በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ተሳትፎው ለቅዱስ ጊዪርጊስ፣ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ለኢትዮጵያ ቡናና ለጅማ አባጅፋር ክለቦች ተጫውቶ አሳልፏል፤ ከዛ ባሻገር ደግሞ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ከዚህ ቀደም በመመረጥ የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ /ሴካፋ/ ዋንጫ ላይ የውድድሩ ኮከብ ተጨዋች ተብሎም ተሸልሟል፤ የአሁን ሰዓት ላይ ደግሞ ለድሬዳዋ ከተማ ክለብ በመጫወት በውድድር ዘመኑ ተሳትፎው ላይ ጥሩ እየተንቀሳቀሰም ይገኛል፤ ይሄ ተጨዋች ኤልያስ ማሞ ሲሆን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሊጉ ውድድር በተቋረጠበት የአሁን ወቅት ላይ ተጨዋቹን በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ማለትም ስለኮሮና ቫይረስ፣ ስለቡድናቸው፣ ስለራሱና ተያያዥ በሆኑ ጥያቄዎች ላይ አናግረነው ምላሽን ሰጥቶናል፤ ተከታተሉት፡፡
ሊግ፡- ኮሮና ቫይረስ በአሁን ሰዓት የዓለምም የእኛ ሀገርም ከፍተኛ ስጋት ሆኗል፤ በተለይ ደግሞ በውጪው ዓለማት የበርካታ ሰዎችን ህይወትም እየቀጠፈ ይገኛል፤ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ የእግር ኳስ ተጨዋች ይህን ስትሰማና ስትመለከት በውስጥህ ምን አይነት ስሜት ነው የተፈጠረብህ?
ኤልያስ፡- መጀመሪያ ላይ ስለ ኮሮና ቫይረስ አስመልክቶ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ መረጃውን ስሰማ ያንን ያህል ለእዚህ ደረጃ ያደርሰናል ብዬ ባላስብም እለት ከእለት ከሚታየው እና ከምንመለከተው ነገር በመነሳት ግን የአሁን ሰዓት ላይ የምናዳምጣቸው መረጃዎች በጣም አስከፊና የሰዎችንም ህይወት እያሳጣን በመሆኑ አስደንጋጭ እና የማላውቃቸው አይነት ጥሩ ያልሆኑ ስሜቶች ናቸው በውስጤ እየተሠሙኝ የሚገኙት፤ ቫይረሱን በሚመለከት እኛ ሀገር ላይ ገና መግባቱን ስንሰማ አስቀድመን በጣም ችላ ብለነው ነበር፡፡ በኋላ ላይ ብዙ ባለመጠንቀቃችንም ቀስ በቀስ ወደ እኛ ሃገር መጥቶም አሁን ላይ አስፈሪነቱም ቀጥሏል፤ እንደዛም ሆኖ አሁን ላይም ብዙ ትኩረትን ለእዚህ ቫይረስ እየሰጠነውም አይደለምና በምንችለው መጠን ከቫይረሱ ለመከላከል አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡
ሊግ፡- ኮሮና ቫይረስ እንደ እኛ ባሉት ሀገራት ከተዛመተ አደጋው በጣም የከፋ ነው የሚሆነው፤ ከዚህ በመነሳት ምን ቢደረግ ምን ብናደርግ ቫይረሱን መከላከል ይቻላል…..እስኪ አንተም እስከ እንደአንድ ሠው ምክርህን ስጥን?
