Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ኢትዮጵያ ቡና ላይ ጎል ሳስቆጥር የተደሰትኩት ከክለቡ እንድለቅ የተደረገበት ምክንያት አግባብ ስላልሆነ ነው” ቃልኪዳን ዘላለም /ወላይታ ድቻ/

 

ለወላይታ ድቻ በመጫወት በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ጥሩ አጀማመርን አሳይቷል፤ ለክለቡ እየተሳተፈ ካለባቸው ጨዋታዎች ውስጥም በቀድሞ ክለቦቹ ኢትዮጵያ ቡና ላይና ሰበታ ከተማ ቡድኖች ላይ ግቦችንም ሊያስቆጥር ችሏል፤ ወጣትና ወደፊት ከፍተኛ ተስፋ የተጣለበት እግር ኳስ ተጨዋች ነው፤ ይህን ተጨዋች ሊግ ስፖርት ጋዜጣ ከታዳጊነት ዕድሜው አንስቶ ስለምታውቀውና ከጨዋታ ወደ ጨዋታም ሲጓዝ በየዓመቱ ከፍተኛ ለውጦችንም ልትመለክበት ስለቻለች ተጨዋቹን ከኳስ ህይወቱ ጋር በተያያዘና ለሊጉ መሪ ወላይታ ድቻም በአሁን ሰዓት ላይ እየሰጠ ስላለው ግልጋሎት እንደዚሁም ከክለቡ ጋር በተያያዘም በጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አማካኝነት ጥያቄን አቅርባለት ምላሹን በሚከተለው መልኩ ሰጥቷታል፡፡

ሊግ፡- በቅድሚያ አንተን ሊያውቁህ ለሚፈልጉ ሰዎች ራስህን ብታስተዋውቅ?

ቃልኪዳን ዘላለም እባላለው፤ ተወልጄ ያደግኩት በልደታ ክፍለ ከተማ ውስጥ ነው፤ ከህፃንነት ዕድሜዬ አንስቶም የምወደውን እግር ኳስ በመጫወት በአሁን ሰዓት ላይ በእዚሁ ሙያ ውስጥ እገኛለው፡፡

ሊግ፡-የሕፃንነት ዕድሜህ ላይ የት ነበር ኳስን ተጫውተህ ያደግከው?

ቃልኪዳን፡- በአካባቢያችን የሚገኝ ብሪሞ ሜዳ አለ፤ እዛም ነበር ተጫውቼ ያደግኩት፡፡

ሊግ፡- በእዛን ወቅት ኳስን ስትጫወት ተምሳሌት ያደረግከው ተጨዋች ነበር?

ቃልኪዳን፡- በእኛ ጊዜ ስምና ዝና ያለው ተጨዋች ስላልነበር ሞዴል /ተምሳሌት/ ያደረግኩት ተጨዋች ማንም አልነበረም፤ ከዛ ይልቅ ግን በሀገር ደረጃ የሚጫወቱ ጥሩ ተጨዋቾች ነበሩና እነሱን በማድነቅ ነው ያደግኩት፡፡

ሊግ፡- ለምሳሌ የትኞቹን ተጨዋቾች ማድነቅ ቻልክ?

ቃልኪዳን፡- ብዙ ነበሩ፤ ከእነዛም መካከል ሳላህዲን ሰይድ፣ ሽመልስ በቀለና አዳነ ግርማ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ሊግ፡- ለመጀመሪያ ጊዜ በክለብ ደረጃ የተጫወትከው ለማን ቡድን ነው? እንዴትስ ወደ ቡድኑ አመራህ?

ቃልኪዳን፡- በክለብ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጫወትኩበት ክለብ የኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ ነው፤ እዚህ የተጫወትኩትም በወጣት ቡድን ደረጃ ነው፤ በዋናው ቡድን ደረጃ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጫወትኩት ለኢትዮጵያ ቡና ነው፡፡

ሊግ፡- እግር ኳስን በፕሮጀክት ደረጃስ ተጫውተህ አልፈሃል?

