Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ግብ በመሳት ታዋቂ ተጨዋች ሆኛለሁ” ፍሬው ሰለሞን /ሲዳማ ቡና/

“ግብ በመሳት ታዋቂ ተጨዋች ሆኛለሁ”
ፍሬው ሰለሞን /ሲዳማ ቡና/

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የአንደኛው ዙር የውድድር ተሳትፎና ጉዞ ሊጉ ሲጀመር ደካማ ውጤትን አስመዝግቦ የነበረው ሲዳማ ቡና አሁን አሁን ላይ ወደ ስኬታማነት በመምጣት ለሻምፒዮናነቱ ከሚፎካከሩት ቡድኖች ውስጥ አንዱ ሊሆን ችሏል።
የአሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌው ሲዳማ ቡና በሊጉ አጀማመር ላይ የውጤት ማጣቱን ተከትሎ የቡድኑ ደጋፊዎችም ከፍተኛ ተቃውሞን ያቀርቡበትም የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ ግን ወደ አሸናፊነቱ ሲመጣ በይፋ ክለቡንና ሀላፊዎቹንም ይቅርታ በመጠየቅ ደማቅ ድጋፋቸውን እየሰጡም ይገኛል።
ሲዳማ ቡና የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የአንደኛው ዙር ሲጠናቀቅ ውድድሩን የአራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ የሁለተኛውን ዙር ግጥሚያዎች እየተጠባበቀ ሲሆን የእዚሁ ቡድን ተጨዋች የሆነው ፍሬው ሰለሞን /ጣቁሩ/ ቡድናቸው በቀጣይነት በሚያደርጋቸው የአዳማ ከተማ እና የባህርዳር ከተማ የጨዋታ ጉዞዎቹ ምርጥ የሚባል ውጤትን በማስመዝገብ ደጋፊዎቻቸውን እንደሚያስደስቱም ይናገራል።
የሲዳማ ቡና የአማካይ ስፍራው ተጨዋች ፍሬው ሰለሞን /ጣቁሩ/ ከእዚህ ቀደም በነበረው የተለያዩ ክለቦች የውድድር ቆይታው ለቡድን ጓደኞቹ ጥሩ ጥሩ ኳሶችን ከማቀበል በተጨማሪ ጎሎችንም በማስቆጠር ይታወቅ የነበረ ሲሆን በእዚህ ከጎል በመራቁ ዙሪያም ይህንንም ብሏል “አዎን፤ በፊት ጎል በማስቆጠር በጣም እታወቅ ነበር፤ አሁን አሁን ደግሞ ጎል በመሳት ታዋቂ ተጨዋች ሆኛለሁ” በማለት ስለ ራሱ ወቅታዊ ብቃትም አስተያየቱን ሰጥቷል።

የሊግ ስፖርቱ አዘጋጅ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ ከሲዳማ ቡና ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ዙሪያና ስለ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ እንደዚሁም ደግሞ በመሰል ጉዳዮች ዙሪያ ከፍሬው ሰለሞን ጋር ያደረገው ቆይታ የሚከተለውን ይመስላል፤ ተከታተሉት። መልካም ንባብ ይሁንላችሁ።

በድሬዳዋ ከተማ ላይ በአንደኛው ዙር የነበራችሁ የውድድር ተሳትፎ መጠናቀቁ ይታወሳል፤ እስካሁን የሄዳችሁበት ጉዞ ምን ይመስላል?

“በመጀመሪያ ደረጃ ቡድናችን በክልላችን ሐዋሳ ውስጥ በተዘጋጀው የዙር ውድድር ላይ በሜዳችንና በደጋፊዎቻችን ፊት ከመጫወታችን አኳያና ካለው የአየር ሁኔታም አንፃር በደንብ አድርገን በውጤት በመጠቀም ነጥብን ለመያዝ ፈልገን የነበረ ቢሆንም የገጠመን ነገር ግን በተቃራኒው ነው። ያን ስላላሳካንም የቁጭት ስሜት ተፈጥሮብናል። ወደ ድሬዳዋ በተጓዝንበት ጊዜ ግን ካደረግናቸው 6 ጨዋታዎች ውስጥ በከፍተኛ የመነሳሳት ስሜት ላይ ሆነን ኳሱን ስለተጫወትነውና አምስቱን ግጥሚያዎቻችንን ደግሞ አሸንፈን 80 በመቶ ህልማችንን ያሳካንበትን ሁኔታ ስለፈጠርን ያ በጥሩ መልኩ የሚገለፅልን ውጤት ነው”።
በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ሐዋሳ ከተማ ላይ የነበራቸው የሊግ አጀማመር መልካምና የተሳካ ያለመሆኑ ምክንያት

“ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት በሲቲ ካፑ ላይ ጥሩ ነገርን ለማሳየት ብንችልም ወደ ዋናው የቤትኪንጉ ተሳትፎአችን ላይ ስንገባ ግን በዘጠኙ ጨዋታዎቻችን ላይ ከውጤት አኳያ ጥሩ አጀማመርን ለማሳየትና የሐዋሳ ቆይታችንንም በመሪነት አጠናቀን ወደ ድሬ ለመጓዝ ፍላጎት ቢኖረንም ከመጫወቻ ሜዳው ምቹ አለመሆንና ከሌላ ነገር ጋር ተያይዞም ከእኛ ቡድን አጨዋወት ጋር አብሮ ያልሄደልን ነገር ስላለ በእኛ ድክመት የተነሳ ጫና ውስጥ የከተተን ነገር ስለነበር ደጋፊዎቻችንን እና አመራሮቻችንን ሳናስደስት ቀረን” ።

ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉን ስትጀምሩ ዋንኛ አላማችሁ ምን ውጤትን ማምጣት ነበር?

“ዓመቱ መጀመሪያ ላይ እኛ ከኮቺንግ ስታፉ ጋር እንደ ግልም እንደ ቡድንም ተነጋግረንና ተዘጋጅተን ስንመጣ ቀጥታ እቅዳችንና አላማችን የነበረው የውድድሩ ሻምፒዮና በመሆን በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ላይ ለመሳተፍና ያ ካልተሳካ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ ወጥተንም በኮንፌዴሬሽን ካፑ ላይ ለመሳተፍ መቻል ነው። ከሁለት አንዱን ማሳካት አለብን ብለንም ነው ወደ ውድድሩ የገባነው። ሶስተኛ እና አራተኛ መውጣት ለእኛ ምንም ጥቅም የለውም፤ አስራ ሶስተኛ ከመውጣት አይተናነስም ብለን የሊጉን ውድድር የጀመርን ቢሆንም በሐዋሳ ቆይታችን ነጥብ ስንጥል ያን አናሳካም ብለን ብናስብም በኋላ ላይ ያሳካናቸው ጥሩ ውጤቶች ደግሞ ለአዳማው የሁለተኛው ዙር ውድድራችን ጥሩ ስንቅ ይሆነናል፤ ቅ/ጊዮርጊስ ላይም በነጥብ ለመድረስም ነው የምንጫወተው”።

ቤትኪንጉን ቅ/ጊዮርጊስ በመምራት ላይ ይገኛል፤ አካሄዱ ያስፈራችኋል……

“አሁን ላይ እኛን የሚያሰጋንም የሚያስፈራንም ቡድን አለ ብዬ አላምንም፤ ከእኛ ጋር ሁሉም ተጫውተዋል። እነ ቅ/ጊዮርጊስም ፋሲል ከነማም በአቋም ደረጃ እየተስተካከሉ የመጡ ቡድኖች ናቸው። ከእኛ ጋር በአንድ አይነት አቋም ላይ የምንገኝ ስለሆነ በነጥብ እንደራረሳለን ብዬም ነው የማስበው”።

በውድድሩ ላይ ስለነበራችሁ ጠንካራና ደካማ ጎን ምን ትላለህ? ምን ክፍተታችሁንስ ታስተካክላላችሁ…

“በውድድሩ ላይ በነበረን ቆይታ አሁን ላይ እንደ ጠንካራ ጎን የምንወስደው ጥሩም ሆንን አልሆንን የማሸነፍ አቅሙ አለን። ህብረታችን አንድ መሆኑም ነው አሸናፊ እንድንሆንም ያደረገን። ደካማው ጎናችን ብዬ የማስበው ደግሞ ኳሱን በምንይዝበት ጊዜ ለአጥቂው ክፍል ኳስ ለማቀበል ችኮላ እና ጥድፊያ መኖሩ ነው። በተለይ ተከላካይ ክፍሉ ኳስ ሲያገኝ ኳሱን መስርተን ከመጫወት ይልቅ ለአጥቂዎቹ ጎል ቶሎ እንዲያስቆጥሩ ለእነሱ ለመስጠት የምንጣደፍበት ሁኔታ ስላለ እና ሐዋሳም ላይ ዋጋ ያስከፈለን ነገር ስላለ እሱ ትልቁ ድክመታችን ነው። ይህን ችግር መቅረፍ ከቻልንም አዳማ ላይ የተሻለ ቡድንን ይዘን የምንቀርብም ይሆናል”።

በአንደኛው ዙር ያስፈራን ቡድን የለም ብለህ ነበር፤ ፈታኝ የሆነባችሁ ቡድንስ?