ኤልያስ፡- ኢትዮጵያዊያን ከአኗኗራችንና ከአዋዋላችን በመነሳት ሁሉንም ነገር እንደምናውቀው እንደተቀሩት ዓለማት አይደለምና የዚህ ኮሮና ቫይረስ እየተስፋፋ መምጣቱ ለእኛ ብዙ የሚያስፈሩን ነገሮች አሉና ለእዛ ከወዲሁ ዕለት ከእለት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ነው የሚኖርብን፤ ኮሮና ቫይረስ በውጪው አለም ሁሉም ነገር ተመቻቶላቸው የእዚህን ያህል ሰው ህይወት ከነጠቀ ወደ ኢትዮጵያ እየተዛመተ ከመጣ ደግሞ በእኛ ጥንቃቄ በእኛ አስተሳሰብ እንዴት እንሆናለንም የሚለው ነገር በጣም ያሳስበኛል፤ አሁን እንኳን አስቤዛ ለቤት ለመግዛት ወደ ሱፐር ማርኬት በምወጣ ሰዓት የማየው ነገር በጣም ነው የሚያሳዝነው፡፡ ምንም አይነት ጥንቃቄን እያደረግን አይደለም የምንገኘው፡፡ ለእዚህ መንግስትና አንድአንድ የህብረተሰቡ አካል የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ቢገኝም አንዳንዱ ደግሞ ምንም አይነት ትኩረት እየሰጠው አይደለም ሠው እስኪሞት ድረስም እየጠበቀ የሚገኝ ነው የሚመስለኝና ሁኔታዎቹ ሁሉ በጣም አስፈሪ ናቸው ስለዚህም እኔም መምከር የምፈልገው ነገር ቢኖር እኛ ሀገር እንዲህ ያሉ ነገሮችን ተጠንቅቀህ እንኳን የማትችለው ቢሆንም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሚያወጣቸውን የየዕለት መመሪያዎችን በመከተል ሁሉም ሠው በየቤቱ በየመስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ያድርግ ነው የምለው፡፡ እኛም በተቻለን መጠን የተባልነውን ነገር ቢያንስ 20 እና 30 ፐርሰንት እንኳን ካደረግን ከዚህ ቫይረስም ራሳችንን፣ ቤተሰቦቻችንን፣ ልጆቻችንና ሀገራችንንም እንጠብቃለንና በተቻለን አቅም በእግዚአብሄር ስም በጣም እንጠንቀቅም ነው የምለው፡፡
ሊግ፡- የድሬዳዋ ከተማ ክለብ ኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ አሁን ላይ ሌሎች ቡድኖችም ወደተሳትፎው ቢገቡም እሱ ማህበራዊ ግዴታውን የተወጣ የመጀመሪያው ቡድን ሆኗል? በዚህ ዙሪያ ማለት የምትፈልገው ነገር ካለ?
ኤልያስ፡- እንደ ድሬዳዋ ከተማ ክለብ ተጨዋችነታችን ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ ይሆናል በሚል በአሁን ሰዓት እኛ ያደረግነው ድጋፍ ቫይረሱ ከአቅም በላይ እየሆነ በመምጣቱ ተነገረልን እንጂ ይሄ ክለብ ከአምና ጀምሮም ነው የተለያዩ ማህበራዊ ግዴታዎችን በመወጣትም ላይ ያለው፤ እኔ እንኳን ክለቡን ከተቀላቀልኩበት ጊዜ አንስቶም ይሄን ነገር በአይኔ ለመመልከትም ችያለው፤ ከዛ ውጪም ራሴም የእዚህ አካል ተሳታፊ ሆኜም ከየቡድኑ አባላቶች በሚቆረጠው ወርሃዊ ደመወዝም ላይ እኔንም አሳትፌ የማህበራዊ ግዴታዬንም እየተወጣሁ ነው የምገኘው፡፡ እኛ የድሬዳዋ ከተማ ክለብ ተጨዋቾች በራሳችን ተነሳሽነትና ፈላጊነት አሁን ላይ ለኮሮና ቫይረሱ መከላከያ ድጋፍ ከማድረጋችን ባሻገር ከዚህ በፊት በሚቆረጠብን የወር ደመወዝ ስናደርግ የነበረው ድጋፍና አስተዋፅኦ ለአረጋውያን ለተቸገሩ እና ለታመሙ የቀድሞ የድሬዳዋ ከተማ ላፈራቸው ታዋቂ ስፖርተኞችን መርዳት ነው፤ ይህን ስናደርግም የእኛ ተሰሚነት በድሬዳዋ እንደ አዲስ አበባ ብዙ ሚዲያ ስለሌለ ባይነገርልንም በየጊዜው ጥሩ ጥሩ ነገሮችንም እናደርጋለንና በእዚሁ አጋጣሚ ለአጠቃላይ የቡድኔ ተጨዋቾች ከፍተኛ ምስጋናዬን ላቀርብላቸው እፈልጋለሁ፡፡
ሊግ፡- የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በሚደረገው ድጋፍ መጀመሪያ አካባቢ የገንዘብ እርዳታው ይደረግ የነበረው በአንድአንድ ስፖርተኞችና አሰልጣኞች አማካኝነት ብቻ ነበር፤ ወደ እናንተ ክለብ ስንመጣ እና አሁን ደግሞ ሌሎችም ቡድኖች ድጋፍን እያደረጉ ያሉት እንደ ቡድን በመሰባሰብ ነው፤ ከእዚህ አንፃር እየተደረገ ስላለው ድጋፍ ምን ማለትን ትፈልጋለህ?
