Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

ዝነኛው ሙሉጌታ ከበደን ካፈራችሁ ደሴ በመገኘት ጥሩ ችሎታውን እያንፀባረቀ ያለው ተጨዋች ፍፁም ዓለሙ (ባህር ዳር ከተማ)

በመሸሻ ወልዴ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የተጨዋችነት ዘመን ቆይታው ለፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድን በጥሩ መልኩ ተጫውቶ አሳልፏል፤ በዘንድሮው የውድድር ዘመንም ለአዲሱ ክለቡ ባህር ዳር ከተማም በመጫወት ጥሩና ስኬታማ የሚባልንም የውድድር ዘመን በማሳለፍ ላይ ይገኛል፤ ከቁመቱ አጠር ብሎ ወደ ሜዳ ሲገባ ግን ምንም አይነት የፍራቻ ስሜት ሳይታይበት ኳስዋን በፈለገችው መንገድ ሲያንሸራሽራትና ሲያንከባልላት እንደዚሁም ደግሞ በሚፈልገው መልኩም ከጓደኞቹ ጋር የአንድ ሁለት ቅብብልን በማድረግና ጎል ለማስቆጠርም ያለውን ፍጥነት በመጠቀም ወደ ተቃራኒ ቡድን የሜዳ ክልል በማምራት ውጤታማነቱን እያሳየ ያለው ይሄ ተጨዋች ፍፁም ዓለሙ ሲባል በእዚህ ዓመት ለባህር ዳር ከተማ ክለቡም ከወዲሁ በፕሪምየር ሊጉ ጥሩ እንቅስቃሴ ከማሳየቱ ባሻገር በእስካሁኑ የቡድኑ ጨዋታም 9 ያህል ጎሎችንም አስቆጥሮ ቡድኑን ከጓደኞቹ ጋር ውጤታማም እያደረገው ይገኛል፡፡
የባህርዳር ከተማ ክለብ በፕሪምየር ሊጉ እያደረጋቸው ባሉት የእስካሁን ጨዋታዎቹ በመሪው ክለብ ፋሲል ከነማ በሶስት ነጥብ ተበልጦ በአምስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን የቡድኑ ተጨዋች ፍፁም ዓለሙም ሊጉ ሲጠናቀቅ ክለባቸው የውድድሩ ዘመኑ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ከመጨረስ ባሻገር በሊጉ የደረጃው ሰንጠረዥም ከአንድ እስከ ሶስት ባለው ደረጃ ውስጥም ሆነው ለማጠናቀቅ የሚቻለቸውን ሁሉ ጥረት እንደሚያደርጉም እየተናገረ ይገኛል፡፡
የሊግ ስፖርት ጋዜጣ ከእዚሁ የባህርዳር ከተማ ስኬታማ ተጨዋች ፍፁም ዓለሙ ጋር በእግር ኳሱ ዙሪያና ከእግር ኳሱም ወጣ ባሉ ጉዳዮች ላይ ረቡዕ በምሳ ሰዓት ላይ በአሁን ወቅት ለእረፍት ከሚገኝበት የደሴ ከተማ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ በቀጥታ ስልክ በመደወል ያናገረው ሲሆን ተጨዋቹም ለቀረቡለት ጥያቄዎች ሁሉ ምላሹን ሰጥቶናል፡፡ የመጀመሪያው ጥያቄያችንም የነበረው በአሁን ሰአት በዓለማችን ላይ ከፍተኛ ስጋት ለሆነው የኮሮና ቫይረስ ህብረተሰቡ እንዳይጋለጥ እና ጥንቃቄም እንዲያደርግ በሚል መመሪያ እና ማሳሰቢያም ተላልፏልና፤ እሱ ምንያህል እየተጠነቀቀ እንደሆነም ለማወቅ ነው፤ በእዚህ ሰዓት የት ነው ያለኸው? የትስ ነው የምትገኘው ብለን ነው የጠየቅነው…? የደሴው ልጅም ለጥያቄያችን እንደመሳቅ ብሎም የሰጠን ምላሽ “አሁን የምገኘው ከምወዳቸው ቤተሰቦቼ ጋር እቤቴ ውስጥ ሆኜ ነው፤ ከእነሱ ጋርም ቡናም በመጠጣት ላይ ነው የምገኘው” ሲልም ምላሹን ሰጥቶናል፡፡
ከእዚህ ተጨዋች ጋር ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ያቀረባቸው በርካታ ጥያቄዎችና ተጨዋቹም የሰጣቸው ምላሾች እንደሚከተሉትም ቀርበዋልና፤ ይከታተሏቸው፡፡
ሊግ፡- ኮሮና ቫይረስ የዓለም ስጋት ከመሆኑ ባሻገር ወደ ኢትዮጵያም ገብቷል፤ ይህን መጀመሪያ ላይ ስትሰማ ምን አልክ? ምን ስሜትስ ተሰማህ?
