ሊግ ስፖርት ጋዜጣን በቅዳሜ
በኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጦች ታሪክ ያለማቋረጥ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ለእትመት እየበቃች ያለችው ሊግ ስፖርት ጋዜጣ ነገም ለእናንተ ውድ አንባቢዎቿ የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የባህር ማዶ ዘገባዎችን ለንባብ በሚመች መልኩ ታቀርብሎታለች።
ሊግ ስፖርት ነገ በሚኖራት የሀገር ውስጥ ዘገባ ለሲዳማ ቡና በመጫወት ጎሎችን እያስቆጠረ ያለው ሳላህዲን ሰይድ ስለ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ፉክክር፣ ስለ ቡድናቸው ስለ ራሱ እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ አስተያየቱን ሰጥቷል።
በሲዳማ ቡና ምርጥ የጨዋታ ጊዜን እያሳለፈ የሚገኘው ሳላህዲንም ቡድናቸው ጠንካራ መሆኑን ገልፆ ሊጉን በሶሰተኝነት ለማጠናቀቅም መዘጋጀታቸውን ይናገራል። ሳላህዲን ከእዛ ውጪም የዘንድሮ የሊጉ ፉክክርን በተጨዋችነት የህይወት ዘመኑ ከእዚህ ቀደም አይቶም ሆነ ተመልክቶ እንደማያውቅ በመግለፅ ጥሩ ፉክክር እየተደረገበት እንደሆነና ዋንጫውንም የቀድሞ ቡድኑ ቅ/ጊዮርጊስ ቢያነሳ ደስ እንደሚለውም ተናግሯል።
ሊግ ስፖርት ጋዜጣ ከሳላህዲን ሰይድ ጋር በነበራት ሌላ ቆይታ ወደ ደቡብ አፍሪካ በፕሮፌሽናል ተጨዋችነት ስለሚጓዘው አቡበከር ናስርም የሰጠው አስተያየት ያለ ሲሆን ካለው ልምድ አኳያም ምክሩንም አስቀምጦለታል።
ሊግ ስፖርት ጋዜጣ በባህርማዶ ዘገባዋ ደግሞ ስለ አዲሱ የባየር ሙኒክ እንግዳ ሳዲዮ ማኔ እና አርሰናሎች ከአዲሱ ፈራሚያቸው ፋቢዮ ቬየራ ምን እንደሚጠብቁ እንደዚሁም ደግሞ የማንቸስተር ሲቲው ስተርሊንግ በመንታ መንገድ ላይ ስለመቆሙና ሌሎችን የሚወዳቸውን መረጃዎች በነገው እትሟ ይዛሎት ለንባብ ትቀርባለች።
ሊግ ስፖርት ጋዜጣ አታምልጦት፤ የነገው የፊት ለፊት ገፅም የሚከተለውን ይመስላል።