ኤልያስ፡- በአሁን ሰዓት ለኮሮና ቫይረስ የሚደረገው የገንዘብ እርዳታና ድጋፍ እንደግልም እንደቡድንም ተጀምሮ ቀስ በቀስ ወደ ሁሉም ክለቦች እየተዳረሰ መምጣቱና የገንዘብ አሰባሰቡም እንደ ቡድን መሆኑ ከሚገኘው ገቢ አኳያ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ በእዚህ የማህበራዊ ግዴታ ውስጥም እኛ ስፖርተኞች መሳተፋችንም ጥሩ ነው፤ ለኮሮና ቫይረስ የአሁን ሰዓት ላይ እንደ ቡድን ከምናደርገው ድጋፍ በተጨማሪ እኔን ጨምሮ ቀድመን ለተጫወትንባቸው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ቡና ቡድኖች ጋርም ሆነን እርዳታን ያደረግንም ተጨዋቾች አለና በእዛ ውስጥ መሳተፍ መቻልም ያስደስታል፤ ምክንያቱም እኛ ስንኖር ነው ሁሉም ነገር ኳሱም ጭምር የሚኖረው፤ ስለዚህም ከፈጣሪ ጋር ወደፊትም ቢሆን ሌሎች ብዙ የሚረዱም አረጋውያኖች አሉና ሁላችንም ተረዳድተን የሚጠበቅብንን ነገር ከአሁኑ ብንወጣ ጥሩ ነው፤ በእዚህ እርዳታ ላይ ያልተሳተፉ ሌሎች ክለቦችም ካሉ ቢሳተፉ ጥሩ ነው፡፡ ያን ስናደረግም በህብረተሰቡ አካባቢም እግር ኳሱ ላይ ያላቸው አመለካከት መልካምና ጥሩ ይሆናልም ብዬ አስባለው፡፡
ሊግ፡- በኮሮና ቫይረስ የዓለም እግር ኳስ እንደዚሁም ደግሞ የእኛም ሀገር እግር ኳስ ሊቋረጥ ችላል፤ ከዚህ በመነሳት ስፖርተኛው በአሁን ሰአት በየቤቱም ተቀምጧልና ስፖርቱ ከሚፈልገው ነገር አንፃር ስፖርተኛው በእዚህ ወቅት ምን ማድረግ ይኖርበታል…. አንተ
Mussie GIRMAY ❄, [04.04.20 10:24]
ስ ምን ነገሮችን እየሠራህ ነው?
ኤልያስ፡- የእግር ኳሡን አስመልክቶ ውድድሮቹ አይደለም በእኛ ሀገር በአለም ላይም መቃረጣቸው ብዙም የሚያስገርም አይደለም፤ መቋረጡ ቫይረሡ እያስከተለው ካለው ችግር አኳያ ተገቢ እና ተገቢም ውሳኔ ነው፤ የስፖርተኞችን ሁኔታን በተመለከተ የውጪዎቹ ተጨዋቾች የአሁን ሠዓት ላይ ዝም ብሎ መቀመጡ ለጤና ጥሩ ስላልሆነ በየመኖሪያ ቤታቸው በግል ሆነው ነው ስፖርትን እየሰሩ ያሉት ወደ እኛ ሀገር ስትመጣም አሁን ለምሳሌ እኔ በቤቴ ውስጥ ላለማረፍ ስል እንደበፊቱ በቂ ነው ባልልም በግሌ ዱብዱብ እያልኩና ሌሎችንም ልምምዶችን እየሠራሁ ነው የምገኘው፡፡ ስለዚህም ሁላችንም ቤት ውስጥ ሆነን እነዚህን ልምምዶች ልንሰራ ይገባናል፡፡
ሊግ፡- በመኖሪያ ቤት ሆኖ ልምምድን ከመስራት አኳያ የውጪዎቹ ብዙ ማቴሪያሎች ኖሯቸው ነው እየተለማመዱ የሚገኙት፤ ከእኛ ነባራዊ ሁኔታ ተነስቼ አንተን ልጠይቅህና በእዚህ በኩል ያንን አሟልተህ ነው ልምምድን የምትሠራው?