ፍፁም፡- የኮሮና ቫይረስ በዓለም በሚገኙ በርካታ ሀገራትም ሆነ ወደ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ መግባቱን ስሰማ በእውነት ልቤ በጣም ነበር የተሰበረው፤ ቫይረሱም ከባድ ስለሆነ እንደሰዉም በጣም ነው ያዘንኩት፤ ይሄ በመሆኑም አሁን ላይ እኛ ኢትዮያውያን ከወዲሁ ማድረግ ያለብን ነገር ቢኖር የእዚህ ቫይረስን ህመም ለመቀነስ እና እንዳይስፋፋም ለማድረግ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ የምንሰማቸውን ትክክለኛ መረጃዎች ተግባራዊ ማድረግ እና በቤት ውስጥ ቁጭ ብሎም ማሳለፍ ነው፤ ከዛም ባሻገር በዋናነትም ወደፈጣሪ በመቅረብም ለፈጣሪ ፀሎትን ማድረግም ተመራጩም መንገድ ነው፡፡
ሊግ፡- እንደ አንድ እግር ኳስ ተጨዋችነትህ ይሄን ኮሮና ቫይረስ ለመከላከል አንተስ ምን እያደረግክ ነው?
ፍፁም፡- ከመቐለ 70 እንደርታ ክለብ ጋር ከተጫወትን በኋላ በአጋጣሚ ለእረፍት ወደቤቴ መጥቼ ነበር፤ በኋላም ላይ የእዚህ ቫይረስ መምጣትና መስፋፋቱንም ስሰማ የአሁን ሰዓት ላይ በቤቴ በመቀመጥ እና ለቫይረሱም መከላከያ ናቸው የተባሉትን መመሪያዎችን በማክበርም ነው ጊዜዬን እያሳለፍኩ ያለሁት፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግም እንደ ሌሎች ሀገራት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተቋርጧል፤ ምን አልክ?
ፍፁም፡- ይሄ ቫይረስ በሃገራችን ብቻ ሳይሆን አስቀድሞ በዓለም ላይ የመጣ ስለሆነ ውድድሩ መቋረጡ በተለይ ደግሞ እንደ እኛ ላለና ብዙ ሰውም ለሚሰበሰብበት እና ለሚገናኝበት ማህበረሰብ ትልቅ አስተዋፅኦ ያለው ስለሆነም መቋረጡ የግድ እና ትክክለኛውም ጥሩ ውሳኔ ነው፡፡
ሊግ፡- አሁን ደግሞ ወደ እግር ኳሱም እናምራ የባህር ዳር ከተማ ተጨዋች ሆነህ በዘንድሮው የፕሪምየር ሊግ ውድድር ጥሩ ጊዜን እያሳለፍክ ይገኛል፤ ከዚህ በፊቱ አንፃር በእዚህ ዓመት በተሻለ አቋም ላይ ትገኛለህ ማለት ይቻላል?