ቃልኪዳን፡- አዎን፤ በዛ ደረጃ ተጫውቼ ስላለፍኩም ነው ወደ ክለብ ተጫዋችነት ልሸጋገር የቻልኩት፤ የተጫወትኩበት የክለብ ስምም በኢንስትራክተር  ሰላም ዘርሃይ ይመራ የነበረውና በመገናኛ 24 ሜዳ ላይ ይሰለጥን የነበረው  ኤስ ዋይ ጂ የሚባለው የታዳጊ ፕሮጀክት ቡድን ነው፤ በእዚህ ፕሮጀክት ቡድን ውስጥ ስጫወትም ነው የወጣቶች አካዳሚ ቡድን አይተውኝ ሊወስዱኝ የቻሉት፡፡

ሊግ፡- ወደ ኢትዮጵያ ቡናም ማምራትህ ይታወሳል፤ የነበረህ ቆይታህ ምን ይመስላል?

ቃልኪዳን፡- አዎን፤ ከኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ የሶስት ዓመታት ቆይታዬ በኋላ በቀጣይነት ልጫወት ያመራሁበት ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ነበር፤ በአሰልጣኝ እድሉ ደረጀና ዮሴፍ ተስፋዬ ጊዜም ነበር በተስፋ ቡድን ደረጃ ልጫወት የቻልኩት፤ በኋላ ላይም ወደ ዋናው ቡድን ካደግኩ በኋላ አሰልጣኝ ዲዲየር ጎሜዝ ቡድናችንን ሲረከብ አረንጓዴ ትሴራ ይሰራለት ብሎ የዋናውን ቡድን እንድቀላቀል አደረገኝ፤ የቡና አጀማመሬና ቆይታዬ ጥሩ ነበር፤ ክለቡንም በጣም ነበር የምወደው፤ በተስፋ ቡድን ደረጃ ላይ በነበርኩበት ሰዓት ላይም በየሁለት ጨዋታዎች 3 ጎሎችን አስቆጥር ነበር፤ በኋላ ላይ ግን የዋናውን ቡድን በደንብ መጥቀም እየቻልኩ ከክለቡ ጋር እንድለያይ ስደረግ በጣም ነው ላዝን የቻልኩት፡፡

ሊግ፡-ለኢትዮጵያ ቡና የዋናው ቡድን የመጫወት አቅሙ ነበረኝ እያልክ ነው?

ቃልኪዳን፡- አዎን፤ አሁንም ደግሜ መናገር እፈልጋለው፤ አቅሙ እያለኝና መጫወትም እየቻልኩ ነው ከክለቡ ጋር እንድለያይ የተደረግኩት፡፡

ሊግ፡- ከክለቡ ጋር ለመለያየትህ በምክንያትነት የምታነሳው ጉዳይ ምንድን ነበር?

ቃልኪዳን፡- ምንም አይነት በቂ ምክንያት ሳይኖር ነው በክለቡ ውስጥ በነበሩትና አሁን ላይ ስማቸውን መጥራት በማልፈልጋቸው  ጥሩ ያልሆኑ ሰዎች አማካኝነት ቡድኑን እንድለቅ የተደረግኩት፡፡

ሊግ፡- ወላይታ ድቻ ከኢትዮጵያ ቡና ባደረገው  ጨዋታ የድሉን ግብ በቀድሞ ቡድንህ ላይ ስታስቆጥር ደስታህ ለየት ያለ ነበር፤ እንደ በቀል ቆጥሮት ነው በእዛ መልኩ ሊደሰት የቻለው ያሉክ አሉ?

ቃልኪዳን፡- በፍፁም፤ ቡናን እንዴት አድርጌ ነው የምበቀለው፤ ክለቡን እኮ በጣም ነው የምወደው፤ ያን ዕለት ደስታዬን ልዩ ያደረገው ከክለቡ የተለያየሁበት መንገድ ትክክለኛና አግባብ ያልሆነ ነው፤ ለቡድኑ የመጫወትም አቅሙና ብቃት አለኝ ለማለት እንጂ ከሌላ ጉዳይ ጋር ፈፅሞ የሚያያዝ አይደለም፡፡

ሊግ፡- ከኢትዮጵያ ቡና ቆይታ በኋላ ወደ ደደቢት ቡድንም ተጉዘህ ነበር፤ በዛ የነበረህ ቆይታስ ምን መልክ የነበረው ነው?