ኤልያስ፡- በእዚህ በኩል እንደእነሡ ባልሆንም ብዙ መሳሪያዎች ባይኖረኝም በቤት ውስጥ ግን እኔ የምለማመድባቸውና አስቀድሜ የገዛኋቸው 60 እና 70 ፐርሠንት የሚሆኑ የመለማመጃ መሳሪያዎች አሉኝና በእነዛ ነው እየተለማመድኩ የምገኘውና አልተቸገርኩም፡፡
ሊግ፡- ለኮሮና ቫይረስ ጥንቃቄ ሲባል በአሁን ሠአት ቤት ውስጥ ከባለቤትህ ጋር ነው የምትገኘው በእዚህ በኩል አንተም ሆንክ ባለቤትህ ራሳችሁን የምትጠብቁበት መንገድ የቱን ያህል ነው?
ኤልያስ፡- ኢትዮጵያኖች በተፈጥሮአችን ስንኖር እንዲህ ያለ ነገሮችን ብዙም አለመድንምና ከዚህ በፊት አንድ ነገር ሲከሠት እግዚአብሄር ይጠብቀን ነበር የምንለው፤ አሁን ላይ ግን ያለው ሁኔታ በጣም ያስፈራልና ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ነው ራሴንም ቤተሰቤንም እጠብቅኩኝ የምገኘው፤ ምክንያቱም በእዚህ ቫይረስ አንድ ሠው ተያዘ ማለት ቤተሰብህን ልጆችህን እንደዚሁም ደግሞ አካባቢህንም ያዘ ማለት ነውና ለእዚህ እኔም ሆንኩ ባለቤቴ ከሰዎች ጋር ያለንን ርቀትን እየጠበቅን እጃችንን እየታጠብን ቫይረሱን ለመከላከል እንዲቻል የሚወጡ መመሪያዎችን ተግባር ላይ እያዋልን ራሳችንን እየጠበቅን ነው፡፡
ሊግ፡- በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከሚወደደው እግር ኳስ መጫወትም ሆነህ መመልከቱ ርቀህ እቤት ውስጥ ስትውል ምን ምን ነገሮች ይናፍቁሃል?
ኤልያስ፡- ብዙ ነገሮች ናቸው የሚናፍቁኝ፤ ምን መናፈቅ ብቻ ሁሉም ነገርም እየደበረኝ ነው የሚገኘው፤ ምክንያቱም ከእግር ኳስ መራቅ በጣም ከባድ ነገር ነው፤ እግር ኳስ ማለት ለአንተ በጣም ደስታ የሚሰጥህ ስፖርት ነው፤ ግን ምንም አማራጭ ስለሌለንና ቫይረሱም ተሰባስበህ ኳስን እንድትጫወት ስለማይፈቅድልህ ብትጫወት ደግሞ ለአደጋ ስለሚያጋልጥህና ከእንቅስቃሴ ውጪም ስለሚያደርግህ ይኸው በቤት ውስጥ እኔም ሆንኩ ሌሎች ተጨዋቾች እንዲያሳልፉም ተደርገዋልና ያው ሁኔታዎቹን መቀበል የግድ ነውም የሚልህ፡፡
ሊግ፡- በአሁን ሰዓት ቤት ውስጥ ስፖርት ከመስራት ባሻገር ሌሎች የምትጠቀማቸው ነገሮችስ አሉ? ከጓደኞችህ ጋር የምትገናኝበት መንገድስ ምን ይመስላል?
ኤልያስ፡- ከጓደኞቼም ሆነ ከክለብ አጋር ተጨዋቾቼ ጋር የአሁን ሰዓት ላይ በብዛት የምንገናኘው በስልክ ብቻ ነው፤ እቤት ውስጥ በውልበት ሰዓት ደግሞ ሌላ የማደርገው ነገር ቢኖር የፕሌይስቴሽን ጌም አለኝና እሱን መጫወት ከበፊት ጀምሮ ስለምወደው ጊዜዬን በእዛ አሳልፋለው፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዘንድሮ የውድድር ዘመን ተሳትፎ የአሁን ሰዓት ላይ ለምትጫወትበት የድሬዳዋ ከተማ ክለብ ጥሩ እንቅስቃሴን እያሳየ ይገኛል፤ ቡድኑ በጣም ተመችቶሃል ማለት ነው? ክለባችሁንስ በሊጉ ተሳትፎ እንዴት አገኘኸው?