ፍፁም፡- አዎን፤ በጣም በተሻለ ሁኔታ ላይ ነው የምገኘው፤ ምክንያቱም ዘንድሮ በርካታ ግቦችንም ለቡድኔ ከወዲሁ እያስቆጠርኩም ነው ያለሁትና፤ ይሄ ደግሞ በወቅታዊ አቋሜም ከዓመት ወደ ዓመት ስጓዝ ራሴንም እያሻሻልኩም እንደተጋዝኩ አመላክቶኛልና የውድድር አመቱን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በጥሩ ሁኔታም እያሳለፍኩት ነው የምገኘው፡፡
ሊግ፡- የፕሪምየር ሊጉ የእስካሁን ተሳትፎአችሁ ላይ አሁን የያዛችሁትን መልካም የሚባል ውጤት እናስመዘግባለን ብላችሁ ጠብቃችሁ ነበር?
ፍፁም፡- አዎን፤ ለዛም በምክንያትነት የምገልፀው ሁሌም ወደሜዳ ለማንኛውም ጨዋታ ስንገባ ለማሸነፍ ብቻ ስለምንጫወት ነው፤ በሊጉ እስካሁን በሜዳችን ላይ የነበሩንን 8 ጨዋታዎች ለማሸነፍ ችለናል፤ ይሄ በጣም ጥሩና የማይገኝም ውጤት ነው፤ ከዚ በኋላ ደግሞ ከሜዳ ውጪ ባሉን ጨዋታዎቻችንም ውጤታችንን እያስተካከልን የምንጓዝበት ውጤት ስለሚኖረን የእዚህ ዓመት ውጤታችን የአማረም ነው የሚሆነው፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የእዚህ አመት ተሳትፎአችሁ አስቆጪው ጨዋታችሁ የቱ ነው?
ፍፁም፡- አስቆጪው ጨዋታ በአዳማው የአበበ ቢቂላ ስቴድየም ከጅማ አባጅፋር ጋር ያደረግነው ነው፤ ይህን ፍልሚያም እኛ ማሸነፍ እንችል ነበር፤ ያም ሆኖ ግን ሳይሳካልንና እድለኛ ሳንሆን ቀርተን ግጥሚያውን በአቻ ውጤት አጠናቀነዋል፡፡
ሊግ፡- ባህር ዳር ከተማን የሊጉ ውድድር ሲጠናቀቅ በምን ውጤትና ደረጃ እንጠብቀው?
ፍፁም፡- የፕሪምየር ሊግ ውድድር አሁን ላይ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ፈጣሪ አጥፍቶልን ይጠብቀን እንጂ ቡድናችን ጥሩ ውጤት ለማምጣት በሚገባ ተዘጋጅቷል፡፡ የደረጃ ተፎካካሪም ይሆናል፡፡ ለእዛም ስንል ጠንክረን ልምምዳችንንም የምንሠራ ይሆናል፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እስካሁን ለባህር ዳር ከተማ 9 ግቦችን ለማስቆጠር ችለሃል፤ የከዚህ በፊቱ ከፍተኛ ግብህ ስንት ነበር….ከዚህ በኋላስ ሌላ ግቦች ይኖሩሃል?
ፍፁም፡- በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ከዚህ በፊት ስጫወት ያስቆጠርኩት ከፍተኛ ግብ ባለፈው ዓመት ለፋሲል ከነማ ስጫወት ያስቆጠርኩት 6 ግብ ነው፤ የእዚህ አመት ውድድር ላይ ግን ገና ከወዲሁ ውድድሩ ሳይጠናቀቅ 9 ግቦችን ያስቆጠርኩ በመሆኑና ከግብ አግቢነቱ በተጨማሪም በእንቅስቃሴው ደረጃም በጥሩ አቋምም ላይ ስላለሁኝ የሊጉ ውድድር የሚቀጥል ከሆነ በእርግጠኝነት ሌሎች ተጨማሪ ግቦች ይኖሩኛል፡፡
ሊግ፡- ከባህር ዳር ከተማ ደጋፊዎች ጋር አሁን ላይ ያለህ ትስስር ምን ይመስላል? ተመቹህ?
