Google search engine

“የድሬን ሜዳ ሲተቹ የነበሩ ወገኖች አሁን ለውጡን አለማመስገናቸው ገርሞኛል” “እንደ ፖሊስነት ማዕረግ ሁሉ በአሰልጣኝነትም በደረጃ ማደግ እፈልጋለሁ” “እኔ ግን ማገዝና በትክክል መርዳት ስፈልን ከምክትል ይልቅ ረዳት መባልን እመርጣለሁ” “እንደ አሰልጣኝም ሆነ ተጨዋች ዳኞች ሊሳሳቱ ስለሚችሉ ማጋነን የለብንም” አሰልጣኝ ኮማንደር ሽመልልስ አበበ /ድሬዳዋ ከተማ/

ተወልዶ ያደገው ድሬዳዋ ልዩ ስሙ ፖሊስ መሬት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው የፖሊስ ቤተሰብ ውስጥ ነው ያደገው …አባቱም ፖሊስ እንደነበሩ ይናገራል….የዛሬው እንግዳችን ፖሊስ የሆነው በእግርኳሱ ነው ሲልም ይናገራል..መደበኛ ፖሊሰ ሆኜ አገለግላለሁ ድሬዳዋ ማሰልጠኛ ተቋም ውስጥ 8 ወር ሰልጥኛለሁ ስፖርትና ፖሊስነትን ጎን ለጎን መስራትም ጀምሬያለሁ ቅጥሬ ከ1991 ይጀምራል ሲልም ይናገራል ..በፖሊስነት ማገልገል ከጀመረ አሁን ወደ 25 አመት ይጠጋዋል… በኤሌክትሪሺያን ተመርቄያለሁ ነኝ ይላሉ ስፖርቱ በጋ ላይ ብቻ ስለሆነ ክረምት ሲሆን ወደ መደበኛ ስራዬ እመለሳለሁ ይህ ሁሉ ታሪክ የፖሊሱ የአሰልጣኙና የኤሌክትሪሺያኑ ኮማንደር ሽመልስ አበበ ነው። በተጨዋችነት ድሬዳዋ ከነማ፣ ምድር ባቡርና ድሬዳዋ ፖሊስ ተጫውቷል… አሁን ደግሞ የተጫወተለትን ድሬዳዋ ከነማ አምበል ሆኖ ከከፍተኛ ሊጉ ሲያድጉ ዋንጫ የተቀበለለትን ክለብ በአሰልጣኝነት እየመራ ነዋ ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ያደረገውን ቃለምልልስ እንካችሁ ብለናል

ሊግ :- ለሶስት ክለቦች ተጫውተሃል እስቲ እንዴት እንደነበር አስታውሰን..?

ሽመልስ:- በ1991 እስከ 1994 ለፖሊስ ተጫወትኩ 1994 በኋላ ፖሊስ ቡድን ሲፈርስ አንድ አመት አርፌ 1996 ፖሊስነቱን እየሰራሁ በውሰት ወደ ምድር ባቡር አቀናሁ, ድሬዳዋ ሱፐር ሊግ ከአለም ተጫውቻለሁ 97 ወደ መደበኛ ስራዬ ተመለስኩ ከዚያ ከጨርቅ ማዕረግ ከዋና ሳጅን እስከ ኮማንደርነት ደረጃውን ጠብቄ ደረስኩ በዚህም ደስተኛ ነኝ ፈጥኖ ፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም የአመራርነት ኮርስ ወስጃለሁ .. ከ2010 ጀምሮ ኮማንደር ተብዬ እጠራለሁ…

ሊግ :- አጠራሩ ኮማንደር.. ኮች.. የቱ ያይላል?

ሽመልስ:- እንደ ቦታው ይለያያል ስፖርቱ ውስጥና ሚሊታሪ ውስጥ በማዕረጌ እጠራለሁ ያለሁበት ቦታ ይወስነዋል በስሜ የሚጠሩኝም አሉ/ሳቅ/

ሊግ :- ባለ 2 ቁጥር ለባሽ የቡድኑ አምበል ሆኖ ያገለገሉትን ክለብ አሰልጣኝ የመሆን እድል ማግኘት ምን ትርጉም አለው..?