“እስካሁን ይሄ ነው የምንለው ቡድን ብዙ ባይኖርም አዳማ ከተማ ግን ከፈተኑን ቡድኖች መካከል ስሙ የሚጠቀስ ነው”።

የኢትዮጵያ ቡናው አቡበከር ናስር ዓምና በሊጉ በጣም ጎልቶ የወጣ ተጨዋች ነበር፤ እስካሁን በነበሩት ጨዋታዎችስ የቱ ተጨዋች ለየት ብሎ ቀርቦብሃል?

“ለእኔ እስከ አንደኛው ዙር በተደረጉት ጨዋታዎች ጎልተው በመውጣት ጥሩ የተንቀሳቀሱት ተጨዋቾች ሁለት ናቸው። እነሱም የሲዳማ ቡናው ይገዙ ቦጋለ እና የአዲስ አበባ ከተማው ፍፁም ጥላሁን በቀዳሚነት የምጠቅሳቸው ተጨዋቾች ናቸው”።

የዘንድሮ ሲዳማ ቡና ለአንተ በምን መልኩ ይገለፃል?

“በብዙ መልኩ የሚገለፅ ቡድን ነው ያለን፤ ሁሌም ኳስን መሰረት አድርጎም የሚጫወት ቡድንም አለን። እንደየተጋጣሚው አጨዋወትም ፕላን ቢ፣ ፕላን ሲ እና ሁሉንም አካተን የምንጫወትና ለደጋፊዎቻችንም ምቹ በመሆን መጥተንም የምንጫወት ነንና ይሄን ነው ልንል የሚገባን”።

የሲዳማ ቡና ደጋፊዎች ሊጉ ሲጀመር ይቃወሟችሁ ነበር፤ በኋላ ላይ ችግሩ ስለተቀረፈበት ሁኔታ

“ደጋፊዎቻችን በውጤት ማጣታችን ነበር እኛን እንዲቃወሙን ያደረገን፤ በኋላ ላይ ግን እነሱን ለመካስ ባደረግነው ያላሰለሰ ጥረት ወደ ስኬታማነቱ ስንመጣላቸው መጥተው ይቅርታ ጠየቁን። አሁን ላይ ደግሞ እነሱ የሚፈልጉትን ነገር እያደረግንላቸው ስለሆነና በአደጋገፋቸው እንደ አስራ ሁለተኛ ተጨዋች ሆነውም እያገለገሉን ስለሆነ ጥሩ ልንግባባም ችለናል”።

ቤትኪንጉ በአንደኛው ዙር ሲጠናቀቅ ለአንተ ምርጡ ቡድን ማን ነው?

“ምርጡ ቡድንማ ሊጉን እየመራ ስለሆነም ቅ/ጊዮርጊስ ነው”።

በአዳማ ከተማ የሚካሄደው የሁለተኛው ዙር ውድድር ምን መልክ ይኖረዋል?

“የሁለተኛው ዙር ጨዋታዎች ለሁሉም ቡድኖች ከባድ ውጥረቶች የሚካሄዱባቸው ናቸው፤ ከዛ ውጪ የአንደኛ ዙር ቁጭታቸውን ለመመለስም ቡድኖች ያለ የሌለ አቅማቸውንም አውጥተው ለመጫወትም ይመጣሉ። በተለይም ደግሞ የአዳማ ከተማ የመጫወቻ ሜዳ ጥሩ ከሆነ ደግሞ ሁሉም ቡድን የበለጠ የተሻለ ሆኖም ይቀርባል።

ቀደም ሲል በነበረው የሊጉ ጨዋታ የድሬዳዋ ሜዳ ከሐዋሳ የተሻለ ስለነበርና ምቹም ሜዳ ስለሆነ የግብ ድርቅ ችግሩ ተቀርፎ ነበር፤ ብዙ ጎሎችም ይገቡ ነበርና በአዳማ ከተማ የሚካሄደው ቀጣዩ የሊጉ ተሳትፎ የበለጠ ያማረም ይሆናል”።