ፍፁም፡- የባህር ዳር ከተማ ደጋፊዎች በሜዳም ሆነ ከሜዳ ውጪ ሲያገኙኝ ከአንደበታቸው በማውጣት ለእኔ ያላቸውን ድጋፍና አድናቆት የሚገልፁልኝ በተለየ መልኩ ነው፤ ለዛም በጣም እንድወዳቸውም አድርጎኛል፤ እነሱ ምርጥ ደጋፊዎችም ናቸው፤ ልክ ቀደም ሲል እንደነበርኩበትም ክለብ ፋሲል ከነማ ደጋፊዎችም ሁሉ ቡድናቸውንም በጣም የሚወዱም ሆነው አግኝቼያቸዋለውምና ይህንን ስመለከት እነሱን ከመውደዴ ባሻገር ላመሰግናቸውም እወዳለው፡፡
ሊግ፡- ባህር ዳር ከተማን አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ በኃላፊነት እየመራው ይገኛል፤ ስለ እሱስ ምን ትላለህ?
ፍፁም፡- አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ በሙያ ቆይታው ከዚህ ቀደም የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ውስጥም ሆነ የብሄራዊ ቡድን ላይ በምክትል አሰልጣኝነት ሰርቶ ያሳለፈ በመሆኑ አሁን ወደ እኛ ሲመጣ ያ ልምዱ ጠቅሞት ለመጀመሪያ ጊዜ በፕሪምየር ሊግ ደረጃ እያሰለጠነ ያለውን በኋላ ቡድናችንን በጥሩ ሁኔታ እየመራው ይገኛል፤ ከዚህ በኋላም ከእኛ ጋር ጥሩ ተጉዞም በአበረታችነቱ አቻ የማይገኝለትም ውጤት ያስመዘግባልና ለዛም ከጎኑ ሆነን የምንረዳው ይሆናል፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ተሳትፎ በሜዳ ላይ ከምታሳያቸው ጥሩ እንቅስቃሴ በመነሳት ይሄ ልጅ ለዋልያዎቹ መመረጥ ነበረበት የሚሉ አካላቶች አሉ፤ አንተ ግን ለብሄራዊ ቡድናችን አልተመረጥክም በእዚህ ዙሪያ ምን ማለት ትችላለህ?
ፍፁም፡- በአሁን ሰዓት በጥሩ አቋም ላይ በምገኝበት ሰዓት ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን መመረጥ ብችል ኖሮ በጣም ደስ ይለኝ ነበር፤ ያም ሆኖ ግን አሰልጣኙ ለራሴ የጨዋታ ፍልስፍና ይሆኑኛል ያላቸውን ተጨዋቾች መርጧልና በእዚህ ዙሪያ እኔ የምለዉ ብዙ ነገር የለም፡፡ ከዛ ይልቅ ለዋልያዎቹ የተመረጡትን ተጨዋቾችንና ጓደኞቼን ሀገሬን ወክለው የሚጫወቱ በመሆኑ ለመመረጣቸው እንኳን ደስ አላቸው፤ ጥሩ ነገርንም ሀገሬንም ሆነ እነሱን እንዲገጥማቸውም ነው የምመኘው፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ውስጥ ተመራጭ ተጨዋች ለመሆን አልቻልክም፤ ቀጣዩ ጊዜስ የእኔ ይሆናል ብለህ ታስባለህ?