ሽመልስ:- አስገራሚ እድል ነው …በጣም ደስተኛ ነኝ ጥቂቶች የሚያገኙትን ነው ያገኘሁት በተጫወትክበት ክለብ ከከከፍተኛ ሊግ ሲያድግ አምበል ሆነህ ዋንጫ ተቀብለህ እንደገና ይህን ቡድን የማሰልጠን እድል ማግኘት ትልቅ ደስታ ዮፈጥራል በልዩ ደስታ ውስጥ ነኝ ሃላፊነቱን የሰጡኝን በሙሉ አመሰግናለሁ

ሊግ :- ኢትዮጵያ ቡናን ማሸነፍ ትርጉም አለው ..?

ሽመልስ:- አዎ የሚገርም ተነሳሽነት ነው ያለው ኢትዮጵያ ቡናና ቅዱሰ ጊዮሬጊስ በሊጋችን ከሚታወቁና ከሚጠሩ ክለቦች መሃል መሆናቸው ይታወቃል እናም ኢትዮጵያ ቡናን ማሸነፍ ትልቅ ትርጉምና ስሜት አለው በጨዋታው ተጨዋቾቻችን የተሻሉ ነበሩ በደጋፊው ፊት በመጨረሻ ደቂቃ ግባ መቆጠሯ በሜዳችን መሆኑ ትልቅ ደስታ ነበረው እውነት ነው ጠንካራውን ኢትዮጵያ ቡና ማሸነፍ ትርጉም አለው

ሊግ :- ደጋፊዎቹ እንዴት ይገለጻሉ..?

ሽመልስ:- የድሬዳዋ ስፖርት አፍቃሪ ኳስ የሚያውቅ ነው ከበፊቱ ጀምሮ ጥሩ ለተጫወተ ይደግፋል..አዝናኝ ጨዋታ ላሳየ ይደግፋልና የግድ የድሬ ቡድን መሆንን አለበት የሚል አይደለም እናም ለራሱ ቡድን ቅድሚያ ይሰጣል ከአሞበሪቾ ጋር ስንጫወት ዝናም ነበር ያ ሁሉ ዝናም ሳይበግረው ነው የደገፈን በጣም የሚደነቅ ደጋፊ ነው

ሊግ :- ለተጫወተ ከደገፈ በነሱ በኩል ያለው ጥቅም አናሳ ነው ማለት ይቻላል..?

ሽመልስ:- አድናቂ ነው ማለት ድፍን ብሎ ተጋጣሚውን ያደንቃል ማለት ግን አይደለም ጥሩ ለተጫወተ አድናቆት ይሰጣል እንጂ ሙሉ በሙሉ ይደግፋል ማለት አይደለም

ሊግ :- ፖሊስም መከላከል ላይ ያተኩራል እንደ ቡድንስ..?

ሽመልሽ:- / ሳቅ/ የፖሊስ የመጀመሪያ ተግባር አደጋ እንዳይደርስ ወንጀል እንዳይሰራ መከላከል ነው የቡድንም ዋና መሰረት ግብ እንዳይቆጠር ማድረግ ነው/ሳቅ/

ሊግ :- በዮርዳኖስ አባይና አስራት አባተ ጊዜ ረዳት ነበርክ … የእውነትን ነበር ረዳትነትህ ..? ሰርሳሪ አልነበርክም..?