ኤልያስ፡- በፕሪምየር ሊጉ ላይ ያለንን የውድድር ተሳትፎ እንደተመለከትኩት የመጀመሪያው ዙር ላይ እንደተጠበቅነው አልነበርንም፤ ደካማም እንቅስቃሴን ነበር ያደረግነው፡፡ ዙሩ ሊጠናቀቅ ሲቃረብ ደግሞ ትንሽ የማስተካከያ ስራዎችን በመስራት እስከ ሁለተኛው ዙር የመጀመሪያዎቹ ጨዋታዎች ድረስ በከፍተኛ የተሳሽነት እና ፍላጎት በመጫወት ለውጦችን አምጥተን ነበር፤ በኋላም ሊጉ በዓለም ላይም ሆነ በሀገራችን በመጣው ኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተቋረጠ፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ወደፊት የሚቀጥል ከሆነ በዓመቱ መጨረሻ ላይ ቡድናችሁ ምን ውጤትን ያመጣል?
ኤልያስ፡- በመጀመሪያ ደረጃ ፈጣሪ ሁሉንም ነገር ሠላም ያድርግልን፤ ምክንያቱም ሠላም ሲኖር ነውና ሁሉም ነገር የሚኖረው፤ ያ ከሆነ በኋላ ግን ውድድሩ የሚጀመር ከሆነ እንደ ቡድኑ ተጨዋችነቴ ማለት የምፈልገው ነገር ቢኖር ከዚህ ቀደም በነበሩት ተደጋጋሚ አመታቶች ክለቡ ላለመውረድ ሲጫወት ነበርና አሁን ላይ ይሄን ታሪክ ለመቀየርና ብሎም ደግሞ አሁን ከያዝነው ደረጃም በተሻለ እስከ 6 እና 7ኛ ደረጃ ሆነን ለማጠናቀቅ ነው ይሄ እቅድም የአሰልጣኛችንም ጭምር ስለሆነ በእዛ ደረጃ ሆነን ቀጣዮቹን ጨዋታዎች የምንጫወተው፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ በሀገሪቱ ትላልቅ ለሚባሉት የቅዱስ ጊዮርጊስና የኢትዮጵያ ቡና ክለቦች ውስጥ ተጫውተህ አሳልፈሃል፤ አሁን ደግሞ ለድሬዳዋ ከተማ ክለብም እየተጫወትክ ይገኛል፤ ከወቅታዊ አቋምህ በመነሳት ምን ትላለህ? ስለ ቀጣዩ ጊዜ የኳስ ተሳትፎውስ ምን ትላለህ….
ኤልያስ፡- በድሬዳዋ ከተማ ክለብ ውስጥ በአሁን ሰዓት ያለኝ ወቅታዊ አቋም ጥሩ የሚባል ነው፡፡ ያም ሆኖ ግን በትላልቅ ቡድኖችና በብሄራዊ ቡድን ደረጃ የነበረኝን የበፊቱን ምርጥ የሚባል ችሎታዬን በደንብ ስለማውቅ አሁን ላይ በዚህ ብቻ ተወስኜ የምቀር አይነት ተጨዋች አይደለውም፤ ስለዚህም ለቀጣዩ ጊዜ የኳስ ጉዞዬም የማስብ አይነት ተጨዋች ስለሆንኩም ራሴን ከወዲሁ ለእዛም በሚገባ አዘጋጀዋለው፡፡
ሊግ፡- እንደ እግር ኳስ ተጨዋችነትህ አሁን ካለህበት ደረጃ በመነሳት በውስጥህ የቁጭት ስሜት አለብህ? በኳሱስ የምፈልግበት ደረጃና ስፍራስ ላይ ደርሻለውስ ትላለህ…..