ፍፁም፡- እኔ እድሉን ለማግኘት ጠንክሬ እሰራለው፤ ስለመመረጥ መቻሌ ግን ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው፤ አሁን ላይ በእግር ኳሱ ጥሩ ጊዜን እያሳለፍኩ ነው፤ የራሴንም ብቃት ከአመት አመትም እያሻሻልኩ በመሆኑም እግዚአብሄር ፈቅዶ ለብሄራዊ ቡድን የመመረጥ እድሉን ካገኘው እርግጠኛ ሆኜ ለመናገር የምችለው ለሀገሬ ብዙ ነገሮችን እንደምሰራላት ነው፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ ውስጥ እያሳለፍክ ባለው የእግር ኳስ ተጨዋችነት ህይወት ደስተኛ ነህ?
ፍፁም፡- በጣም እንጂ! ዋናው ደስታዬም ችሎታዬን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻሻልኩ በመጓዜና በርካታ ግቦችንም ካለፈው ዓመት ጀምሮም እያስቆጠርኩ በመሆኔም ነው፤ ከዛ ሁሉ ይልቅ ደግሞ የእግር ኳስ ተጨዋች መሆን በራሱ ትልቅ መዝናኛና ከእርካታ በተጨማሪም እንጀራዬም እንደሆነ ያገኘሁበት ስፖርትም ስለሆነ ደስተኝነቴን ይበልጥ ጨምሮልኛል፡፡
ሊግ፡- በኳሱ ተከፍቼ አላውቅም እንዳትለኝ ብቻ….?
ፍፁም፡- እንዴት እልሃለሁ፤ አምና የፋሲል ከነማ ተጨዋች ሆኜ በመጨረሻው ቀን ላይ በተደረገው ጨዋታ ከሽረ እንደስላሴ ጋር ስንጫወት አቻ በመውጣታችን በእጃችን የገባውን ዋንጫ ለመቐለ 70 እንደርታ አሳልፈን ሰጥተን ነበርና በዛ በጣም ነው ያዘንኩት፤ በጣምም ነው የተከፋሁት፤ ያ ሀዘን ሁሌ ከውስጤም አይጠፋም፡፡
ሊግ፡- ፋሲል ከነማ አምና ለሻምፒዮናነት የተጫወተ ቡድን ነበር፤ ዘንድሮ ደግሞ በጥንካሬው ተጉዞ የሊጉ መሪ ለመሆን ችሏል፤ ከዚህ በመነሳት የአንተን ካለ ችሎታ አኳያ ከእዚህ ክለብ ለቅቀህ ወደ ባህር ዳር ከተማ ያመራህበትን ሁኔታ ብዙዎቹ በአነጋጋሪነቱ ይገልፁታል፤ ፋሲል ከነማን በምንና እንዴት ነበር ለመልቀቅ የቻልከው?
ፍፁም፡- ፋሲል ከነማ በእግር ኳስ ተጨዋችነቴ ለእኔ ጥሩና መልካም ጊዜን ያሳለፍኩበት የምወደው ቡድን ነው፤ ያም ሆኖ ግን በክረምቱ ወራት የውል ጊዜዬን እንዳጠናቀቅኩኝ ከክለቡ ጋር ለመቀጠል በሚያስችለው የደመወዝ አከፋፈል ላይ እኔና ቡድኑ ልንሰማማ ስላልቻልንና አለመግባባቶችም ስለነበሩ በእዛው ሳልቀጠል በመቅረት ለባህር ዳር ከተማ ፊርማዬን ላኖር ቻልኩ፤ ፋሲሎች ከእኔ ጋር መጀመሪያ ባይስማሙም በኋላ ላይ ደግሞ መልሰው እንስማማለን ጠብቀን ቢሉኝም የዝውውር መስኮቱ የዝውውር ጊዜው እየሄደም ነበርና ነው በመጨረሻም ወስኜ ለባህርዳር የፈረምኩት፡፡
ሊግ፡- ወደ ኢትዮጵያ እግር ኳስ የመጣኸው ደሴ ከተማ ውስጥ ተወልደህ በማደግ ነው፤ ደሴን እንዴት ትገልፃታለህ?
