጠቀመ ድረስ የትኛውም ህግ መተግበሩ ልክ ነው፡፡

ሊግ:- የኢትዮ ኤሌክትሪክ ደጋፊዎችን አገኘሃቸው ..?

ዘሪሁን:– ከደጋፊው ጋር አልተገናኘሁም ነገር ግን ከቦርዱ ጋር ካሉት የደጋፊ ማህበሩ አመራሮች ጋር ተገናኝቻለሁ…

ሊግ:- ጨረስኩ …ማስተላለፍ የምትፈልገው መልዕክት አለ…?

ዘሪሁን:- ውድ ለሆኑ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ምስጋናዬን አድርስልኝ …ለነሱ ትልቅ ምስጋና አለኝ፡፡ በነበረኝ የሃላፊነት ጊዜዬ 12ኛ ሰው ሆነው ከጎኔ ቆመው አግዘውኛል በዚህም አጋጣሚ አሁንም ደግሜ አመሰግናለሁ፡፡ ከዚህ ውጪ የክለቡ የቦርድ ፕሬዝዳንት አቶ አብነት ገ/መስቀልን በጣም አመሰግናለሁ፡፡ በቅዱስ ጊዮርጊስ የትልቅነት ጉዞ ላይ ትልቅ ዋጋ  ከፍሏልና ያለኝን ከልብ የሆነ ክብር  ለአቶ አብነት ገብረ መስቀልን መግለጽ እፈልጋለሁ አመሰግናለሁ።

ሊግ:- አሰልጣኝ ዘሪሁን ለሰጠኧን ቃለምልልስ አመሰግናለሁ፡፡ በአዲሱ ሃላፊነትህ እንዲሳካልህ እመኛለሁ….

ዘሪሁን:- አመሰግናለሁ እናንተንም ….

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

P