ኤልያስ፡- አዎን፤ የእግር ኳስ ተጨዋች ስትሆን የቁጭት ስሜት ከሌለህ አንተ ስፖርተኛ አይደለህምና ሁሌም ነው መቆጨት ያለብህ፤ ካልተቆጨህ ደግሞ እንዴት ነው ወደ ምትፈልገው ደረጃ ላይ መድረስ የምትችለው፤ የእኛ ሃገር ኳስን እንደምታየው ብዙ የተጠና ነገር ስለሌለ ሁሌም እንደፈለግከው አይደለም ኳስን የምትጫወተው፤ በተለይ ደግሞ ጥሩ ችሎታ ኖሮክና በለጋ እድሜ በፍጥነት ስትታወቅ ከአንድ እና ከሁለት ዓመታት በኋላ አንተን እንዳረጀ አይነት ተጨዋችም አድርገው ይቆጥሩሃልና ብዙ ነገሮች በጣም አስቸጋሪዎች ናቸው፤ ከዛ ተነስውም ያኔ አንተን ጥሩ እየተጫወትክም ከሲስተሙ ለማውጣት እና ኳሱን እንድታቆምም የሚታሰብልህ ነገር አለ፤ በዚህ በኩል አንድአንድ ተጨዋቾች ላይ ገና ኳስን በትክክለኛው ሁኔታ መጫወት ጀምሬበታለውና እውቅናንም እያተረፍኩኝ መጥቼያለው በሚሉበት ሰዓት ያልሆኑ ነገሮች ሲወራባቸውም የሰማሁበት ሁኔታ አለና እነዚህ ነገሮች ሁሌም ነው የሚገርሙኝ፡፡ የእግር ኳስን ስጫወት በምትፈልግበት ደረጃ ላይ ደርሰሃል ላልከኝ መልሴ በፍፁም ነው፤ ምክንያቱም ሀገሬንም ክለቤንም ገና ማገልገል ይጠበቅብኛልና፤ ስለዚህም አሁን ላይ እኔ የምለው ኳሱን የመጫወት ጥሩ አቅሙ አለኝ፤ ምንአልባት መጫወት የማልችል የምሆነው ለአሰልጣኙ አጨዋወት ምቹ ካልሆንኩ እና ችሎታው ከሌለኝ ብቻ ነውና የእግር ኳስ ተጨዋቾች በአጠቃላይ መታሰብ ያለባቸው ከዚህ አንፃር እና ከችሎታው አኳያ እንጂ እንደ እኛ ሀገር ጥቂት ዓመታትን ተ
Mussie GIRMAY ❄, [04.04.20 10:24]
ጫውተህ ያለ እድሜህ ጥሩ እውቅናን ካተረፍክበት የቀጣይ ዓመታት ላይ በእድሜ ትልቅ ተጨዋች እንደሆንክ ታስቦ በመቁጠር አይደለም ሊሰራ የሚገባውና ከእዚህ ብዙ ነገር ልንማር ይገባል፤ በውጪው ዓለም እኮ እግር ኳስን እስከ 35 እና 36 ዓመታቸው ድረስ በደንብ አድርገው ሲጫወቱ እንመለከታለን፤ ምክንያቱም ኳስ ጨዋታ የችሎታ ጉዳይ እንጂ የቢሮ ስራም ስላልሆነ ከዚህ ተነስቶም ነው በእኛ ሀገር ላይ ስራዎች ሊሰሩ የሚገባቸው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመንህ ላይ ከአመታቶች በፊት የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ /ሴካፋ/ የውድድሩ ኮከብ ተጨዋች ተብለህ ተሸልመህ ነበር፤ ያንን ወቅት ወደኋላ ሄደህ እንዴትና በምን መልኩ ነበር የምታስታውሰው?
ኤልያስ፡- በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የተካሄደውን የሴካፋ ውድድር አሁን ላይ ሆኜ የማስታውሰው በጣም ጥሩ የተጫወትኩበትና የእግር ኳስ ዘመኔም ምርጡ ጊዜዬ የምለው ስለነበርያን ውድድር ሁሌም ቢሆን በጣም ነው እየናፈቅኩት የምገኘው፤ ያኔ ለብሄራዊ ቡድን ለመመረጥ የቻልኩት በኢትዮጵያ ቡና ክለብ ተጨዋችነቴም ምርጥ ብቃቴን ያሳየሁበት ወቅትም ስለነበርም ነውና እሱም መቼም አይረሳኝም፤ እንደዛ አይነት ጥሩ የውድድር ጊዜያቶችን አሳልፌ ግን አሁን ላይ ያለውን ሁኔታ ስመለከት ግን በእዛ ደረጃ ላይየምገኝ አይነት ተጨዋች አይደለሁም፡፡ በእግር ኳሱ አሁን ላይ የሚታየው ነገር የዛሬ 3 እና 4አመታት ላይ ከሚታየው ነገር በጣም ይለያል፤ ለማሸነፍ እና ለማሸነፍ ብቻም ነው ወደሜዳ የምትገባው ጥሩ ኳስን የማየት እድልህ በጣም አናሳ ነው፤ ወደተጨዋቾች ብቃት ስትሄድም አንተ ጥሩ እየተጫወትክ ታክል የሚገባ ተጨዋች ብቻ የሚወደስበትም ጊዜ ላይም ነው ያለነውና ከዚህ ተነስተን የእግር ኳሱ ጉዞአችን ላይ ብዙ ልንሰራበት ይገባል፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመንህ አሁን ላይ ለደረስክበት ደረጃ እኔን በማሰልጠን ቀርፆኛል ክሬዲቱንም ሊወስድ ይገባል የምትለው ማንን ነው?
