Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“በኢትዮጵያ ቡና ቆይታዬ ደስተኛ ነኝ፤ ቀጣዩም ኮከብ ተጨዋች መሆን አፈልጋለሁ”ዊሊያም ሰለሞን (ኢት.ቡና)    

 

ዊሊያም ሰለሞን /ኢትዮጵያ ቡና/

በኢትዮጵያ ቡና የዘንድሮ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ተሳትፎ ላይ ዓይን ውስጥ የሚገባ አበረታች ብቃቱን በሜዳ ላይ አሳይቷል፤ እንደ አማካይ ስፍራ ተጨዋችነቱም በተደጋጋሚ ጊዜ ወደ ተቃራኒ የግብ ክልል ጋርም በመድረስ ቀዳሚ ከሆኑ ተጨዋቾች መካከልም አንዱ ሆኗል፤ ይሄ ወጣት ተጨዋች ጠንካራና ደፋር ሲሆን የሚያገኛቸውን የግብ እድሎች መጠቀም ከቻለ ወደፊት ለትልቅ ደረጃ  ሊበቃ እንደሚችልም እየተነገረለት ይገኛል፡፡

ለኢትዮጵያ ቡና ዘንድሮ ፊርማውን በማኖር በጥሩ ብቃቱ እየተጫወተ የሚገኘውን ይኸውን የአማካይ ስፍራ ተጨዋች ዊሊያም ሰለሞንን የሊግ ስፖርቱ ጋዜጣ አዘጋጅ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አናግሮት ተጨዋቹ የሰጠው ምላሽ የሚከተለውን ይመስላል፤ ተከታተሉት፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ከ9 ዓመት በኋላ ወደ ኢንተርናሽናል ውድድር ስለመመለሱ

“በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የዘንድሮ የውድድር ዘመን ተሳትፎአችን እኛ ስንጫወት የነበርነው የውድድሩ ሻምፒዮና ሆነን ለአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ለማለፍ ነበር፤ ይሄ እልማችን ግን ፈጣሪ ስላላለው ሳይሳካልን ቀርቷል፤ ያም ሆኖ ግን ሊጉን በሁለተኛነት ደረጃ ላይ ሆነን በማጠናቀቅ ለኮንፌዴሬሽን ካፑ ውድድር ልናልፍ ችለናል፤ ከ9 ዓመትም በኋላ ቡናን ወደ ኢንተርናሽናል ውድድር እንዲያልፍ አድርገናል፤ ይሄ ሊሆን በመቻሉም እኔንም ሆነ የቡድኔ አባላቶችን ደስተኛ እንድንሆን አድርጎናል”፡፡

የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ለምን እንዳላሸነፉ

“ከሁሉ በላይ ዋንኛ እልማችን የነበረውን ይሄን ዋንጫ ከፍ አድርገን እንዳናነሳ ያደረገን የመጀመሪያው ምክንያት ከእኛ ቡድን የኳስ አጠቃቀም አኳያ የተመቻቸ ሜዳን ለማግኘት አለመቻላችን በተለይ ደግሞ ግጥሚያችንን በድሬዳዋ ስታድየም ስናደርግ የሜዳው ብዙ ምቹ አለመሆን ብዙ ነጥቦችን እንድንጥል ስላደረገን ከዛ ውጪ ደግሞ የራሳችን ጥቃቅን ክፍተቶችም ዋጋ እንድንከፍልም ስላደረጉን እነዚህ ናቸው ውጤትን አሳጥተውን ሻምፒዮና እንዳንሆን ያደረጉንና የመጪው ዘመን ላይ ግን ስህተቶቻችንን አርመን በመምጣት የሻምፒዮናነት እልማችንን እናሳካዋለን”፡፡

የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የመጨረሻ ቀን ጨዋታቸውን ከአዳማ ከተማ ጋር አቻ ስለመለያየታቸው

“ይሄን ጨዋታ እኛ በአሸናፊነት በማጠናቀቅና አቡበከር ናስርም ቤተሰቦቹ በእንግድነት በተገኙበት የሐዋሳ ዩንቨርስቲ ሜዳ ላይ ተጨማሪ ግብ አስቆጥሮ የኮከብ ግብ አግቢነቱን ቁጥር በሚያሰፋበት መንገድ የውድድር ዘመኑን ለመዝጋት ነበር ወደ ሜዳ የገባነው፤ ለጨዋታ ስንገባ ግን ያልተጠበቀ ነገር ገጠመን፤ አዳማ ሊያሸንፈንም ተቃርቦ ነበር፤ በስተመጨረሻ ግን የአቻነትን ግብ አስቆጠርንና ግጥሚያው በዛ ተጠናቀቀ፤ እኛም በዛ ጨዋታ ሽንፈትን ሳናስተናግድ የውድድር ዘመኑን በሁለተኛ ደረጃ ላይ ሆነን ስላጠናቀቅን ደስተኞች ሆንን”፡፡

ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉን ፋሲል ከነማ በበላይነት ስለማጠናቀቁና የውድድሩም ሻምፒዮና ስለመሆኑ

“ለፋሲሎች ድሉ ይገባቸዋል፤ ምክንያቱም ሁሉንም ክለቦች በብዙ የነጥብ ርቀትም ጥለው ሄደውም ነውና ውድድሩን ያሸነፉት፤ በዛ ላይም ደግሞ ሁሉም ተወዳዳሪ ክለባትም ስለ እነሱ ሻምፒዮናነትም ጥሩ ምስክርነትንም ሰጥቷልና የልፋታቸውንና የድካማቸውን ውጤትም ነው ሊያገኙ የቻሉት”፡፡

በሻምፒዮናው ፋሲል ከነማና በሁለተኛው ኢትዮጵያ ቡና መካከል የ13 ነጥብ ልዩነት ኖሮ ነው ሊጉ የተጠናቀቀቀው፤ በእዚህ ዙሪያ ምን አልክ?

“በፋሲል ከነማ እና በእኛው ቡድን ኢትዮጵያ ቡና መካከል ይሄን ያህል የነጥብ ልዩነት ኖሮ ውድድሩ ሊጠናቀቅ ቢችልም በሜዳ ላይ አቋም ግን በሁለታችን መካከል እንዲህ ያለ የሰፋ ልዩነትን አልተመለከትኩም፤ እንደውም በእንቅስቃሴ ደረጃ ከሁሉም የተሻለ ቡድንም የእኛ ነበር፤ ከእኛ አልፎም ሁሉም ቡድን በጨዋታ እንደሚበለጥም አምኖ ነበር ወደ ሜዳም የሚመጣውና ዘንድሮ ይሄን ነገር በውድድሩ ተሳትፎአችን በሚገባ ልመለከት ችያለው”፡፡

በኢትዮጵያ ቡና ስላሳለፈው የውድድር ዘመን ቆይታው

“በጣም ደስተኛ ነበርኩ፤ ምክንያቱም በፕሪምየር ሊግ ደረጃ ስጫወት ለመጀመሪያዬ ጊዜ ስለነበርና ሊጉንም ስለማላውቀው ከእኔ እንዲህ ያለ አበረታች የሚባል አቋም ይታያል ብዬ አልጠበቅኩም ነበርና በእዚህ ሊግ ደረጃ ፈፅሞ ባላሳብኩበት ሰዓት በመጫወቴ እና ከዛ የበለጠም ደግሞ በጣም በምወደው እና ሳደንቀው በነበረ ክለብ ውስጥ ስለተጫወትኩም ጭምር ነው ልደሰት የቻልኩት”፡፡

በዘንድሮው የውድድር ዘመን ለኢትዮጵያ ቡና ምርጥ የሚባል ብቃቴን እያበረከትኩ ነው ብሎ እያሰበ እንደሆነ

“በፍፁም፤ መቼ ኳሱን መጫወት ጀመርኩና፤ እንዳለኝ አቅምም ገና የውስጤን አውጥቼም አልተጫወትኩም፤ ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ ግን በጣም ምርጡን ዊሊያምን እንደምትመለከቱት ተስፋን ሰንቂያለው”፡፡

ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴን ግን እያደረግክ ነው?

“አዎን፤ ይሄን ከፈጣሪ እርዳታ ጋር አሁን ላይ እውን እያደረግኩት ነው፤ ቡናን ዘንድሮ ስቀላቀል በሀሳብ ደረጃ አስቀድሜ የቡድኑ ደጋፊም ስለነበርኩ በቀጣዮቹ ወቅት እዚህ ስፍራ ላይ ልገኝ እችላለው ብዬ ስንቅን ሰነቅኩኝ እንጂ እዚህ ደረጃ ላይ እደርሳለው ብዬ ፈፅሞም አልጠበቅኩምና አካሄዴ ተስፋ ሰጪ ነው”፡፡

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ አቡበከር ናስር የውድድር ዘመኑ ኮከብ ተጨዋች ተብሎ ስለመሸለሙ

“በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ አቡበከር ያገኛቸው አጠቃላይ ሽልማቶች የሚያንሰው እንጂ የሚበዛበት አይደለም፤ ይህ ወጣት ዘንድሮ ልዩና ክስተት የሆነም ተጨዋች ነው፤ በአንድ የውድድር ዘመን ያውም በ13 ክለቦች መካከል በተካሄደ ውድድር ላይ 29 ግቦችን ለማስቆጠር መቻሉና ለአራት ጊዜም ያህል ሀትሪክ መስራቱ ከዛ ውጪም ደግሞ አንድ አንድ የሚያስቆጥራቸው ግቦች ፈፅሞ የማይታመኑ መሆናቸውን ስትመለከት የውድድር ዘመኑ ኮከብ ተጨዋች ተብሎ መሸለሙ የሚገባው ሆኖ ነው ያገኘሁት”፡፡

በቤቲኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ከአቡበከር ውጪ ሌላውስ የአንተ ምርጡ ተጨዋች

“ከእኛ ክለብ ልውጣና የሰበታ ከተማው መስዑድ መሐመድ አጨዋወት በጣም ስቦኛል፤ መስዑድ ከችሎታው ባሻገር ያለው ዲስፕሊንም የሚገርም ነው፤ ከዛ ውጪ የሐዋሳ ከተማ ቆይታችን ላይም ምንም እንኳን የአንድ ቡድን ተጨዋች ባንሆንም ዶርማችን አንድ ስለነበርና ስለምንገናኝም ከእኔ ችሎታ በመነሳት ለወደፊቱ የኳስ ህይወቴ ጥሩ ምክሮችንም ሰጥቶኛልና ያን ተግባራዊ ለማድረግ እፈልጋለው፤ በዚሁ አጋጣሚም መስዑድን ለማመስገን እፈልጋለውኝ”፡፡

የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የኮከብ ተጨዋችነትን ክብር አቡበከር ናስር አግኝቷል፤ ቀጣዩ ተረኛ እኔ መሆን አለብኝ በሚል አልጓጓህም

“ስሜቱማ አለ፤ እንዴት አልጓጓም፤ ይሄን በቀጣዩ ጊዜም የማሳካው ይሆናል”፡፡

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ለወጣት ተጨዋቾች የመሰለፍ እድልን ስለመስጠቱና የመጪው ዘመን ቡድኑ ከዘንድሮው የበለጠ ይሆን እንደሆነ

“ኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌን በደንብ የሚሰማውና የሚያዳምጠው ከሆነ ከዘንድሮ የበለጠውን ኢትዮጵያ ቡናን በመጪው የውድድር ዘመን ላይ የምንመለከተው ይሆናል፤ ቡና ከዚህ ዘመን የሚሻለውንና  ውጤት የሚያመጣም ቡድን ለመስራት አሰልጣኙ የሚፈልጋቸውን ተጨዋቾችም ቢሮ አካባቢ የሚገኙት ሰዎች በደንብ ተረድተዉት ካመጡለት አሰልጣኙ ጥሩ ነገር ይሰራል፤ ያ ካልሆነ ነው ጉዳቱ፤ ለወጣት ተጨዋቾች የመሰለፍ እድልን ከመስጠት ጋር በተያያዘ ቡድናችን  በእዚህ ዓመት የተወዳደረው በአብዛኛው ወጣት ተጨዋቾችን ይዞ ነው፤ በዚህ ደረጃም ሊጉን ተካፍሎ በሁለተኝነት ውድድሩን ማጠናቀቁም ሊያስመሰግነው የሚገባውም ነው፤ ከዛ ውጪ የእኛ ቡድን በጀመረው ለታዳጊ ወጣት ተጨዋቾች የመሰለፍ እድልን በመስጠቱም ነው ሌሎችም ክለቦች እየደፈሩ በመምጣት ለወጣት ተጨዋቾች በሩ ሊከፈትም የቻለው፤ እኛ ክለብ ጋር ለእኔና ለሬድዋን ናስር የመሰለፍ እድል ሲሰጥ ሌሎችም ጋር በስፋት ይሄ ነገር ታየ፤ ስለዚህም ወጣት ተጨዋቾች ጋር ጥሩ አቅም ስላለ ይሄ አሰራር ዘንድሮ በመታየቱ በጣም ነው ደስ ያለኝ”፡፡

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና አቡበከር ናስርን በመጪው ዓመት ካጣ

“አቡኪ ለኢትዮጵያ ቡና ዘንድሮ የሰጠውን ግልጋሎት ሁላችንም የምናውቀው ነው፤ ተፅህኖ ፈጣሪ ተጨዋችም ነው፤ እሱ ቢኖርልን የበለጠ ይጠቅመናል፤ ከሌለም ኢትዮጵያ ቡና እንደ ቡድን የሚንቀሳቀስ ክለብ ስለሆነና አቡኪም በእዛ ውስጥ ተሳትፎን አድርጎ ግብ ሲያስቆጥርልን የነበረ ተጨዋች ስለሆነም እሱን ሊተካና ሊቃረበው የሚችል ተጨዋችን ነው ወደ ቡድናችን እንዲመጣ አድርገን የተሻለ ነገርን ልንሰራ የሚገባን”፡፡

ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ እንደተጠናቀቀ ወደየት ተጓዝክ?