ሽመልስ:- /ሳቅ/ ጥሩ ጥያቄ ነው ግን ሁለቱ አሰልጣኞች በተሻለ ቢመልሱ ደስ ይለኝ ነበር ሰው ለራሱ ስለሚያደላ ..በአንድ ጊዜ ቦታውን ለመያዝ ማሰብ ልክ አይደለም መማር ማወቅ መለወጥ እፈልጋለሁ እንደ ፖሊስነት ማዕረግ ሁሉ በአሰልጣኝነትም በደረጃ ማደግ እፈልጋለሁ መርዳት እንጂ መሰርሰር የፖሊስም ዲሲፕሊን አይደለም በግሌ ምክትል ከሚለው ረዳት አሰልጣኝ የሚለው ይመቸኛል ረዳት ልብ ይጠይቃል እውነተኝነትም እንደዚሁ…ለዋናው አሰልጣኝ እገዛ ማድረግ ምቹ ሁኔታ መፍጠር ነው የምፈልገው ሌላው እንደ አሁኑ እግዚአብሄር ጊዜውን ጠብቆ ያመጣዋል። በርግጥ የስያሜ ደረጃን ስታየው ምክትል ሁለተኛ ረዳት ሶስተኛ ማለት ነዋ እኔ ግን ማገዝና በትክክል መርዳት ስፈልን ከምክትል ይልቅ ረዳት መባልን እመርጣለሁ

ሊግ :- የፕሪሚየር ሊጉ ፉክክር ጠንካራ ነው ማለት ይቻላል..?

ሽመልስ:- አዎ ሊጉ ጠንካራ ነው ሁሉም ቡድን በቀላሉ አይሸነፍም አሸናፊውም ድል ከቀናው በከባድ ትግል ነው ላለመውረድ ያሉ ክለቦቼ እላይ ያለትን እየፈተኑ ነው ሊጉ ለውጥማ አለው

ሊግ :- የዋንጫ መውሰድ ጭላንጭል ያሳየ ክለብ አለ..?

ሽመልስ:- አይመስለኝም በሩ ክፍት ነው አሁን መገመት አይቻልም ገና በርካታ ጨዋታ አለ.. አሸናፊነቱ ክፍት ነው እገሌ የሚባል ክለብ ይወስዳል የምትልበት ጊዜ አይደለም ጥሩ ናቸው ሲባሉ ነጥብ ሲጥሉ እያየንም ስለህነ ለግምቱ ገና ነው አሁን መፍጠን የለብንም አንደኛ ዙር ላይ ተገንጥለው የነበሩ ነጥብ ጥለው እንደገና ሲደረስባቸው አይተናልና ትንሽ ጨዋታዎቹን እንየው አንድ ቡድን አምልጦ ብቻውን ይሄዳል ማለት ይከብደኛል የማይሸነፍ ቡድን አልገጠመኝም

ሊግ :- ዳኝነቱን እንዴት አገኘኧው..?

ሽመልስ:- ስለዳኝነት ብዙም ባላወራ እመርጣለሁ ሁሉም የየራሱ ድርሻ አለውና ዳኝነት ላይ ያለ ድርሻዬ አልገባም ሰዎች ስለሆኑ ሊሳሳቱ ይችላሉ። ሆኖ ብሎ መሳሳት እንጂ የዳኝነት ስህተት ይጠበቃል። እንደ አሰልጣኝም ሆነ ተጨዋች ዳኞች ሊሳሳቱ ስለሚችሉ ማጋነን የለብንም ሜዳ ላይ ያለው ሰዋዊ ስህተት የሚጠበቅ ነው ነገር ግን አደራ የምለው የቤት ስራ ይዘው መጥተው እንዳይሳሳቱ ነው እስካሁን ግን ጫፍ የደረሰ ስህተት አላየሁም

ሊግ :- የቡድናችሁ እቅድ ምንድነው

ሽመልስ:- እንደ ድሬዳዋ ከተማ አመቱ ሲደመር እቅድ ያልነው ከ1-5 መጨረስ ነው በመሃል ላይ የነጥብ መጣልና የውጤት መዋዠቅ በመከሰቱ ተንገዳግደን ነበር አሁን ደግሞ እግዚአብሄር ይመስገን ጥሩ አቋም ይዘናል ጥሩ ተፎካካሪ መሆንን ነው ያቀድነው ለዚህም ከፊታችን ያለውን ጨዋታ ላይ ማሸነፍ ነው ተጨዋቾቻችን ላይ ያለው አንድነት መተሳሰብ የተሻለ ደረጃ ላይ ያደርሰናል ብዬ አምናለሁ።

ሊግ :- የቀድሞ የፋሲል ከነማ ተጨዋች ሱራፌል ዳኛቸው ተከላካዮች ብቻ ሳይሆኑ ሜዳውም ኳስ እየቀማን ነበር አለ የሜዳ ችግር አሁን ተወገደ ማለት ይቻላል…?