ኤልያስ፡-የእግር ኳስ ተጨዋች ስትሆን ምን ጊዜም ቢሆን አንተ ልትረሳው የማይገባህ እና ቅድሚያም ሰጥተኸው ልታመሰግን የሚገባ ነገር ቢኖር የልጅነት እድሜህ ላይ አንተን በማሰልጠን ሃላፊነቱ ላይ የተሰማሩትን አሰልጣኞች ስም ጠርተህ ስለእነሱ ማውራት ስትችል ነው፤ በተጨዋችነት ዘመኔ እኔም በዛ ደረጃ የማስብ ተጨዋች ስለሆንኩም ወደ ኳሱ ስመጣ ልጅ ሆኜ ያሰለጠነኝን አሰልጣኝ ደረጄ ተስፋዬ /አንገቴን/ ከሰፈሬ ከምጫወትበት የ35 ሜዳ ወደ ትንሹ ስታድየም በማምጣት የጌታ ዘሩ ቡድን ውስጥ አስገብቶኝና ለጀርመኑ የዓለም ዋንጫ በተዘጋጀው ውድድር ላይም እንድጫወት አድርጎኝ ጥሩ እንድጫወትና ዋንጫውንም እንድናነሳ አድርጎኝ ነበርና ያን አልረሳውም፤ ከዛ ውጪም የሀይኮፍ የታዳጊ ቡድን አሰልጣኝ የነበረው ኤፍሬም ደምሴ ቤቢምበዛ ቡድንና የቅዱስ ጊዮርጊስ ታዳጊ ቡድንንም ሲይዝ እኔን ወስዶ በማጫወት ወደ ዋናው ቡድን እንዳድግ የጥርጊያውን በር ስለከፈተልኝ የእሱም ውለታ ፈፅሞ የማይረሳኝም ነው፤ ኤፍሬም ቤቢ በተለይ እኔን በክለብ ደረጃ ከማሰልጠኑ ባሻገር አሁን ድረስም ሜዳ እየገባ በማደርጋቸው ጨዋታዎች ላይ ሁሉ ስላለኝ ጥሩ ጎንና ምን ነገሮችንም ማስተካከል እንዳለብኝም የሚነርኝ ስለሆነም በእዚህ እሱ ይለያል፤ የኳስ ተጨዋችነት ዘመኔ ላይ ከእነዚህ አሰልጣኞች ሌላ ልጠቅሰው የምፈልገው ባለሙያ ቢኖር ደግሞ ወደቅዱስ ጊዮርጊስ የዋናው ቡድን በፍጥነት እንዳድግ ያደረገኝ ሰርቢያዊው የቡድኑ አሰልጣኝ ሚቾም ነበር፤ ለእሱ ከፍ ያለ ምስጋናም አለኝ፡፡ ሚቾ ጎበዝና ትልቅ አሰልጣኝ ነው፤ የእሱ ከእዚህ ሀገር መሄድም የብዙ ወጣት ተጨዋቾችን ህልምም አቀጭጯል፡፡
ሊግ፡- ከእነዚህ አሰልጣኞች ውጪ በጥሩነቱ ሌላስ የምትጠቅሰው አለ?
ኤልያስ፡- አዎን፤ ውበቱ አባተ በባንክ ቡድን ተጨዋችነቴ ለአንድ ዓመት ቢሆንም አሰልጥኖኝ አልፏልና እሱም ጥሩ አሰልጣኝ ነው፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስ ጨዋታ ዘመንህ ላይ በስቴድየም ውስጥ ስትጫወት ተመልክተኸውም ሆነ በኋላ ላይ አንተም ራስህ እየተጫወትክ ያደነቃቸው ተጨዋቾች እነማን ናቸው?