ቃልኪዳን፡- ደደቢት ስገባ ከሲቲ ካፕ ጀምሮ ጥሩ ተሳትፎን እያደረግኩኝ ነበር፤ ወቅቱ ኮሮና የገባበትም ጊዜ ነበር፣ በመቀጠልም ጦርነቱ ሲመጣና ነገሮች ምቹ ሳይሆኑልኝ ሲቀር ለተወሰበኋላ ላይ ስላልሆነና

ሊግ፡- አምና ለሰበታ ከተማ ተጫወትክ፤ ዘንድሮ ደግሞ ወደ ወላይታ ድቻ በመቀላቀል እየተጫወትክ ነው፤ ስለ ጉዞዎችህ ምን ትላለህ?

ቃልኪዳን፡-ሰበታ ከተማን በኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ጊዜ ስቀላቀል ጥሩ ቆይታ ነበረኝ፤ በእሱ ስር ተጨዋች ሆኜም ስላሳለፍኩና ልሰራ በመቻሌም በጣም ደስተኛ ነበርኩ፤ ከእዚህ ክለብ ቆይታ በኋላ ደግሞ ያመራሁት በክረምቱ ወራት ወደ ወላይታ ድቻ ነው፤ አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ምህረትም ነው ወደ ቡድኑ ያስመጣኝ በእዚህ አጋጣሚ ይሄ አሰልጣኝ እኔን ከማምጣት ጀምሮ ለቡድኑም በማሰለፍ እየተጠቀመብኝ ስለሆነም ላመሰግነው እፈልጋለው፡፡

ሊግ፡- ወላይታ ድቻ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉን በመምራት ላይ ነው የሚገኘው፤ የእስካሁን አቋማችሁን እንዴት ተመለከትከው?

ቃልኪዳን፡-ወላይታ ድቻ በመጀመሪያ ደረጃ ጥሩ ቡድንና በትላልቅ ክለቦች ደረጃ የሚመደብ ጠንካራ ቡድን ነው፤ የሊጉን አጀማመራችን ሳየውም ጥሩ ነው፤ ካደረግናቸው አምስት ጨዋታዎች ውስጥ አራቱን ማሸነፍ ችለናል፤ ለእዚህ ስኬታማነታችንም በዋናነት የረዳን እንደ ቡድን መጫወት መቻላችንና የምናገኛቸውን የግብ አጋጣሚዎችንም የምንጠቀም መሆናችንም ነው፡፡

ሊግ፡- በወላይታ ድቻ የእስካሁን ጨዋታ በክፍተት ደረጃ የተመለከትከውስ ነገር አለ?

ቃልኪዳን፡- ስለ ክፍተት ጎናችን አለ ማለት ይከብዳል፤ እስካሁን ጥሩ ጎኑ ብቻ ነው የታየኝ፡፡

ሊግ፡- በውድድር ዘመኑ ምን ውጤትን ማምጣት ነው ያለማችሁት?

ቃልኪዳን፡- አሁን ላይ ሊጉን እየመራንም ስለሆነ የእኛ እቅድና ግባችን ወላይታን በሚመጥን ደረጃ ከፍ ባለ ስፍራ ላይ ማስቀመጥ መቻል ነው፡፡

ሊግ፡- እስከ ሻምፒዮናነት ማለት ነው?

ቃልኪዳን፡- ዋናው ነገር ከፊታችን የምናደርጋቸውን ግጥሚያዎች እንደ ጥሎ ማለፍ ፍልሚያ በመመልከት ከስር ከስር እያሸነፍን ተጉዘን የሚመጣውን ውጤት መጠበቅ ነው፤ ከእነዛ ውስጥ አንዱ ደግሞ ወይ ሻምፒዮና መሆን መቻልም ነውና እሱንም ከፈጣሪ እርዳታ ጋር ለማሳካት ጥረትን እናደርጋለን፡፡

ሊግ፡- በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ካደረጋችሁት ግጥሚያ ለአንተ የቱ ምርጡ ነበር?