ፍፁም፡- ደሴ ምርጥ፣ እንግዳ ተቀባይ፣ እና የመቻቻልም ሀገር ናት፤ ከእሷ የማትወደውም ምንም አይነት ነገርም የለም፤ ሁሉም ነገሯም አስደሳች ነው፤ በእዚህች ውብ እና ምርጧም የትውልድ ከተማዬም ሁሌም በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ደሴ ብዙ ስመጥርና እውቅና ያላቸውን ተጨዋቾች አፍርታለች፤ አንተ ስለእነማን ታሪክ በደንብ ሰምተሃል? ሲጫወትስ የተመለከትከው ተጨዋች?
ፍፁም፡- የእኔ የትውልድ ከተማዬ ደሴ ስመጥር ተጨዋቾችን ያፈራች ሃገር ብትሆንም ሲጫወት የተመለከትኩት ተጨዋች ቢኖር ግን ዳንኤል አያሌው /አረቦንና/ ሌሎችን ጭምር ነው፡፡ ከዛ ውጪ ደግሞ ክልላችን ካፈራቻቸው የቀድሞ ተጨዋቾች መካከል ደግሞ ታሪካቸውን በመስማት በጣም የወደድኳቸው ተጨዋቾች ደግሞ ብዙ ናቸው፤ በዋናነትም ስለዝነኛው የቀድሞ እግር ኳስ ተጨዋች ስለ ሙልጌታ ከበደ የሰማሁት ነገር ትኩረትን የሚስብ ነበር፤ ሙልጌታ ከበደ በችሎታው ምርጥ ብቃት ያለው ተጨዋች ከመሆኑ ባሻገር የተጫወተባቸውን ክለቦችም ሆነ ሀገሩን ለውጤት ያበቃ ስለመሆኑ ከዛ ባሻገርም በተደጋጋሚ ጊዜም የኮከብ ተጨዋችነትንም የኮከብ ግብ አግቢነትንም ሽልማት ያገኘ ተጨዋች መሆኑን ያደመጥኩበት ሁኔታ አለና ከእዚህ ክልሌና ሀገሬም ካፈራችው ዝነኛ ተጨዋች የትውልድ ቦታ በተጨዋችነት የተገኘው መሆኔ በጣም ነው የሚያስደስተኝ፤ ከእሱ ሌላም ደሴ እነ ዮናታን በትረ፣ ብርሃኑ ፈይሳ /ፈየራን/ ሚካኤሌ ዋለልኝንም የመሳሰሉት ተጨዋቾችንም ያፈራች ምርጥ ሀገርም ስለሆነች እኔም የእነሱን ፈለግ ተከትዬም ክልሌን በደንብ ማስጠራት እፈልጋለውኝ፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስን መጫወት በጀመርክበት ሰዓት ማንን አድንቀህ ነው ያደግከው?
ፍፁም፡- የደሴ ከተማ በርካታ የእግር ኳስ ተጨዋቾችን ያፈራች ሀገር ብትሆንም የልጅነት እድሜዬ ላይ ሳለው በጣም አድንቄው ያደግኩት ተጨዋች ቢኖር ዳንኤል አያለውን /አረቦ/ ነው፤ የእሱ ችሎታ ያኔ በጣም ሳቢና አስገራሚም ነበር፤ ለእዛም ነው እሱን የእግር ኳስ ተጨዋችነት ህይወቴ ተምሳሌትና ሮል ሞዴሌም ያደረግኩት፡፡
ሊግ፡- በእዚያን ጊዜ የእግር ኳስ ተጨዋች ባትሆን ኖሮስ?
ፍፁም፡- በደሴ ከተማ ውስጥ በነበርኩበት ሰዓት ብዙ ጊዜ ታክሲዎች በሚበዙበት ሰፈርና አካባቢ ነበር የምውለው፤ ያኔ የእግር ኳስ ተጨዋች ባልሆን ኖሮ የምሆነው የታክሲ ሹፌር ነበር፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ በምታሳየው የጨዋታ እንቅስቃሴ የአዲስ አበባ ስፖርት አፍቃሪዎችን ጨምሮ የሌላ ክልልም ኳስ ተመልካቾች ለአንተ ከፍተኛ አድናቆት አላቸው፤ ለእዚህ ምላሹ አለህ?