በከዚህ ቀደሙ የኳስ ህይወትህ ብዙ ጎሎችን ታስቆጥር ነበር፤ አሁን የጎል ረሃብተኛ አልሆንክም…
“ሆኛለሁ እንጂ! በተለይም ደግሞ ወደ ሲዳማ ቡና ካመራሁ በኋላ በጣም ብዙ ኳሶችን በመሳትም ታዋቂ ተጨዋች ሆኛለሁ። በፊት በፊት አንድ ኳስ ካገኘው ጎል አገባ ነበር። በድጋሚ ልናገር አሁን በመሳት ታውቄያለሁ። ይሄ ግብ መሳቴም አንዳንዶቹ ደግሞ የምስታቸው የሚገራርሙ ኳሶች መሆናቸው ከምን የመጣና የመነጨ እንደሆነ ባላውቅም የሁለተኛው ዙር ላይ ግን በአህምሮም ሆነ በስነ-ልቦና ደረጃ ራሴን በጣም ጠንካራ በማድረግ እና ተዘጋጅቼም የምመጣባቸው እና ክፍተቶቼንም የማርማቸው ስለሚሆኑ ምርጡ ብቃቴን በውድድሩ ጎል በማስቆጠር ጭምር የማሳይ ነው የሚሆነው”።

በውድድር ቆይታችሁ ምርጡ አሲስትህ ለማን ያቀበልከው ነው?

“ለሀብታሙ ገዛኸኝ እና ለይገዙ ቦጋለ ከወላይታ ድቻ ጋር ስንጫወት ያቀበልኳቸውን ነው ለእኔ ምርጡ የምለው፤ በተለይ ለይገዙ የሰጠሁት በጣም ምርጡ ነበር”።

በ15ኛው ሳምንት ከሀድያ ሆሳዕና ጋር ስላደረጉት ጨዋታ እና የተመዘገበው ውጤት ይገባቸው እንደሆነ
“ውጤቱማ የሚገባን ነው፤ ከእነሱ ጋር ባደረግነው ጨዋታ ጥሩ ጥሩ አቅም ያላቸው ተጨዋቾች ስላላቸው ትልቅ ፈተና እንደሚገጥመን እናውቅ ነበር፤ ቀድመው ጎልም ሁሉ አገቡብን። ሀዲያ ሆሳህና ትልቅ ቡድን ነው። ኳሊቲ ያላቸው ተጨዋቾችንም ይዟል። በእዛ ጨዋታም እነሱ ተሸንፈውና እኛ ደግሞ አሸንፈን የመጣን ስለነበርንም ግጥሚያው ጠንከር ይልም ነበር። ከእረፍት በኋላም ባሉብን ክፍተቶች ላይ ከአሰልጣኛችን ጋር ስለተነጋገርንና የተጨዋቾች ለውጥም ስላደረግን ወዲያው እኛ ነብር ሆነን ቀረብንና በጊዜ የናፈቀንን ጎል ማስቆጠር በተግባር ለማሳየት ቻልን፤ ያ ግብም ሞራል ሆኖን ሁለተኛ ግብም ልናገባ ቻልን”።

የ15ኛው ሳምንት ተጋጣሚያችሁ ስለነበረው ሀድያ ሆሳዕና ምን የምትለው ነገር አለ….?

“ሀድያ ሆሳዕና ምርጥ ኳሊቲ ያላቸው ተጨዋቾችን የያዘ ቡድን ነው፤ ለምን እንደሚሸነፉም ይገርመኛል። በአንድ ስህተትም ተስፋ ይቆርጣሉ መሰለኝ አንድ ጎል ወይንም ሁለት ጎል ሲገባ እነሱም ጎል ለማስቆጠር እንደሚችሉም አቅሙ ኖሯቸው የመነሳሳት ችግር አለባቸውና ይሄን ክፍተት ነው ሊያርሙት የሚገባው”።

በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ወደ ሀድያ ሆሳዕና ልታመራ ተቃርበህ ነበር፤ ያ ሳይሳካ ቀርቶ ወደ ሲዳማ ቡና አመራህ። ስለ ሁኔታው የምትለን ነገር ካለ….

“አዎን፤ ወደ ሀድያ ሆሳዕናማ ላመራ ነበር። ፌዴሬሽንም ለመፈረም ሄጄ ነበር። ያም ሆኖ ግን እዛ ከደረስኩ በኋላ የክለቡን የቡድን መሪን ጨምሮ አንዳንድ የእኛ ስታፎችንም ከክስ ጋር በተያያዘ ፖሊሶች መጥተው ሲይዟቸው እኔ ደነገጥኩኝ። ለእዚህ ቡድን ፈርሜ ብጫወት ምን ዋስትና ይኖረኛልስ ብዬ ካሰብኩ በኋላም ወደፊት ችግር ውስጥ እንዳልገባ ብዬ ክለቡን ጥዬ በመሄድ ወደ ሐዋሳ መጣሁና ለሲዳማ ቡና ለመፈረም ቻልኩ”።

በአሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ በተደጋጋሚ ጊዜ ለመሰልጠን ችለሃል፤ እሱ እንዴት ይገለፃል?