“ወደ ሐረር ቤተሰቦቼ ጋር ነው የሄድኩት፤ እዛም እንዳመራው አላረፍኩም፤ ምክንያቱም ፈጣሪ ብሎ ለኢትዮጵያ ዋናው ወይንም ደግሞ የተስፋው ብሔራዊ ቡድን ላይ ጥሪ ከተደረገልኝ በሚል እያሰብኩም ነው ራሴን ዝግጁ አድርጌ ለማቅረብ ልምምድን እየሰራውኝ ያለሁት”፡፡

በእግር ኳሱ ምን ማሻሻል አለብህ?

“ብዙ ነገሮች አሉ፤ ከእነዛ ውስጥ እንደ አማካይ ስፍራ ተጨዋችነቴ ልጠቅሰው የምፈልገው ጎል ጋር በመድረሱ የተሻልኩ ተጨዋች ሆኜ ተደጋጋሚ  ጎልን አላስቆጥርም፤ በሜዳ ላይ ይህን ክፍተቴን በማሻሻል ቡናን ጠቅሜ ራሴን መጥቀም እፈልጋለው”፡፡

ስለ አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ

“ስለ እሱ በእኔ አቅም ማውራት በጣም ይከብዳል፤ አንድ ነገርን ብቻ ልበልና ግን ላብቃ ምርጥ አባታችን እንደሆነና የተለየ ሰው እንደሆነ”፡፡

ስለ ቀጣይ ጊዜ እልሙ

“ዓላህ ካለ የኳስ ህይወቴ በዚህ በሀገር ውስጥ ደረጃ ብቻ ተወስኖ እንዲቀር አልፈልግም፤ በትንሽ ጊዜ ውስጥ ወደ ውጪ ወጥቶ መጫወትን እፈልጋለው፤ ከዛ በተጨማሪ ደግሞ ሀገሬን ወክዬም መጫወትን እፈልጋለውና ለዛ ደረጃ ለመብቃት በርትቼ እሰራለው”፡፡

በኮንፌዴሬሽን ካፕ ቡድናቸው ስለሚኖረው የመጪው ዓመት ተሳትፎ

“ኢትዮጵያ ቡና ለውድድሩ የሚጓዘው ተጫውቶ ለመመለስ ብቻ አይደለም፤ አሁን የያዘውን አጨዋወት ለሌሎች ሀገራት ማሳየት ይፈልጋል፤ ከዛ ውጪ ዋንኛ ዓላማውም በእዚህ በያዘው የጨዋታ እንቅስቃሴ ውስጥ ሆኖ ከዚህ ቀደም በሀገራችን ክለቦች የኢንተርናሽናል የውድድር መድረክ ላይ ተይዞ ከነበረው የሪከርድ ውጤት ከፍ ባለ ስፍራም መገኘት መቻልና ከተቻለም እስከ ፍፃሜ ድረስም ለመሄድ ነውና ይሄን ለማሳካት ጥረትን እናደርጋለን”፡፡

በባህርማዶ ስለሚደግፋቸው ቡድኖች

“የማንቸስተር ሲቲ ደጋፊ ነኝ፤ ባርሴሎናንም እደግፋለው”፡፡

በሻምፒዮንስ ሊጉ ፍፃሜ የማንቸስተር ሲቲ በቼልሲ መሸነፍ

“ውጤቱ በእዚህ መልኩ ይጠናቀቃል ብዬ ፈፅሞ አልጠበቅኩም ነበር፤ ሲቲ ያሸንፋል ብዬ ነው የተሸነፈው፤ ሲቲ በመሸነፉ ደብሮኛል፤ ሆኖም ግን በዕለቱ ኳስን ስትመለከት ከእነሱ ትምህርትን ለመውሰድም ጭምር ስለሆነ የተሻላን ቡድን ማድነቅ አለብህና እኔም ቼልሲን አድንቄያለው”፡፡

ከባህር ማዶ የሚያደንቀው ተጨዋች

“የማንቸስተር ሲቲው እና የአልጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ማህሬዝ አድናቂ ነኝ፤ አጨዋወቱ በጣም ይመቸኛል”፡፡

እናጠቃል

“ቤተሰቦቼን፣ እስካሁን ያሰለጠኑኝን አሰልጣኞች፤ አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌንና የኮቺንግ ስታፉን እንደዚሁም ደግሞ ደጋፊዎቻችንና የቡድን አጋር ጓደኞቼን ከጨዋታ ወደ ጨዋታ እንድሻሻል እያደረጉልኝ ላለው ማበረታታት ምስጋናን ላቀርብላቸው እፈልጋለው፤ ይህን ካልኩ ሌላ ልጨምረው የምፈልገው ነገር ቢኖር የቡድናችን ስኬታማና የዘንድሮው ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ኮከቡ ተጨዋች አቡበከር ናስር ወደ አውሮፓ ክለቦች ደረጃ ሄዶ ቢጫወት በጣም ደስ እንደሚለኝ ነው”፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P