ፍፁም፡- አዎን፤ በእግር ኳሱ አፍቃሪዎች ለሚሰጠኝ አድናቆት ሁሉ ለሁሉም እግዚአብሄር ያክብርልኝ ነው የምለው፤ ከዚህ በኋላ ደግሞ በሚኖረኝ የተጨዋችነት ዘመን ቆይታዬም የቻልኩትን ያህል ከፍተኛ ጥረት በማድረግና ለሃገሬም ብሄራዊ ቡድኑ በመመረጥ በችሎታዬ እነሡን ከማስደሰት ባሻገር ሃገሬንም ማገልገል እፈልጋለሁና ለዛ ያድርሰን ነው የምለው፡፡
ሊግ፡- በፋሲል ከነማ ለረጅም ጊዜያት 6 ቁጥርን ማሊያን ነበር የምታደርገው፤ ያም መለያህ ነበር፤ አሁን ደግሞ በአዲሱ ክለብህ 14 ቁጥርን ነው የምታደርገው፤ ለምን የማሊያ ቁጥርን ለውጥ አደረግክ?
ፍፁም፡- በፋሲል ከነማ የተጨዋችነት ቆይታዬ የ6 ቁጥርን ማሊያ የእውነትም በጣም ስለምወደው ነበር አጥልቄ እጫወት የነበረው፤ አሁን ወደ ባህር ዳር ከተማ ስገባ ደግሞ የእዚህ ማሊያ ቁጥር ቡድኑ ውስጥ አልመጣም ነበርና ለዛ ነው የ14 ቁጥርን የማደርገው፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመንህ ከገጠሙህ ውስጥም ሆነ አሁን ላይ የባህር ዳር ከተማ ተጨዋች ሆነህ በጣም የሚያዝናናህና የሚያስቅህ ተጨዋች ማን ነው?
ፍፁም፡- በፋሲል ከነማ ሳለው ጀማል ጣሰውና አምሳሉ ጥላሁን /ሳኛ/ ናቸው በጣም ያስቁኝና ያዝናኑኝ የነበሩት የአሁን ሰአት ላይ ደግሞ ሳምሶን ጥላሁን /ሳሚ ባሪያው/ በባህር ዳር ከተማ ክለብ የተጨዋችነት ቆይታዬ በጣሙን እያዝናናኝ ይገኛል፡፡
ሊግ፡- በአኩራፊነት ካጋጠሙህ ተጨዋቾች ውስጥስ…?
ፍፁም፡- አኩራፊ ተጨዋች ያጋጠመኝ የፋሲል ከነማ ተጨዋች በነበርኩበት ሰዓት ነው፤ እሱም ሙሉቀን ታሪኩ ነበር፤ አሁን ወደ ሲዳማ ቡና ገብቷል፤ ሙሉቀን ቶሎ በሻቂ እና አኩራፊም ተጨዋች ነበር፡፡
ሊግ፡- የአንተስ ባህሪህ ሲገለፅ…?
ፍፁም፡- በጣም ተናዳጅ እና እለኸኛ ነኝ፤ በተለይ ሜዳ ውስጥ፤ ከእዛ ውጪ ግን ሌሎች ብቻ ሳይሆኑ ራሴን ጨምሮም ስፎገር መሳቅንም የምወድ አይነት ተጨዋች ነኝ፡፡
ሊግ፡- በቤተሰባችሁ ውስጥ ስፖርተኛው አንተ ብቻ ነህ? ስንት ወንድምህ እህትስ አለህ? በምንስ ሙያ የተሰማሩ ናቸው?