ሽመልስ:- ሲጀመር በሱራፌል አባባል እስማማለሁ እውነት ነው.. ሱራፌል ይህን ሜዳ ሳያየው መሄዱ ይቆጨኛል እሱም ሲጫወት ባየው ደስ ይለኝ ነበር። አንዳንዴ ኳሱን ልትቆጣጠር ስትል ሜዳው ተጋጭቶ ለሌላው ተጋጣሚ ሊሰጥብህ ይችላል አሁን ግን አይታሰብም ሜዳው ቀን ወጥቶለታል ..የቀረውም ክለብ ቅሬታ ማቅረብ አይችልም ሜዳው ዝናብ ዘንቦበት እንኳን ለጨዋታ አላስቸገረም…የድሬን ሜዳ ሲተቹ የነበሩ ወገኖች አሁን ለውጡን አለማመስገናቸው ገርሞኛል ምነው ዝም አሉ ሊጉ ሲጀመር ሀይለኛ ዝናብ ዘንቦ ጨዋታውን ሳያስተጓጉል መጨረሱ ይገርማል ሰው ሰራሹ ስታዲየም በተፈጥሮ ተፈትኖ አልፏል። ያም ሆኖ አለማመስገናቸው ገርሞኛል። አሰልጣኝ ለሚፈልገው ታክቲክና ቴክኒክ ሜዳው ተመችቶ ተጨዋቹ ሮሮ እንዳያሰማ ያደረጉትን አለማመስገን ግን ልክ አይደለም

ሊግ:- ባለትዳርና የአንዲት ሴት ልጅ አባት ነህ.. እስቲ አስተዋውቀኝ..?

ሽመልስ : ባለቤቴ ዝናሽ በቀለ ልጄ ቤተልሄም ሽመልስ ይባላሉ በኔ ስራዎች ይጨነቃሉ..ባለቤቴ ተጨዋችም ሆኜ አሰልጣኝም ሆኜ ውጤት ሲጠፋ ትጨነቃለች የእግርኳስ መጥፎ ጎኑ ይሄ ይመስለኛል በዚህች አጋጣሚ ከልብ አመሰግናቸዋለሁ እወዳቸዋለሁ…

ሊግ ;- ጨረስኩ….የመጨረሻ ቃል..?

ሽመልስ:- የመጀመሪያው ምስጋናዬ ለዚህ ላደረሰኝ እግዚአብሄር ይድረስልኝ …ገና ጅማሬ ላይ ነኝ ረጅም ጉዞ ይጠበቅብኛል እኔ ወደ አሰልጣኞነት እንድመጣ ያበረታታኝ የገፋፋኝ አሰልጣኝ ዶ/ር ኢያሱ ነው ድሬዳዋ ላይ አሰልጥኖኝ ወደ ኮቺንጉ ግባ ይለኝ ነበር ለዚህም አመሰግናለሁ..አሰልጣኝ የነበረው ኮማንደር ሰለሞን ፣ ጥሪ አድርጎ ወደ አሰልጣኝነቱ የሳበኝ ዮርዳኖስ አባይ፣ ምቹ ሁኔታ የፈጠረለኝ ዋና ስራ አስኪያጁ እስከዳር ዳምጠው፣ ከፖሊስ ቢሮ ወደ አሰልጣኘነቱ እንድመጣ ሙሉ ድጋፍና ፍቃድ የሰጠኝ ፖሊስ ኮሚሽኑን በተለይ ኮሚሽነር አለሙ ፣ ከንቲባችን ከድር ጁሃርን አመሰግናለሁ… በአጠቃላይ ቤተሰቦቼን ጓደኞቼን ደጋፊውን የድሬ ማህበረሰብ በኔ ነገር ላይ ድጋፋቸውን ላደረጉ በሙሉ ከልብ አመሰግናለሁ።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this:
P