በመሸሻ ወልዴ /G.BOYS/
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአንደኛው ዙር ጨዋታዎች ነገ እሁድ፣ ሰኞና ማክሰኞ በሚደረጉት ግጥሚያዎች የሚጠናቀቁ ሲሆን ተስተካካይ ጨዋታዎች ያላቸው ቡድኖች ደግሞ ከሳምንቱ አጋማሽ ጀምሮ በሚያከናውኗቸው ጨዋታ ውድድሩ ይጠናቀቃል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 16 ክለቦችን እያሳተፈ ባለው የእስካሁኑ ውድድርም ሊጉን አሁን ላይ ቅ/ጊዮርጊስ በ—–ነጥብ እና…..የግብ ክፍያን በመያዝ እየመራ ሲሆን የተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው መቐሌ 70 እንደርታ በተመሳሳይ ነጥብ እና በ…..ግብ ክፍያ እንደዚሁም ደግሞ ሲዳማ ቡናም በተመሳሳይ ነጥብ እና በ…..ግብ ክፍያ በጎል ተበልጠው ተከታዩን ስፍራ ሊይዙ ችለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዘንድሮ የውድድር ተሳትፎ ክለቦች በተቀራረበ ነጥብ ላይ በሚገኙበት የአሁን ሰዓት ሁለት የተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው መቐሌ 70 እንደርታ ተከታታይ ድሎችን እያስመዘገበ እና በነጥብም መሪዎቹን ክለቦች የተቀላቀለበት አጋጣሚ ለሻምፒዮናነት ለሚኖረው ጉዞ ለብዙዎቹ አስፈሪ የሆነባቸው ሲሆን የክለቡ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋችና በሊጉም ምርጥ የሚባል ብቃቱን እያሳየ የሚገኘው እና በብዙዎቹም ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን እያተረፈ ያለው አማኑኤል ገ/ሚካኤልም ለክለቡ ተከታታይ ጨዋታዎች የድል ጎሎችን እያስቆጠረ በመሆኑ የእሱም ጉዞ ለክለቡ ሻምፒዮናነት ከሚያደርገው ጥረት ባሻገር በወደፊቱ ጉዞውም ያለውን ብቃት ይዞ ከቀጠለ የሀገሪቱ ኮከብ ተጨዋች ወይንም ደግሞ የኮከብ ግብ አግቢ ለመሆንም የሚችልበት ዕድሉ ስለሚኖረው የተጨዋቹ በጥሩ ብቃት ላይ መገኘት አስፈሪ የሆነባቸውም አሉ፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአንደኛው ዙር ላይ በርካታ ክለቦች በተቀራረበ ነጥብ ላይ በመገኘት ውድድሩን ሊፈፅሙ ከጫፍ በደረሱበት ሰዓት በወራጅ ቀጠናውም ብዙ ክለቦች በነጥብ ተጠጋግተው ይገኛል፤ ይሄ ውጤት በመመዝገቡም የ16ቱ ክለቦች የሁለተኛው ዙር የሊግ ውድድር ከወዲሁ በከፍተኛ ሁኔታ በጉጉት እየተጠበቀም ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛው ዙር ውድድር ሲጀመር በርካታ ክለቦች ቡድናቸውን ሊያጠናክርላቸው የሚችሉ በርካታ ተጨዋቾችን ስለሚያስፈርሙ ውድድሩ ትኩረትን መሳቡ የማይቀር ሲሆን የሊጉን ዋንጫ ማን ያነሳል? የትኞቹ ክለቦችስ ከሊጉ ይወርዳሉ የሚለውን ምላሽ ይሰጥበታል፡፡