ፍፁም፡- የእግር ኳስ ተጨዋቹና ስፖርተኛው አዎን እኔ ብቻ ነኝ፤ አንድ እህትም ብቻ ነው ያለኝ፤ እሷም አስተማሪ ነች፡፡
ሊግ፡- ውሃ አጣጪህን አግኝተሃል? ማንስ ትባላለች?
ፍፁም፡- አዎን፤ አግቼያለው፤ ስሟም ቅድስት ወልደ አምላክ ይባላል፤ ከእሷም ናታንሄም የሚባል አንድ ልጅም አለኝ፡፡
ሊግ፡- ከባለቤትህ ጋር የተዋወቅክበት መንገድ ምን ይመስል ነበር? እሷን እንዴትስ ትገልፃታለህ?
ፍፁም፡- ከባለቤቴ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ለመተዋወቅ የቻልነው የፋሲል ከነማ ክለብ ተጨዋች በነበርኩበት ሰዓት ጎንደር በሚገኘው ካምፓችን በአጋጣሚ ከእሷ ጋር ለመተያየት በመቻላችንና በኋላ ላይ ያለን ትውውቅም እየጠበቀ በመሄዱ በጣም ልንዋደድም በመቻላችን ነው፤ እሷን የምገልፅበት ሁኔታ በጣም ጥሩ ሰው ናት፤ ትዳር የሚሰጠውም ከፈጣሪም ነውና ያን ያሟላችም ናትና በጥሩ ሁኔታም አብሬያት እየኖርኩ ነው፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስን መጫወት ስትጀምር ከአንተ ጀርባ ሆነው ለዛሬው እዚህ ደረጃ ላይ መድረስህ አስተዋፅኦ ያደረጉልህ ሰዎች አሉ?
ፍፁም፡- በጣም እንጂ፤ ከፈጣሪዬ በመቀጠል የመጀመሪያው ተጠቃሹ የልጅነት እድሜዬ ላይ ቤተሰቦቼ ኳስን እንድጫወት አይፈልጉም ነበርና ያን ያውቅ የነበረው የታዳጊነት ዘመን አሰልጣኜ ኑሩ ቀሰሰ ማሊያና ቁምጣ እየገዛ ያበረታታኝ ነበርና እሱን አልረሳውም፡፡ ሌላው በጥቁር አባይ ቡድን ሳለው ያሰለጠኑኝ አረጋዊ ወንድሙና እዮብ ማለ /አሞካቺ/ በፋሲል ከነማ ያሰለጠኑኝ ዘማርያም ወ/ጊዮርጊስና ውበቱ አባተ እንደዚሁም ደግሞ ጓደኛዬ ከድር ኤባና ውዷ ባለቤቴም ከእኔ ጀርባ በመሆን በመምከርና በማሰልጠኑም ስለረዱኝ ለሁሉም ምስጋናዬን አቀርብላቸዋለው፡፡
ሊግ፡- ቤተሰቦቼ ልጅ እያለው ኳስን እንድጫወት አይፈልጉም ነበር ብለሃል ለምን ነበር…?
ፍፁም፡- እነሱ ያኔ የኢትዮጵያ እግር ኳስ የትም አያደርስህም ብለው ስለሚያስቡና ስፖርቱም እንጀራ የሚያበላም እንዳልሆነም አድርገው ስለሚረዱ ነው ኳስን እንድጫወት የማይፈልጉት፤ በኋላ ላይ ግን የእኔን እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ ሲያዩ በጣም ደስ አላቸውና እኔን ማበረታታትና መደገፍም ጀመሩ፤ በእኔ የተነሳም አሁን ላይ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ዜናም እየከፈቱም ስለስፖርቱም መስማት ጀምረዋልና ለእነሱም አሁን ላይ ለሚያደርጉልኝ ማበረታታት ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ…?
ፍፁም፡- ፈጣሪ የአሁን ሰዓት ላይ ለዓለም ስጋት ከሆነው የኮሮና ቫይረስ እና ከሌሎችም አደጋዎች ይጠብቀን፡፡
https://t.me/Leaguesport

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P