ኤልያስ፡- በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ ወደ ዋናው ቡድን አድጌ ስቴድየም ውስጥ ስጫወት ለመጀመሪያ ጊዜ አይቼው በጣም ያደነቅኩት ተጨዋች ቢኖር እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ አሁንም ደግሜ መናገር እፈልጋለሁ ሙሉአለም ረጋሳን ነው፤ እሡ የተለየ አይነት ተጨዋችም ነው፡፡ በአጋጣሚ ሆኖ ደግሞ ሁለታችንም የምንጫወትበት ቦታም ተመሳሳይ እና አንድ አይነት በመሆኑም የእሡ ችሎታ እና ብቃትን በየጊዜው ማየቴም በጣም ብዙ ነገሮችን ሊጠቅመኝ ችሏል እና እሱን አይቼ መምጣቴና ማደጌ በጣም ጠቅሞኛል፡፡ ራሴ እየተጫወትኩ ሌላው በተለየ መልኩ ያደነቅኳቸው ተጨዋቾች ደግሞ መስዑድ መሃመድና ዳዊት እስጢፋኖስ ናቸው፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመንህ ምን አይነት ባህሪይ ያለህ ተጨዋች ነህ?
ኤልያስ፡- መጥፎና የተለየ አይነት ባህሪይ ፈፅሞ የለኝም፡፡ ሰውን ስትቀርበውም ነው የምታውቀውና እኔንም በዛ መልኩ ነው ቀርበህ ስታየኝ የምታውቀኝ፤ ስለዚህም የእኔን ባህሪይ ባለማወቅ በአጋጣሚ ተሳስተው የነበሩም ሰዎች ነበሩና እነዛ ሰዎች ይቅርታ ብለውኝ በደንብ አድርገው ሊያውቁኝ ችለዋልና እኔ ማለት መሳቅና መጫወትን የምወድ አይነት ተጨዋች ነኝ፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመንህ ስትቆይ እስከአሁንምን ምን ነገሮችን አተረፍክ?
ኤልያስ፡- በእግር ኳስ ተጨዋችነት አትርፌያለሁ ብዬ የማስበው ነገር ቢኖር በኳስ ያገኘሁትን እርካታና ደስታን ብቻ ነው፤የእግር ኳስን በጣም ነው የምወደው፡፡ ይሄም ነው ትርፌ፡፡
ሊግ፡- በባህር ማዶ የእግር ኳስ ክለብ ማንን እየደገፍክ ነው ያደግከው?
ኤልያስ፡- አርሰናልን ለእነሱ ልዩ ፍቅርም ነው የነበረኝ፤ አሁንም ድረስም ደጋፊ ነኝ፡፡
ሊግ፡- በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አርሰናልን ስትደግፍ መደሰትም ማዘንም አለና የአንተን የእስካሁን ጉዞ በምን መልኩ ይታያል?
ኤልያስ፡- የእግር ኳስ ጨዋታ ስትጫወተውም ስትመለከተውም የምትወደው አይነት ስፖርት ነውና እኔም በአርሰናል ቡድን ደጋፊነቴ ሁለቱንም ማለትም ደስታንም ሃዘንንም ተመልክቼበታለውና ከዛ የዘለለ ነገር ግን ፈፅሞ የለኝም፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን በእዚህ አመት ስትመለከት የየትኛው ቡድን የጨዋታ እንቅስቃሴ ለአንተ ለየት ብሎብሃል፤ የቱስ ቡድን አስቸግሮአችዋል?
ኤልያስ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ለክለቤ ድሬዳዋ ከተማ በተጫወትኩባቸው ጨዋታዎች በእዚህ አመት እንደ ቡድን ሲጫወቱ ጥሩ ሆነው ያገኘኋቸውና እኛን ያስቸገሩን ቡድኖች የመጀመሪያው ኢትዮጵያ ቡና ሲሆን ሌላው ክለብ ደግሞ ሰበታ ከተማ ነው፤ ከሁለቱ ውጪ የእኛን ቡድን ጨምሮ በግል የምንቀሳቀስበት ሁኔታ ነው ያለውና እንቅስቃሴያችን ያንን ያህል እንደ እነሱ ጥሩ የምትለው አይደለም፤ በጨዋታው እንቅስቃሴ በተለይ ኢትዮጵያ ቡናዎች ኳስን በእግራቸው ላይ በማቆየትና ወደፊትም ሄደው ለመጫወት የሚሄዱበት መንገድ ጥሩ ሆኖ አይቼዋለውና ይሄን ነው ልጠቅሰው የምፈልገው፡፡