“ከኮች ገብረመድህን ሀይሌ ጋር ከዚህ በፊት ለአራት ዓመታት በመከላከያ ክለብ ውስጥ ጥሩ ጊዜን አሳልፈናል። እሱ ከቡድኑ ጋር ከተለያየ በኋላም የተለያዩ ቡድኖችን ማለትም ጅማንና መቀለ 70 አንደርታን በሚያሰለጥንበት ሰዓት እኔን የመፈለግ ሁኔታ ቢኖርም ለቤተሰብ ቅርብ ለመሆን በሚል ወደ ሐዋሳ ከተማ ክለብ ካመራው በኋላ በድጋሚ ለመከላከያ በመቀጠል ደግሞ የገብሬ ሲዳማ ቡናን በሀላፊነት መያዝ መቻልም እኔን እንዲጠራኝ ስላደረገኝ በአሁን ሰዓት ከእሱ ጋር በጥሩ ሁኔታ ተግባብተን ስራዬን በመስራት ላይ ነው የምገኘው”።

የወልቂጤ ከተማ ቡድን ቆይታህ ጥሩ የማይባል ነበር?

“አዎን፤ ጥሩ አልነበርኩም፤ ያም ሆኖ ግን ወደ ሲዳማ ቡና ሳመራ በአሰልጣኝ ገብረመድህን በድጋሚ መለወጥን እንደምችል አውቅ ስለነበር ያንንም ነው ተመልክቼ ወደ ቡድኑ ያመራሁት”።

የእግር ኳስ ህይወት ቆይታህ ምርጡ ጊዜ

“በሐዋሳ ከተማ እያለሁ የነበረውን ነዋ! ምርጥ ቡድን ነበረን፤ ኳስንም እንደፈለግንም እንጫወታትም ነበር”።
ቤትኪንጉን አምናና ዘንድሮ አነፃፅር ብትባል ምላሽህ ምን ሊሆን ይችላል?

“የቡድኖችን መብዛት ከአምናው አንፃር ሳይ ጥሩ ፉክክር እየተደረገበት ይገኛል። ነባር ቡድኖችም ሆኑ ከታች የመጡትን ስመለከት ደግሞ አብዛኛው ቡድኖች ለዋንጫው እየተፎካከሩ እንዳለም አሳይቶናልና ድባቡ እንደ አጠቃላይ በጣም አስደስቶኛል”።

በወደፊቱ የኳስ ህይወትህ እንደ አንድ እግር ኳስ ተጨዋች ብዙ የምትመኛቸው ነገሮች አሉ ፤ ከእነዛ መካከል አንዱን ላንሳልህ፤ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ዋንጫ አልናፈቀህም?

“ናፍቆኛል እንጂ! ዋንጫውን ባነሳ በጣም ደስ ይለኛል። ከዚህ በፊት የጥሎ ማለፍና የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን ነው ከመከላከያ ክለብ ጋር ለማንሳት የቻልኩት”።

ባሳለፍከው የኳስ ህይወት ደስተኛ ነህ?

“እጅግ በጣም ደስተኛ ነኝ፤ ወደፊትም ደስተኛ እሆናለሁ “።
የተከፋክበት ጊዜስ

“በአንድ አንድ ነገሮች ልናደድ እችል ይሆናል እንጂ በኳስ ዓለም ተከፍቼ አላውቅም”።

እናጠቃል፤ በመጨረሻ አንድ ነገር በል

“በእስከዛሬው የኳስ ህይወቴ እዚህ ደረጃ ላይ እንድቀመጥ ከጎኔ ሆነው የረዱኝ ብዙ ሰዎች አሉ፤ ከእነዛ ውስጥም ቅድሚያ ፈጣሪ ልዑል እግዚአብሔር ይወሰድና ቤተሰቦቼ ይከተላሉ፤ ቀጥሎ ደግሞ ባለቤቴ ላምሮት ተጠቃሽ ናት። ከእሷ በኋላም በእኔ የተጨዋችነት ዘመን ውስጥ ያለፉትን አሰልጣኞችና የአሁኑን አሰልጣኜን ገብረመድህን ሀይሌን እንደዚሁም ደግሞ በሙገር ክለብ ውስጥ ያሰለጠኑኝን ማስተር አቶ አዳነ ገብረየሱስን ጨምሮ በጣም ላመሰግናቸው እወዳለሁ”።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P