ቃልኪዳን፡- ከሰበታ ከተማ ጋር የነበረንን ነው በቀዳሚነት የማስቀምጠው፤ ጥሩ ነበርን ከመመራት ተነስተን ለማሸነፍ መቻላችን የእኛን ጥንካሬ አጉልቶ ያሳያልና ያ ጨዋታ የተለየ ስሜትን ፈጥሮብኛል፡፡

ሊግ፡-ወላይታ ድቻ ሊጉን እየመራ ነው፤ የእናንተ የዋንጫ ተፎካካሪ ማን ይሆናል?

ቃልኪዳን፡- ሁሉም ክለብ ጠንካራ ስለሆነ የእኛን ተፎካካሪ ቡድን አሁን ላይ ማወቅ ይከብዳል፤ ሊጉ ገና የማራቶን ያህል ቆይታ አለው፤ ዘንድሮ ቡድኖች ተጠናክረዋልና ሁሉም ነገር የሚታወቀው ወደ በኋላ ላይ ነው፡፡

ሊግ፡- የአምናውን ሻምፒዮና ፋሲል ከነማን ዛሬ ትፋለማላችሁ፤ ጨዋታው ምን መልክ ይኖረዋል? ምን ውጤትንስ ትጠብቃለህ?

ቃልኪዳን፡- ከፋሲል ከነማ ጋር የሚኖረን ጨዋታ የወደፊቱን የውጤት እልውናችንን በደንብ አድርገን የምንመለከትበት ነው፤ ሁለታችን ጥሩም ጨዋታ እናሳያለን፤ ግጥሚያውን እኛ እንደምናሸንፍም እምነቴ ነው፡፡

ሊግ፡- ቤትኪንጉን ከዓምናው አንፃር ስትመለከተው?

ቃልኪዳን፡- ከአምናው መሻሻል አለው፤ አንድ ደረጃም የሀገራችንን እግር ኳስ ከፍ አደርጎታል፡፡

ሊግ፡- በወላይታ ድቻ በሚኖረው ቆይታው ለቡድኑ ምን አይነት ጥቅምን ሊሰጠው እንዳሰበ?

ቃልኪዳን፡- ለእዚህ የመጫወት እድሉን ላስገኘልኝ ክለብ አቅሜን ሳልሰስት ነው በየግጥሚያዎቹ ላይ ከእኔ የሚጠበቀውን ብቃት በማሳየት ለውጤት ላበቃው የተዘጋጀሁት፤ ይሄም ይሳካልኛልም ብዬ አስቤያለው፡፡

ሊግ፡- ስለ ቀጣይ ጊዜ የኳስ እልምህ ምን አልክ?

ቃልኪዳን፡- ለብሔራዊ ቡድን በመመረጥ ሀገሬን ማገልገል እፈልጋለው፤ ከዛ በኋላም ነው ወደ ውጪ ሀገር በመውጣት ስለመጫወት የማስበው፡፡

ሊግ፡- በመጨረሻ….?

ቃልኪዳን፡- ዛሬ ላይ በእግር ኳሱ እዚህ ደረጃ ላይ እንድደርስ የብዙ ሰዎች አስተዋፅኦ አለበት፤ ከሁሉ አስቀድሜ ፈጣሪዬንና ቤተሰቦቼን አመሰግናለው፤ ሲቀጥል በፕሮጀክት ደረጃ ያሰለጠነችኝ ኢንስትራክተር ሰላም ዘርሀይን፤ በክለብ ደረጃ ያሰለጠኑኝን እድሉ ደረጄና ዮሴፍ ተስፋዬን፣ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱንና አሁን ወደ ወላይታ ድቻ በማምጣት የመጫወት እድሉን የፈጠረልኝን ፀጋዬ ኪዳነ ምህረትን ከልብ አድርጌ ማመስገን እፈልጋለውኝ፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P